ወንጀል ነክ መረጃ‼️
#ፍቅረኛውን አንዴ #እፈልግሻለው ብሎ ከጠራት በኃላ ወደ ስውር ቦታ በመውሰድ ባደረገችው ሂጃብ #አንቆ_የገደላት ወጣት 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

"እየጨፈርን #የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!"
.
.
"ሁላችንም ዘር አለን፡፡ ዘሩ ግን እኛ #አይደለንም! እኛ #ሰዎች ነን፡፡ ሰውነት #ከመፈጠር እንጂ #ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጲያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው፡፡ ሲዘራው ኢትዮጲያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን፡፡ መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን፡፡ ትናንት የሆነ የሰው ዲስኩር አንዳችንን ካንዳችን ካልለየሁ እያለ ሥያሜ አበጀልን፡፡ ፈጣሪን ለማረም ይመስል እኛም ሆሆሆ ብለን ተቀበልን፡፡ በሕንድ 2032 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ በቻይና 499 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ ምነው እኛ (ሰማኒያዋን) መሸከም አቃተን?ተራ በተራ መግዛታችንን ለበላይነት ተጠቀምንበት? ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም የዕውቀት ጥል እንጂ፡፡ ገና ስንወለድ ዘር ምን ይሁን ቋንቋ ምን ይሁን የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ #የዕውቀት ጥል ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም፡፡ ምክንያቱም #ይቅርታ እንጂ #በቀል ታሪክን አያርምምና፡፡ ቋንቋ የሚባልን ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡ #እየጨፈርን የናድነውን ቤት #እያለቀስን አንሠራውም፡፡ ሁልጊዜ ጥፋት ካደረስን በኀላ እንዳጠፋን ምንረዳ ከሆነ ዞሮ መልሶ አለማወቅ ይሆንብናል፡፡ በመቻቻል ሳይሆን በፍቅር እንኑር መቻቻል አንድ ቀን ያሰለቸናል፡፡ ታገስኩህ ቻልኩህን ያመጣል፡፡ ፍቅር ግን እስከዖሜጋ ይሸከማል፡፡ ከሰውነት በላይ ምን ማንነት ኖሮ፤ የሁሉም መገኛ ያው አዳም ነው ዞሮ፤ የማይሻር ሽረን አይሆኑሽ ሆነናል፤ የማይድን ስናክም የማይሞት ገለናል፡፡አትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ናት! እንወዳድ በፍቅር እንኑር፡፡"
©ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ
#ሼር #Share

ሻለቃ ኃይሌ ወደ ኃላፊነቱ #እንዲመለስ ተጠየቀ‼️
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለሁለት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመራ ቆይቶ ከወራት በፊት ከኃላፊነቱ መልቀቁን ያስታወቀው ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ወደ ኃላፊነቱ #እንዲመለስ ክልሎችና የከተማ ስፖርት አመራሮች መጠየቃቸው ታወቀ፡፡
ስፖርት ኮሚሽን ጥር 18 እና 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በአገሪቱ ስፖርታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልልና ከከተማ የስፖርት አመራሮች ጋር ባካሔደው ውይይት ወቅት የቀድሞው ባለድል አትሌት ወደ አመራርነት ቦታው ይመለስ ጥያቄ መነሳቱ ታውቋል፡፡
ስፖርት ኮሚሽኑ ያቀረበው የውይይት አጀንዳ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይም በማዘውተሪያዎች አካባቢ የሚስተዋለው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር፣ በስፖርቱ ሊኖር የሚገባው የመሪነት ሚናና ውጤታማነት ላይ ለመምከር ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በከፍተኛ ወኔና ብቃት ለመምራት ኃላፊነቱን በመውሰድ ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ ግን ‹‹በቃኝ›› ያለው የኃይሌ ገብረሥላሴ ጉዳይ ተነስቶ ነበር፡፡ ከተወሰኑ ክልሎች ዝምታ በስተቀር፣ ኃይሌ ወደ ቀድሞው ኃላፊነቱ እንዲመለስ የሚጠይቁ አስተያየቶች መስተጋባታቸውን በውይይቱ የታደሙ የክልል አመራሮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
ጥያቄውን ካነሱት ክልሎች መካከል ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ደቡብ፣ አማራና ትግራይ ሲጠቀሱ፣ በተለይም ኃይሌ ከፌዴሬሽኑ የለቀቀበት ምክንያት በግልጽ ሊነገር እንደሚገባ #ማሳሰባቸው ተነግሯል፡፡ የመድረኩ አዘጋጅ ስፖርት ኮሚሽን፣ ስለጉዳዩ ያለው ነገር ባይኖርም ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኮሚሽኑ ሙያተኞች በበኩላቸው ኮሚሽኑ ጥያቄው ተገቢ ቢሆንም ዘግይቷል የሚል እምነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የኃይሌ ገብረሥላሴ አስተያየት እንዲሰጥበት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በስፖርት አመራር ጉዳይ ላይ ለሚያነሱት ጥያቄ ውሳኔ ሊያስተላልፍ እየጠየቁ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ #ቢልልኝ_መቆያ ስለጉዳዩ እንደገለጹት ከሆነ፣ በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ፕሬዚዳንቱ በሌሉበት ተቀዳሚው ምክትል ፕሬዚዳንት ተክቶ ይሠራል በሚለው አግባብ ሥራ አስፈጻሚውና የስፖርት ኮሚሽኑ ምክር ቤት በደረሱበት የፌዴሬሽኑ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በዚህ አኳኋን እየጠመራ ይገኛል፡፡ የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) መሠረት በመድረግ የፌዴሬሽኑን ኃላፊነት ተቀብለው እየሠሩ ለሚገኙት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የዕውቅና ደብዳቤ መጻፉን ጭምር ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር

መንገዱ ተከፍቷል‼️
በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ቀን በላይ ተዘግቶ የበረው ከሐረር ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የመንገዱ መከፈትን አስመልክቶ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳለው ከባቢሌ ወረዳው ስድስት ቀበሌ ገበሬ ማህበር የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ባስነሱት የጸጥታ ችግር ምክንያት መንገዱ ከሁለት ቀን በላይ ተዘግቶ ቆይቷል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ቦንሲቱ ኢብራሂም ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት መንገዱ የተከፈተው ያለምንም ግጭት የአካባቢውን ህብረተሰብ በሰላማዊ ሁኔታ በማወያየትና የጋራ ስምምነት ላይ በመድረሱ ነው።
“ተፈናቃዮቹ ‘የአዋሳኝ ድንበር ሁኔታ መፈታት አለበት፣ በአካባቢው የዜጎች መፈናቀልና ሞት ሊቆም ይገባል እንዲሁም ተፈናቅለው በባቢሌ ከተማ የሚገኙ ዜጎች በዘላቂነት መቋቋምና ወደ ቀያቸው መመለስ አለባቸው’ በሚል ባቀረቧቸው ሐሳቦች ላይ በጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል” ብለዋል።
ከእዚህ በተጨማሪ ተፈናቃዮች የወደመባቸው ቤትንብረት እንዲተካላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ወይዘሮ ቦንስቱ አመልክተዋል።
በውይይቱ የሀገር መከላከያ፣ የዞኑ የጸጥታና የአመራር አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የህብረተሰቡ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን የተደረሰውን የጋራ ስምምነት ተከትሎም መንገዱ ከዛሬጠዋት ጀምሮ መከፈቱን ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

የእሳት አደጋ‼️
በአዲስ አበበ ከተማ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በተለምዶ በጸጋ ሆስፒታል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ በ9 የመኖሪያ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ፡፡
አደጋው ባሳለፍነው ቅዳሜ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፥ በእሳት አደጋውም በ5 ሚሊየን ብር ብ የሚገመመት ንብረት ሲወድም፣ 63 ሺህ 500 ቤት ውስጥ የተቀመጠ ብር መቃጠሉም ነው የተገለጸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ባለስልጣኑ 8 ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን ከ53 ሰራተኞች ጋር እሳቱን ለመቆጣጠር አሰማርቷል፡፡
የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች በ4 ሰዓታት ውስጥ የእሳት አደጋውን መቆጣጠራቸውን ተናግረዋል፡፡
ለዚሁ ተግባር 76 ሺህ ሊትር ውሃ የተጠቀሙት ሰራተኞቹ 15 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረትና ቤት ውስጥ የተቀመጠ 33 ሺህ ብር ከአደጋው ማትረፍ መቻላቸውን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ገልጸዋል።
በተማሳሳይ መልኩ ቅዳሜ ምሸት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ባሉ ቤቶች ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲልፍ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡
በዚሁ አደጋ 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም፥ የጴጥሮስ ቤተክርሰቲያን የምዕመናን ማረፊያ ላይም በከፊል የእሳት ደደጋው መድረሱንም ነው አቶ ስለሽ ተስፋዬ የሚናገሩት፡፡
እሳቱን ለማጥፋት በተደረገው ዘመቻም 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ የተቻለ ሲሆን፥ አሁን ላይ አየሩ ነፋሻማ በመሆኑ ህብረተሰቡ ለእሳት አደጋ ያለውን ተጋላጫነት ለመቀነስ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባም አቶ ስለሺ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ምንጭ፦ fbc

አቶ ምትኩ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️
የቀድሞው የጥረት ኮርፖሬት ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ #ምትኩ_በየነ በባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍረድ ቤት ዛሬ ቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ በቀጠሮና በዋስ መብት ላይ ለመወሰን ለዛሬ 9፡00 ቀጥሯል፡፡
ስራን በአመች ሁኔታ ባለመምራት እና በሙስና ወንጀል ተጠረጥረዉ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል የቀድሞው የጥረት ኮርፖሬት ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ምትኩ በየነ በባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍረድ ቤት ቀርበዋል፡፡
አቶ ምትኩ በየነ የጥረት ኮርፖሬት አክሲዮን ማኅበር ምክትል ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሲሰሩ ከሌሎች የአክሲዮን ባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር በ2005 ዓ.ም ‹‹ለበየዳ ሰስቴኔብል አክሲዮን ማኅበር›› 1 ሚሊየን 4 መቶ ሺህ ብር ከጥረት ኮርፖሬት ያለአግባብ ወጭ ሆኖ እንዲከፈል አድርገዋል በማለት ዐቃቤ ህግ ለችሎቱ አሥረድቷል፡፡
በተጨማሪም ጥረት በሽርክና ለመሰረታቸው ኩባንያዎች ብድር ለመስጠት የሚያስችል ህጋዊ መመሪያ በሌለበት ‹‹ባህር ዳር ሞተርስ›› እና ‹‹በየዳ ሰስቴኔብል›› ለተሰኙ አክሲዮን ማህበሮች ከሌሎች የጥረት አመራሮች ጋር በመሆን ከ4 ነጥብ ስድስት ሚሊየን ብር በላይ ብድር እንዲሰጥ አድርገዋል ፡፡ የህዝብ እና የመንግሥትን ንብረት አባክነዋል ሲል ዐቃቤ ህግ የምርመራ ውጤቱን አቅርቧል፡፡ ምርመራው ተጠናቆ እስኪያልቅ ድረስ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ አንዲሰጠውም ዐቃቤ ህግ ጠይቋል፡፡
ተጠርጣሪው አቶ ምትኩ በየነ ደግሞ የጥረት ኮርፖሬት የውስጥ መመሪያ ለእህት ኩባንያዎች ብድር መስጠት በሚፈቅደው መሰረት2 መቶ ሺህ ብር ብቻ መፍቀዳቸውን እና ፊርማቸው የተቀመጠበት የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ላይ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ውጭ የበየዳ ሰስቴነብል ጉዳይ ‹‹ከነበረኝ የሥልጣን እና የሥራ ዘርፍ አንጻር አይመለከተኝም›› ብለዋል፡፡ ‹‹ድርጊቱ ተፈጸመ የተባለው የጸረ ሙስና አዋጅ ከወጣበት 2007 ዓ.ም በፊት በመሆኑ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ጉዳዩን የመመርመር ስልጣን የለውም›› በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡
የዋስ መብታቸው እንዲከበር እና በዐቃቤ ህግ የተጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ አላስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ዐቃቤ ህግ በበኩሉ አቶ ምትኩ የጥረት ምክትል ስራ አስፈጻሚ ሆነው ያገለገሉ በመሆናቸው የወንጀል ምርመራው በቀጥታ እንደሚመለከታቸው አስረድቷል፡፡
ግለሰቡ ከነበራቸው የስልጣን ቦታ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት አንጻር በዋስ ቢለቀቁ ሰነድ ሊያሸሹ እና በምርመራ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ሲልም የዋስ መብታቸው እንዲከለከል ጠይቋል፡፡ ምርመራው በተለያዩ አካባቢዎች ስለሚካሄድ፣ ጠቃሚ ሰነዶች ገና ያልተሰበሰቡ ስለሆነ እና በጉዳዩ የሚመረመሩት ተጠርጣሪዎች ቁጥር በርከት ያሉ በመሆናቸው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱ አስፈላጊ እንደሆነ አቃቤ ህግ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር በማዳመጥ በዕለቱ የተሰየሙት ዳኞች ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ 9፡00 ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

እስቴ ወረዳ‼️
በቤተ እምነቶቹ ላይ የደረሰው #ቃጠሎ አማኞችን እንደማይወክል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ድርጊቱ ሀይማኖትን በመጠቀም ኢትዮጵያ ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ አካላት እንደሆነም ነው ምክር ቤቱ ያስታወቀው፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እሰቴ ከተማ ቀበሌ 03 ላይ ሁለት #መስጊዶች #ተቃጥለዋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰው ጥር 26/ 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ አብመድ ያነጋገራቸው የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ #ሼህ_ሙሀመድ_ሀሰን ድርጊቱ ለበርካታ ዘመናት በፍቅር የኖሩትን ህዝቦች #ለማለያየት ያለመና ሁለቱንም ወገኖች የማይወክል መሆኑን አሥረድተዋል፡፡
ትናንት ማለዳ አካባቢ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ በሚያዘጋጀው የሰርግ ሥነ ሥርዓት ላይ ከማተሚያ ቤቶች በመጣ ወረቀት እና ማስጌጫ ዳሱን የማስዋብ ሥራ እየተከናወነ እያለ ነው የድርጊቱ መነሻ የተከሰተው ብለዋል ሼህ ሙሃመድ፡፡
ከማስዋቢያው ጋር አብሮ የመጣ #የማርያም ስዕል ከሌሎች ማስዋቢያ ቁርጥራጮች ጋር ወድቆ መገኘቱን ነው የጸቡ መነሻ መሆኑን ያስረዱት፡፡ ጉዳዩ እንደተፈጸመ ስዕሉን ማን እንዳመጣው ስላልታወቀ የሁለቱም ኃይማኖቶች አማኞች በተገኙ ስዕሉ ተነስቶ ጉዳዩም አሳፋሪ እንደሆነ ተነግሮ ሁኔታው ተረጋግቶ ነበር፡፡
‹‹ከቀኑ 10፡00 አካባቢ ግን ይህን ምክንያት በማድረግ ሁለት መስጊዶች #ተቃጥለዋል፤ ሌላ ሶስተኛ መስጊድ ላይም #ድብደባ ተፈጽሟል፤ ሱቆችም ዘርፈዋል›› ነው ያሉት ሼህ ሙሃመድ፡፡
ድርጊቱ #የክርስትናም ሆኑ #የእስልምና አማኞችን የማይወክል ነው ሲሉም አውግዘውታል፡፡ ኢትዮጵያ #ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ የፖለቲካ አራማጆች የዘሩት ጥል አልሆን ሲላቸው ወደ ሀይማኖት እየተዘዋወሩ መሆናቸውን የተናገሩት የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊው ‹‹ኢትዮጵውያን የሀይማኖት ልዩነት ሳይለያየን ለብዙ ዓመታት በሰላም እና በፍቅር ኖረናል፤አሁንም እንኖራለን፤የሴረኞችን ድርጊት አውግዘን በፍቅራችን እቀጥላለን ነው ያሉት፡፡››
‹‹ሀይማኖት ሀገር መገንቢያ እንጂ ሀገር ማፍረሻ አይደለም›› ያሉት ዋና ጸኃፊው በሀይማኖቶች ገብተው ኢትዮጵያን ለመበታታን የሚጣጣሩ የፖለቲካ ቅጥረኞችን ሁሉም ዜጋ ሊያወግዛቸው እንደሚገባ ነው የጠየቁት፡፡ ድርጊቱ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችን እንደማይወክልም አረጋግጠዋል፡፡
ህዝቡን የሚያረጋጋ እና ድርጊቱን እነማን እንደፈጸሙት የሚለይ ቡድንም ወደ ስፍራው መሄዱን ነግረውናል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ድርጊቱ የፖለቲከኞች እንጂ የአማኞች አለመሆኑን ተረድቶ በተለመደው ፍቅሩ እንዲቀጥልም ሼህ ሙሀመድ ሀሰን አስገንዝበዋል፡፡
via AMMA

#update በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እሰቴ ከተማ ቀበሌ 03 ላይ ሁለት #መስጊዶች #ተቃጥለዋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰው ጥር 26/ 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ #ሼህ_ሙሀመድ_ሀሰን ለአብመድ እንደተናገሩት ድርጊቱ ለበርካታ ዘመናት በፍቅር የኖሩትን ህዝቦች #ለማለያየት ያለመና ሁለቱንም ወገኖች #የማይወክል መሆኑን አሥረድተዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሀይማኖት ሀገር #መገንቢያ እንጂ ሀገር #ማፍረሻ አይደለም›› የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ #ሼህ_ሙሀመድ_ሀሰን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉህን🔝
የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ (ጉህን) የተባለ የፖለቲካ ፓርቲ ተመሰረተ። ትላንት በቸርችል ሆቴል "የጉራጌ ህዝባዊ ትግል ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የምስረታ ጉባዔውን ያካሄደው ጉህን #ለጉራጌ ህዝብ መብት እታገላለሁ ብሏል።
Via ELU