ስካይ ላይት ሆቴል🔝
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ለአፍሪካ መሪዎች በስካይ ላይት ሆቴል የእራት ግብዣ አደረጉ። በእራት ግብዣው ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
• ብዙዎች አፍሪካ ሲባል ወደ አይምሯቸው ምን እንደሚመጣ ቢታወቅም ለኔ ግን መልካም ተስፋ ያለባት አህጉር ናት
• አፍሪካ ከማንም በላይ የመልማት ተስፋ የሰነቀች አህጉር ናት፣ ከእንቅልፏም ነቅታለች
• ነገር ግን አፍሪካ ስኬታማ ለመሆን አሰቀድማ ከተለየችበት ማንነት መግኘት አለባት
• የዚህ ዘመን አፍሪካዊያን መተባበር መተማመን እና መደመር ያስፈልገናል፡፡ ከዚህ የተሻለ ምቹ ሁኔታ አይገኝምና
• አፍሪካ ከረሷ አልፎ በሰላምና ብልጽግና ለአለም ማበርከት ትችላለች
• የለውጥ ባቡር ያገኘውን እየደመረ ጉዞውን ጀምሯል፡፡ ኢትዮጵያም በግስጋሴ ላይ ትገኛለች፤ ባቡሩም ለሁሉም የሚበቃ ነው፡፡
• ከእኛም አልፎ መደመራችን አለም አቃፋዊ ይዘት እንዲኖረው መስራት ይኖርብናል
• የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ መሪ ለነበሩት ቀደማዊ ኃይለስላሴ ሃውልት እንዲቆምና እንዲታወሱ በማድረጉ ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡
• የትላንት ሳይኖር የዛሬው እኛ ያሌለን በመሆኑ የትላንቱን ማመስገን ተገቢ ነው።
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ሰላምና ፀጥታ እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ በመሰራቱ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስተፌ ሙሁመድ የመንግስታቸውን የአምስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት አቀርበዋል። በሪፖርታቸውም አዲሱ የክልሉ አመራር ሥራ ከጀመረ ወዲህ በክልሉ ሲስተዋል የነበረው ብጥብጥ፣ ረብሻና አለመረጋጋት በሙሉ እንዲወገድ መስራቱን አመልክተዋል። በክልሉ ሊከሰቱ የነበሩ ሰላሳ የጎሳ ግጭቶች በውይይት እንዲፈቱ በመደረጉ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ መረጋጋት እየታየ መምጣቱን ተናግረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስካይ ላፕት ሆቴል🔝
ትላንት ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአፍሪካ መሪዎች ያደረጉት የእራት ግብዣ!
ፎቶ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

የዕለቱ መልዕክት...
ሰላም በሌለበት ስለምንም ጉዳይ ልንነጋገር አንችልም፤ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው። ዛሬ ሰላም ብንሆን ነው ይህንን ፅሁፍ እንኳን ተረጋግተን ምናነበው፤ ሰላምን ወታደር፤ ፖሊስ አይሰጠንም ቤተሰባችን ሰላም ከሆን ሀገራችም ሰላም ትሆናለች!! ሁላችንም ለራሳችን ስንል ሰላማችንን እንጠብቅ!
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAENjSkUg0WenkgR_CA

ዋና ሳጅን እቴነሽ ላይ 11 ክሶች ተመሰረቱበት‼️
በሽብር ወንጀል ተፈርጀው ታስረው በነበሩ የኦነግና አርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ላይ ሽንት በመሽናት፣ ጥፍር በመንቀልና በሌሎችም ዘግናኝ የተባሉ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥራ የታሰረችው፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የቀድሞ አባል ዋና ሳጅን #እቴነሽ_አረፉዓይኔ 11 ክሶች ተመሠረቱባት፡፡
ተከሳሿ በተለምዶ ማዕከላዊ ይባል የነበረውና በቅርቡ በተዘጋው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን መሪና መርማሪ ሆና ስትሠራ፣ ካልተያዙ ግብረ አበሮቿ ጋር በመሆን በሽብር ተግባር ወንጀል ተፈርጀው በታሰሩ ዜጎች ላይ ፈጽማለች የተባለችውን የወንጀል ድርጊት፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡
ተከሳሿ ተመስገን ፀጋዬ፣ ወርቁ ፈረደ፣ ዘመነ ምሕረት፣ ሀብታሙ ሚልኬሳ፣ ዳንኤል እንየው፣ ጌትነት አማረ፣ አንሙት ታምሩ፣ ሽመልሽ አድማሴና ሌሎች ተጠርጥረው የታሰሩ ግለሰቦች ላይ የመመርመር ሥልጣን ሳይኖራት፣ ሌሊት በመጥራት ማሰቃየቷን፣ በሐሰት የእምነት ቃል እንዲሰጡና ሳያነቡ እንዲፈርሙ፣ ያልተያዘ ኤግዚቢት ላይ እንዲፈርሙ ስታስገድድና ስታስፈርም እንደነበር ክሱ ይገልጻል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ምንም ዓይነት ድርጊት እንዳልፈጸሙ ምላሽ ሲሰጧት፣ በማስመሪያ ፊታቸውን እንደመታቻቸው፣ በአፍንጫቸው እስክርቢቶ በማስገባትና ለረዥም ጊዜ እጃቸውን አሥራ በማንጠልጠልና ራቁታቸውን በጠባብ ክፍል ውስጥ ታስቀምጣቸው እንደነበር በክሱ ተገልጿል፡፡ ፂማቸውንና የብብታቸውን ፀጉር ፒንሳ በሚመስል ነገር በመንቀል ራሳቸውን ስተው ሲወድቁ ውኃ በመድፋትና ‹‹ገና አፍህ ላይ እሸናብሃለሁ›› በማለት፣ ጀርባቸው ላይ ሽንቷን መሽናቷንና ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሟን ክሱ ያብራራል፡፡
‹‹የግንቦት ሰባት አርበኞች አባል ነን›› ብለው እንዲያምኑ ሱሪያቸውን በማስወለቅና የውስጥ ሱሪያቸውን በአፋቸው ውስጥ በመጠቅጠቅ፣ ብልታቸውን በማስመሪያ ትመታቸው እንደነበርም አክሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹን ከባድ ስፖርት በማሠራትና በመደብደብ፣ እንዲሁም ሁለት እጆቻቸውን በካቴና በማሰርና በግንብ ላይ በተሰካ ብረት ላይ በማንጠልጠልና በኤሌክትሪክ ገመድ በመግረፍ ቃላቸውን እንደተቀበለቻቸውም ክሱ ያስረዳል፡፡
ታሳሪዎቹን በጠረጴዛ ላይ በማስተኛት፣ በጥፊ በመምታት፣ ጀርባቸው ላይ ሽንቷን በመሽናት፣ የቪዲዮ ማስረጃ፣ መጻሕፍትና የኦነግ ዓርማ ከእነሱ እጅ የተገኘ መሆኑን አምነው እንዲፈርሙ ታስገድዳቸው እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ በስቴፕለር መምቻ ጭንቅላታቸውን በመምታትና ጎናቸውንም በመርገጥ ታሰቃያቸው እንደነበርም አክሏል፡፡
መርማሪዎቹ በጋራ በመሆን የታሳሪዎቹን እጆች በማሰርና በእጃቸው መሀል እንጨት በመክተት ገልብጠው በማቆየት፣ ውስጥ እግራቸውን በኤሌክትሪክ ገመድ እንደገረፏቸውና እንዳሰሯቸው ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡ ተከሳሿ ተጠርጣሪዎቹን በኤሌክትሪክ ገመድ ከመግረፏም በተጨማሪ፣ በብረት ጉጠት የአውራ ጣታቸውን ጥፍር መንቀሏንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡
በጠረጴዛ መካከል በማስገባት መዘቅዘቅ፣ ሽንቷን በሰውነታቸው ላይ መድፋት፣ በብልታቸው ላይ ውኃ እንደምታንጠለጥል በመንገር ታስፈራራና የሰብዓዊ መብጥ ጥሰት ስትፈጽም እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቷል፡፡ በአጠቃላይ ተካሳሿ ሥልጣኗን ያላግባብ በመገልገል በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸመችው የማይገባ አሠራር መጠቀም ወንጀል መከሰሷን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቷል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር