TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አፋልጉኝ!
ሚስተር አርጁን ራሳድ!

በ14 አገሮች በስድስት አህጉሮች እንዲሁም በአገራቸው ደግሞ በስድስት ግዛቶች በመዘዋወር ደም በመለገስ የሚታወቁት ሚስተር #አርጁን_ራሳድ_ማናሊ የተባሉት አሜሪካዊ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2011 ዓም በአዲስ አበባ በመገኘት ለ168ኛ ጊዜ ደም ለግሰዋል። ሚስተር አርጁን ራሳድ ማናሊ በራሳቸው ተነሳሽነት ከአሜሪካ ድረስ በመምጣት ደም ከመለገስ ባሻገር የአገራችን ለበርካታ ጊዜ ደም የለገሱ ግለሰቦች የእውቅናና ሽልማት እንዲያገኙ መረሃ ግብር እንዲዘጋጅ በማድረግ ወጪውን ሙሉ ለሙሉ ሸፍነዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ፦

"የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ፕላን ለማስጠበቅ አረንጓዴ ቦታዎችን፣ ወንዝ ዳርቻዎችን፣ አስተዳደሩ ካሳ ከፍሎባቸው ቤት የተሰራባቸውን እና ባለሃብቶች #ከተፈቀደላቸው በላይ የያዙትን ቦታ ላይ የተሰሩትን ቤቶች ዛሬ ማፍረሱ ይታወቃል። ሆኖም በFB ገጽ ላይ Etiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የቤቶችን ፈረሳ በተመለከተ #በብሄር ላይ የተመሰረተ ፈረሳ ነው፣ ሚዲያ እንዳይገባ ተከልክሎአል ከሁሉ በላይ ደግሞ ሁለት ሰው #ሞቶል እንዲሁም ቆስለዋል በማለት FB ላይ የለጠፈው ነገር ፍጹም #ውሸት እና በብሔር ላይ የተመሰረተ ፈረሳ የለለ ሚዲያዎችም የነበሩ እና አንድም ሰው እንኮን ሊሞት የቆሰለም ያልነበረ መሆኑን ከተቆቆመው ኮማንድ ፖስት ማረጋገጥ ተችሎል።በመሆኑም Ethiopian Dj ም ሆነ ለሎች በ FB ላይ የምለጥፉ ከእንደዚህ አይነት ድርጊት ብርቁ መልካም ነው እንላለን።"

©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 11 በፎቶግራፍ🔝በትግራይ ክልል #መቐለ ከተማ የተከበረው የህወሓት 44ኛ የምስረታ በዓል። "ስእላዊ መግለፂ ኣከባብራ በዓል 11 ለካቲት 2011 ዓ/ም'

#Tigray #መቐለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ወለጋ‼️

በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረት #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።

የኮማንድ ፖስቱ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ #ደጀኔ_ገብረማርያም እንደገለጹት በዞኑ በነበረው የፀጥታ ችግር የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት ተመልሰዋል። ከነዚህም 110 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 41ሽጉጦችና 20 የእጅ ቦምቦች ይገኙበታል። እንዲሁም 326 ኋላ ቀር ጠመንጃዎችና ከአራት ሺህ የሚበልጡ ጥይቶች መመለሳቸውን አስረድተዋል።

በተጨማሪም 50 በርሜል ነዳጅ፣ 14 የመንግሥትና የግል ተሽከርካሪዎችና 28 የሞተር ቢስክሌቶች መመለሳቸውን አቶ ደጀኔ ተናግረዋል።

የዞኑ ሕዝብ የተዘረፉትን የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት ለማስመለስ በተደረገው ጥረት ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው መንቀሳቀሱን ገልጸዋል።

በዞኑ በ20 የገጠር ወረዳዎችና ሦስት ከተሞች በተካሄዱት የሰላም ኮንፈረንሶች አንፃራዊ #ሠላም በመስፈኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ በካማሺና የምዕራብ ወለጋ ዞኖች መካከል የሕዝብ ለሕዝብ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡

የመነ ሲቡ ወረዳ የአስተዳደርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ #ለታ_አባተ በሰጡት አስተያየት ሕዝቡና ኮማንድ ፖስቱ ባደረጉት ክትትልና ቁጥጥር የጦር መሣሪያዎቹ መመለሳቸው ለዞኑ ሰላምና ጸጥታ መከበር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡ አሁንም ያልተመለሱትን የጦር መሣሪያዎች ለማስመለስ ተቀናጅቶ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

የመንዲ ከተማ የአስተዳርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ #ዳኖ_ኢተፋ በበኩላቸው የተዘረፉት የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ንብረት መመለሳቸው ለሰላም ያላቸው ፋይዳው ጉልህ ነው ብለዋል። የምዕራብ ኢትዮጵያ ከዚህ ዓመት መግቢያ ጀምሮ በተከሰተው ግጭት ሰላምና ጸጥታው ታውኮ መቆየቱ ይታወሳል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል። በያዝነው ሳምንት ብቻ 3,685 ቤቶች እንደሚፈርሱ የከተማው ከንቲባ ወይዘሮ #ሀቢባ_ሲራጅ ለOMN ተናግረዋል። በቀጣያ 12ሺ ቤቶችን ለማፍረስ እቅድ መያዙንም ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ እንደሚሉት ቤቶቹን ለማፍረስ የተገደዱት የከተማው #መሪ_ዕቅድን_በመጣስ ለአረንጓዴ ቦታ (green area) በተከለለ ስፍራ በመሰራታቸው ነው። መኖሪያ ቤታቸው እንዲፈርስ የተወሰነባቸው ዜጎች በበኩላቸው በከተማው ለአመታት መኖራቸውንና በህጋዊ መንገድ ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸውን ለዋልታ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው፡፡ በቅርቡ ከተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ወደ ምዕራብ የተላኩት የአባገዳዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ #በየነ_ሰንበቶና አቶ #በቀለ_ገርባ ከህዝቡ ጋር በመሆን ለኦነግ አባላት አቀባበል እያደረጉላቸው ነው፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia