TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት🔝

ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በአዲስ መልክ መልምሎ ለ300 ቀናት በብሔራዊ ደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ያሰለጠናቸውን ጀማሪ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት #አስመረቀ

አዲስ ተመርቀው ወደስራ የሚሰማሩትና ነባር የአገልግሎቱ ሰራተኞች ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ በመሆን አገራቸውን እንዲያገለግሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ መመሪያ ተሰጥተዋል።

ሰልጥነው የተመረቁት ጀማሪ ባለሙያዎቹ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ተመራቂዎቹ በአዲሱ ካሪኩለም መሰረት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የጾታ እኩልነትንና የሁሉንም ብሄሮች ተሳትፎ አማክሎ የተመለመሉ መሆናቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎች ለአንድ ጀማሪ ባለሙያ የሚያስፈልገውን የደህንነት ኪነ ሙያ፣ የአገሪቱን ህገ-መንግስት፣ የወቅቱ የደህንንት ስጋት የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት በአገር ውስጥና በውጭ ባለሙያዎች እንዲያገኙ ተደርጓል።

የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጀኔራል አደም መሀመድ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ አገልግሎቱ ከጣሊያን ወራረ ጀምሮ ሲሰራ ቢቆይም የአገርንና የህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ የገዥ ቡድኖችን ጥቅም ማስጠበቅ ላይ ተጠምዶ ቆይቷል።

መንግስት በተፈራረቀ ቁጥር እንደአዲስ የሚደራጅ በመሆኑ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ልምድ ያካበተና ሙያዊ ስራ የሚሰራ ጠንካራ ተቋም ሊሆን እንዳልቻለ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት መንግስት በለውጥና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባት አዲስ ጅማሮ ውስጥ ከሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች አንዱ አገልግሎቱን ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን ማስቻል በመሆኑ የተለያዩ የለውጥ ርምጃ እየተወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው ተመራቂዎቹ የተሰጣቸው ሃላፊነት ከፍተኛ በመሆኑ አገርንና ህዝብን ለመጠበቅ ነቅተው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ባለሙያዎቹ ስልጣን ላይ ያለውን ፓርቲ ሳይሆን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን የመጠበቅ ሃላፊነታቸውን ከፓርቲ ወገንተኝነት ነጻ በመሆን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

መንግስት የአገልግሎቱ ባለሙያዎች ከፓርቲ ወገንተኝነት ነጻ ሆነው እንዲያገለግሉ ለማስቻል ሲሰራ መቆየቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ውስጥ በርካታ ለውጡች መካሄዳቸው ይታወቃል።

የአገልግሎቱ የስራ ሃላፊዎች በተለያየ ወቅት ለአገሪቱና ለህዝቦቿ ደህንነት የሚሰሩ መሆናቸውን ከመግለጻቸው ባለፈ ተቋሙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲጎበኝ መደረጉ ይታወሳል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተቋሙ በመገኘት የስራ እንቅስቃሴውን መጎብኘቱ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia