TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከፓርላማ አባላት መከላከያን አስመልክቶ ለተነሱት ጥያቄ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• የመከላከያ ሰራዊት በሰፈር ውስጥ አንድ ሌባ ቦርሳ ይዞ ሲሮጥ ለምን ቦርሳ አላስጣልክም ብሎ መጠየቅ የለበትም፡፡

• የአገር ሉዓላዊነት ተደፍሮ መከላከያ ዝም ያለበት ጊዜ የለም፡፡ ያ ነው የመከላከያ ሰራዊት ስራ፡፡

• ችግሮች ሲገጥሙ መከላከያ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ከፍሎ ችግሮችን ማረጋጋት ችሏል፡፡

• መከለካያ በአገር ውስጥም በውጭም ሕይወቱን ገብሮ ለዚህች አገር እየሰራ ነው

• ወለጋ ውስጥ የክልሉ መንግስት ጥሪ ሲያደርግ መከላከያ ችግሩን ለመፍታት ሁለት ወር አልፈጃበትም፡፡

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከፓርላማ አባላት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን አስመልክቶ ለተነሱት ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደ ጦር ቀጠና የመጠቀም ዝንባሌ እንደሚኖር ቀድመን እናውቅ ነበር፤ ለዚያም ውይይትና ዝግጅት ተደርጎ ነበር፤ ለሁሉም ተማሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት በሚዲያ ተላልፎ ነበር

• ይህም ተደርጎ ተማሪዎችን የፖለቲካ ንግድ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚሰሩ ኃይሎች ነበሩ፡፡

• የፖለቲካ አጀንዳን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አስገብቶ ተማሪዎችን ለማጋደል የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ የሚውለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው፣ ሌላ ዓለም ላይ የትም የለም፡፡

• ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሀሳብ ልዩነት ላይ መወያየት፣ መከራከር ችግር የለውም፡፡ ተማሪዎች ድንጋና ድንጋይ አጋጭቶ እሳት ማውጣት የጋሪዮሽ ዘመን አስተሳሰብ ነው፡፡ ሀሳብና ሀሳብ እያጋጨ የተሻለ ሀሳብ የሚያመጣ ተማሪ ነው የሚፈለገው

• ድንጋይና ድንጋይ አጋጭቶ እሳት መፍጠር እንደሚቻል ለማረጋገጥ ትምህርት አያስፈልግም፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ...

"ኢትዮጵያ ውስጥ #ወንጀል ሰርቶ መንግስት ወንጀለኛ መሆኑ መንግስት ካወጀ በኋላ ያልታሰረ ግለሰብ የለም፡፡ ልዩነቱ በመንግስት ቀለብ እያቀረበለት እስር በመንግስት እስር ቤት መሆኑና እራሱን ማሰሩ ነው፡፡ በእኔ እምነት ሁሉም ታስሯል፡፡ እንደውም በመንግስት እስር ቤት የታሰሩ ግለሰቦች ቤተሰባቸው እየተጠየቃቸው ስፖርት እየሰሩ ነው ያሉት፡፡ እራሳቸውን ያሰሩ ግን ይሄንም ዕድል አላገኙም፡፡ የጊዜ ነገር እንጂ ወንጀል ሰርቶ ተሸሽጎ የሚቀር የለም፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከፓርላማ አባላት ወንጀለኞችን ለፍርድ ስለማቅረብ በተመለከተ ለተነሱት ጥያቄ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሰርቶ ያልታሰረ ሰው የለም፡፡ ልዩነቱ መንግስት ባዘጋጀው ማረሚያ ቤት መታሰርና ራሱን ማሰር ካልሆነ እንጂ፡፡

• መታሰር ማለት በአንድ በተወሰነ አከባቢ ተወስኖ መኖር ነው

• ሰውን ገድሎ፣ ሰርቆ ከሕግ ተጠያቂነት ውጪ የሚሆን የለም፡፡

• የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በማረሚያ ቤቶች ድንገተኛ ጉብኝት አድርጎ ክፍተት ያለበት እንዲስተካከል ተደርጓል፡፡

• በእስር ቤት ያሉ ያነባሉ፣ ይጽፋሉ፣ ስፖርት ይሰራሉ፣ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፡፡ በግል እስር ቤት ያሉ ያን ያክል የተመቻቸ ነገር እንዳለ አላውቅም

• ሁሉም ክልሎች ወንጀለኛ ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ነው፤ አሳልፈው የሰጡ አሉ፣ እየፈለግን ነው ያሉም አሉ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ገድሎም ሰርቆም መጠየቁ አይቀርም፣ ከሕግ በላይ የሆነ ማንም የለም፡፡

• እንደ ብሔር ቀርቶ እንደ ቤተሰብም ሌባ የለም፣ ሌቦች ሁሉም ብሔር ውስጥ አሉ፣ ሌቦች ሲሰርቁ ማንንም አያማክሩም፣ ከሰረቀ በኋላ የእንትን ብሔር ስለሆንኩ ብሎ ወደ ብሔር ይጠጋል፡፡

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ...

“በኢትዮጵያ #ሉዓላዊ የግዛት ጉዳይ #አንደራደርም፤ ይህን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ችግር ሲያጋጥም ህጋዊ መሰረት ያለው #እርምጃ እንወስዳለን። በኢትዮጵያ ሰላም፣ ዴሞክራሲና አንድነት ላይ እንቅፋት ለማድረግ የሚሞክር ሃይልን አንታገስም። ለዚህ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን አይጠበቅብንም ማንም ግለሰብ መስዋዕትነት ማድረግ ያለበት ጉዳይ ነው የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተኑ ጉዳዮችን በጋራ መታገል ይኖርብናል።”

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ #ነብያት_ጌታቸው በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 እስከ የካቲት 4 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በቻይና እስር ቤት ትገኛለች‼️

• ጓደኛዋ አድርሽልኝ ያለቻት ሻምፑ #አደንዛዥ_ዕፅ ሆኖ ተገኝቷል!

via Addis Admas
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ASTU🔝

"የተማሪዎች ጥያቄ እና #አስደንጋጩ ውሳኔ!"

via ፍትህ መፅሄት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ማንም ኢትዮጵያዊ በገዛ ሀገሩ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዳይችል ማድረግ #ኋላ_ቀርነት ነው፡፡" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia