TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አላማጣ ቆቦ‼️

የትግራይን ክልል ከአማራ ክልል የሚያገናኘው አላማጣ ቆቦ መስመር ለተሽከርካሪዎች ከተዘጋ 5 ቀናት አስቆጥሯል። መንገዱ የተዘጋው በአላማጣ ከተማ #የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱላቸው በጠየቁ የቆቦ ከተማ ወጣቶች ነው ተብሏል።

የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምርያ እንዳስታወቀው ችግሩን #በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት #ውይይት እየተካሄደ ነው።

የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው - መንገዱ በመዘጋቱ ለስራቸውን #እንቅፋት እየፈጠረባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ(የትላንት ምሽት ዘገባ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ‼️

ከሰሞኑ በሀገራችን በሚገኙ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ #ያልተፈፀመን ድርጊት የተፈፅመ በማስመሰል በተማሪዎች መካከል #መጠራጠርና አለመረጋጋት ተፈጥሮ የትምህርት ሂደቱን የማደናቀፍ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲም አንዲት ተማሪ ላይ በደረሰ #የአስገድዶ_መድፈር ጥቃት ህይወቷ አለፈ የሚል #የሀሰት መረጃ በማሰራጨት በተማሪዎች መካከል ድንጋጤና ተቃውሞ ተፈጥሮ #የብሄር ተኮር የቡድን ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ ተደርጎ ትናንት ምሽት ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በዋናው ግቢ ጥቂት ተማሪዎች በቡድን እንዲደባደቡ ምክንያት ሆኗል፡፡ በግጭቱ በተማሪዎች ላይ የከፋ ጉዳት አልተከሰተም፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ ዛሬ በከፊል የተካሄደ ሲሆን በዩኒቨርሲቲያችንም ዛሬ የፀጥታ ችግር ያልተከሰተ ሲሆን የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታይ ተማሪዎችም ዓመታዊ የቅዱስ ሚካኤል የንግስ በዓልን ገንደ ጄይ አካባቢ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ተገኝተው አክብረው ተመልሰዋል፡፡

በተማሪዎቹ መካከል ተከስቶ የነበረው ችግር ዳግም እንዳይከሰት ሊደረግ በሚገባው ጥንቃቄ ዙሪያ ከተማሪዎች ተወካዮችና የጸጥታ አካላት ጋር ዛሬ #ውይይት የተደረገ ሲሆን ተማሪዎችም ችግሩ ዳግም እንዳይከሰት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር እንዲቻልም ነገ ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የኃይማኖት አባቶች ፤ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በሚገኙበት የዕርቅና የይቅርታ መድረክ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል፡፡

ከሰሞኑ በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ የከፍተኛ ትምህርትና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም መግለጫ አውጥቷል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ‼️

የተቋሙ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ የተፈጠረው ችግር በዘላቂነት እንዲፈታ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉንም ያካተተ #ውይይት ሊደረግ ይገባል ብለዋል። ትላንት የተወሰኑ ተማሪዎች ተስማምተው ግቢው ውስጥ ሰላም ወርዶ የነበር ቢሆንም ምሽት ላይ ተማሪ ተጋጭቶ ነበር በዚህም የፀጥታ አካላት እርምጃ ውስደዋል ሲሉ ተማሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.አ.ሳ.ቴ🔝የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ተማሪዎች ከፀጥታ አካላት ጋር #ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዳሴው ግድብ‼️

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለዩ ክፍተቶችን በማስተካከል
በፈረንጆቹ 2022 #እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

በዛሬው ዕለት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ #ውይይት እየተካሄደ ነው።

ጥልቅ ጥናትና ምርምር ስራ ሳይከናወንለት ግንባታው በመጀመሩ ምክንያት ግንባታ ጊዜው ሊጓተት እንደቻለ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያስከተለው ጉዳት ሀገሪቷ በየዓመቱ 800 ሚሊየን ዶላር እንድታጣ አድርጓታል ተብሏል።

የግንባታው ስራው በአሁን ወቅት የሚገኝበት ደራጀም በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ወቅት ይፋ ሆኗል።

በዚህም በሳሊኒ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ምህንድስናው ስራው 82 በመቶ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው ደግሞ 25 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል በውይይቱ ወቅት።

በአጠቃላይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 65 በመቶ መጠነቀቁ ተነግሯል። ከዚህ ባለፈ የግንባታው ፅህፈት ቤት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልና ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።

የህዝባዊ ተሳትፎን ፣ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ባለው የሶስትዮሽ ግንኙነት እና የኃይል ሽያጭ ትስስር ላይ ትኩረት ባደረጉ አራት ጉዳዮች ላይ ውይይቱ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከዛላምበሳ ግምባር የጦር መሳሪያ ጭነው ወደ መሀል ሀገር ሲንቀሳቀሱ #የታገቱ የመከላከያ ተሽከርካሪዎች #ተለቀዋል። የመከላከያ ተሽከርካሪዎቹ የተለቀቁት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር #ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ በመደረሱ ነው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፖሊስ በቂ ዝግጅት አድርጓል~ሀዋሳ‼️

በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ። 

የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር #መስፍን_ዴቢሶ ለኢዜአ እንደገለጹት ነገ በሃዋሳ የሚካሄደውን ሰልፍ ተከትሎ #ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተደርጓል።

የከተማው ፖሊስ ከዞን፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋልም ብለዋል፡፡

ፖሊስ አዛዡ እንዳሉት ከሪፈራል አደባባይ ጠዋት አንድ ሰዓት የሚጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ መዳረሻው ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ነው፡፡

ሰልፉ ወደ ብሉናይል የሚያወጣውን አስፓልት ይዞ ተስፋዬ ግዛው ህንጻ አደባባይ ሲደርስ ወደ ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚገባና ማጠቃለያውን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ምክንያት መንገዶቹ ለተሸከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ያሉት ኮማንደር መስፍን፤ በበቂ የፀጥታ ሃይል ጥበቃ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

የከተማው ነዋሪ በሰልፉ ምክንያት ስጋት ውስጥ እንዳይገባ በየክፍለ ከተማው #ውይይት መደረጉን ገልጸው ህዝቡም ለሰልፉ ሰላማዊነት የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ የሚዲያ ተጠሪ አቶ ሳሙኤል በላይነህ በበኩሉ የሲዳማ ብሄር በክልል የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄውን ተከትሎ ህዝበ ውሳኔው በመዘግየቱ የተዘጋጀ ሰልፍ ነው” ብሏል።

ዓላማውም “ከዞን ምክር ቤት ጀምሮ በክልሉ ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝበ ውሳኔ ለምርጫ ቦርድ የተላከው ሪፈረንደም ጥያቄ ዘግይቷል ይፋጠንልን” የሚል መሆኑን ተናግሯል።

ጥያቄው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ተከትሎ የቀረበ ቢሆንም ምላሹ በመዘግየቱ በዞኑ ካሉ ወረዳዎችና ከሃዋሳ ከተማ የተውጣጡ ነዋሪዎች መንግስትን በሰላማዊ መንገድ የሚጠይቁበት እንደሆነም ተናግሯል፡፡

“ሰልፉ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከከተማው ፖሊስና ከሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው” ብሏል፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ የመንግስት አካላት፣ የተለያዩ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የሰልፉ ደጋፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia