TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ አረፉ‼️

ኮ/ል #ታደሰ_ሙሉነህ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የ71 ቅጥር አባል ናቸው። በቀደመው አየር ኃይል በሚግ-23 ተዋጊ ስኳድሮን ውስጥ በምሥራቅም ሆነ በሰሜን ግንባር ተሰልፈው ከፍተኛ ተጋድሎ ካደረጉት የአገራችን ኢትዮጵያ ባለውለታ አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ።

በ1991 ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ በመቃወም ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።

የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን በመምራት በኤርትራና በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ምዕራብ በረሃዎች ሳሉ በኤርትራ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር በመዋላቸዉ ለበርካታ አመታት ደብዛቸው፤ አድራሻቸው ጠፍቶ ነበር።

ከወራት በፊት ኮ/ል ታደሰ ከኤርትራ እስር ነፃ ይሁን እንጂ ጤንነታቸው ታውኮ ሰውነታቸው እንደልቡ በማያዝቡት ሁኔታ በመሆኑ በህክምና #በህንድ ሐገር ሲታከሙ ቆይተው ጥር 27 ቀን 2011 ዓም አርፈዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጸመ‼️

የኮሎኔል #ታደሰ_ሙሉነህ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ፡፡ ኮሎኔል ታደሰ ከወይዘሮ አዛለች ጥሩነህ እና ከአቶ ሙሉነህ ሃምሌ 16/1944 ዓ.ም በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ እንደተወለዱ ከትግል አጋሮቻቸው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትም በ67 ዓመታቸው ነው፡፡ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ የአራት ሴቶችና የሁለት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በማህደረ ስብሀት መርዓዊ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ተፈጽሟል፡፡

በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ላቀ አያሌው፣ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እና የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባላት ተገኝተዋል፡፡ የአበባ ጉንጉንም አስቀምጠዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia