TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከትራንስፓርት ሚንስቴርና ከሌሎች ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው የሉኡካን ቡድን የጅቡቲ ወደብን ጎበኘ። በጉብኝቱ ወቅት ስለወደቡ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በጂቡቲ ወደብ ላይ የሚያጋጥመውን መጨናነቅ ለመቅረፍ በተለይም የነዳጅ፣ ማዳበሪያና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች በፍጥነት ማመላለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክሯል። የትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የሉኡካን ቡድኑ ወደ ጅቡቲ መምጣት የአገራቱን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ በቅንጅት ለመስራት የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለቴፒ‼️

ለፌደራሉ መንግስት
ለደቡብ ክልል መንግስት
ለሀገር መከላከያ
ለፌደራል ፖሊስ
.
.
የክልሉ መንግስት እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት በቴፒ ያለውን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ለTIKVAH-ETH አሁን የተላኩ መልዕክቶች ያስረዳሉ። ሁኔታዎችን አሁን ካሉበት ወደሌላ ደረጃ ሳይሸጋገሩ መንግስት #መፍትሄ_ሊያበጅ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ እንዲሁም ምሥራቅ ጉጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች መካከል በታካሄደ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በርካቶች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተናግረዋል። የተኩስ ልውውጡ የተፈፀመው በምዕራብ ጉጂ በምትገኘዉ ዱግዳ ዳዋ ወረዳ እንዲሁም በምሥራቅ ጉጊ ሰባ ቦሩ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል። አቶ ጂራታ የተባሉ የዱግዳ ዳዋ ወረዳ ነዋሪ ተከሰተውን ሁኔታ ለVOA አስረድተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንታርቲካ በረዶ መቅለጥ ስጋት እየሆነ ነው‼️

በቅርቡ በአንታርቲካ  ጥናት ያካሄደው የአሜሪካ ብሄራዊ አካዳሚ ሳይንስ ተቋም  እ.አ.አ ከ1979 ጀምሮ ለአለፉት 40 አመታት በአካባቢው የበረዶ መቅለጥ በየ አመቱ በ6 እጥፍ እየጨመረ  መምጣቱን ገልጿል፡፡

ተቋሙ የአለማችን የሙቀት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣትን በምክንያትነት ጠቅሶ ከ1979-2017 ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ የባህር ጠለል በ 1.4 ሴንቲ ሜትር ከፍ እያለ መምጣቱን በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ተመራማሪዎቹ በቅርቡ በ 18 የአንታረቲካ ቦታዎች በመርከብ በመዘዋዎር ባካሄዱት ጥናት በአካባቢው በየጊዜው የበረዶ መቅለጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን አረጋግጠዋል፡፡

የአንታርቲካ የበረዶ መቅለጥ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በቀጣይ ጥቂት አመታት  ውስጥ የባህር ጠለል መጠን በከፍኛ መጠን እንደሚጨምርና በአለም ላይ ለሚኖሩ የሰው ልጆችም ዋነኛው የአደጋ ምንጭ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ጨምረው አስቀምጠዋል፡፡

በዚህ መሰረት ተመራማሪዎች ከ1979-1990 ድረስ የአንታርቲካ የበረዶ ግግር በየአመቱ በአማካኝ 40 ቢሊዮን ቶን እንደሚቀንስም አረጋግጧዋል፡፡

ከ2009 ወዲህ ለአለፉት አመታት ከነበረው  6 እጥፍ በላይ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱም ተረጋግጧል።

ሌላው በዘርፉ ጥናት የአካሄደው የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ተቋም በበኩሉ የሳተላይት አሰሳዎችንና የአውሮፕላን ቅኝቶችን በማድረግ የተለያዩ ፎቶ-ግራፎችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ የሁኔታውን አሳሳቢነት በመጠቆም፤  በቀጣይም  የአለምን የአየር ንብረትን በማስተካከልና  የበረዶ መቅለጥን በመቀነስ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁሟል፡፡

ከዚህ ቀደም በመስኩ የተካሄዱ ጥናቶች ወደ ፊት እ.አ.አ በ 2100 በባህር ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ ከተሞች ቅድመ ጥንቃቄ ካልተድገላቸው  በጎርፍ እንደሚጠቁና ብዙ ነዋሪዎችንም ከመኖሪያ ቀያቸው ሊያፈናቅል እንደሚችል ሰጋታቸውን ማስቀመጣቸው ይታወሳል፡፡   

ምንጭ፡ አልጄዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሳውዲ አረቢያ የፀረ-ሙስና ዘመቻዋን እንዳጠናቀቀች አስታወቀች። ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረ-ሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ በፀረ-ሙስና ዘመቻው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር አሊ-አላሙዲንን ጨምሮ በመቶዎች ሚቆጠሩ የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባላት እና ቢሊየነር ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል። የባህር ሰላጤዋ ንጉሣዊ ግዛት አስተዳዳሪዎች እንደሚሉት በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት 87 ግለሰቦች የቀረበባቸውን ክስ በማመናቸው ከመግባባት ላይ ተደርሷል። 8ቱ የቀረበባቸውን ክስ ስላላመኑ ጉዳያቸው ለአቃቤ ሕግ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን የ56 ሰዎች ጉዳይ ደግሞ ውሳኔ ያላገኘ የወንጀል ክስ ስላለባቸው ጉዳያቸው አልተጠናቀቀም ተብሏል። የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከቀናት በፊት ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። ሳዑዲ ወደ 200 የሚጠጉ ልዑላንን፣ ሚንስትሮችን እና የንግድ ኃላፊዎችን ሪያድ በሚገኘው ባለ 5 ኮከቡ 'ዘ ሪትዝ ካርልተን' ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ሥር አቆይታ ነበር። የፀረ-ሙስና ዘመቻው የተጀመረው ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው እየጨመረ በመጣው በልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ነው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የፀደቀውን #የስደተኞች_አዋጅ በመቃወም ነገ በጋምቤላ ከተማ ሊደረግ ለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ #ከልክሏል

via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ6 ሺህ ነጋዴዎች ግብር ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ግብር ስረዛው ከ2003 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከፍተኛ የግብር ተመን ተጥሎባቸው አቤቱታ ሲያቀርቡ የቆዩትን ነጋዴዎች ያካትታል፡፡ ሰረዛው የተደረገው የከተማው ገቢዎች ባለስልጣን የታክስ ንቃናቄ መድረክ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው፡፡ ሌሎች ውሳኔ የተላለፈባቸው እና ገና በሂደት ላይ የሚገኙ 1 ሺህ 780 ነጋዴዎች ደሞ ዕዳ እንዲሰረዝላቸው እና ክሳቸው እንዲቋረጥ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጋር ምክክር ተጀምሯል።

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ትናንት ከሪል ስቴት አልሚዎች በመከሩበት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ የሪልስቴት ዘርፉ የከተማውን የቤት ችግር ለመቅረፍ እንደ አጋዥ ፕሮጀክት የሚጠቅም መሆኑን ገልጸው፤ የከተማ አስተዳደሩ ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል እስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድም አሳስበዋል፡፡

Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ‼️

አራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ ሊጀመር መሆኑን የማዕከላዊ እስታስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ።

ቆጠራው የሚጀመረው ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 20 ሲሆን ቤት ለቤት በመሄድ እንደሚደረግ ተገልጿል።

የማዕከላዊ አስታስቲክስ ዋና ዳሬክተር አቶ #ቢራቱ_ይገዙ እንደለጹት፣ ለቆጠራው የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል።

የአሁኑን ቆጠራ ከሌሎች ጊዜያቶች ቆጠራ የሚለየው የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ቆጠራው ሲካሄድ በአርብቶ አደር አካባቢና በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ከተያዘው የመደበኛ ጊዜ ዘግይቶ የሚደረግ ሲሆን በአሁኑ ግን በተመሳሳይ ጊዜ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ነው የተገለጸው።

በተጨማሪም ባለፉት የቆጠራ ጊዜያቶች አንድ ቋንቋ ብቻ በመጠቀም ቆጠረው ይካሄድ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ገድሞ አምስት የክልል ቋንቋዎቸን በመጠቀም ቆጠራው እንደሚካሄድም ተጠቁሟል።

ለዚህም ስራ በሁሉም ክልሎች 1መቶ 82ሺህ በላይ ለሆኑ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳ ዛኝ ዜና‼️

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

የጃማ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ አደጋ መርማሪ እንደገለጹት ሲኖትራክ ተሽከርካሪው በቶ ከተባለ ስፍራ በጫነው አሽዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደጎሎ ከተማ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር አደጋው ያጋጠመው።

ተሽከርካሪው በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ 14 ቀበሌ ልዩ ቦታው ዝግባ ከሚባል ስፍራ ሲድርስ እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በግምት 60 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ በመግባቱ አደጋውም መከሰቱንም አስረድተዋል።

በአደጋው የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ11 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ዋና ሳጅን ተስፋው ነጋ አስታውቀዋል።

ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በጃማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 13 ሰዎች ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር መላካቸውን ዋና ሳጅን ገልጸዋል፡፡

ዋና ሳጅን ተስፋው አሸዋና ድንጋይ ላይ ሰዎችን መጫን እየተለመደ እየመጣ በመሆኑ በቀጣይ ባለሀብቶችና ሹፌሮች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸውን ከጃማ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert ቴፒ‼️

በቴፒ ከተማ ከትንላንት ጀምሮ ዳግም #ያገረሸው #አለመረጋጋት ዛሬም ቀጥሏል። ዛሬም በተለያዩ የከተማይቱ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የጥይት ድምፅ እየተሰማ እንደሚገኝ በከተማው የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። ነዋሪዎች በከተማው ያለው ውጥረት ወደ ሌላ ደረጃ ሳይሸጋገር የኢትዮጵያ መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል። ከትላንት ጀምሮ በተፈጠረው አለመረጋጋት ሳቢያ ስለደረሰው ጉዳት የተረጋገጡ መረጃዎችን ሳገኝ ወደእናተ አደርሳለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራንስፖርት ታሪፍ  ጭማሪ አልተደረገም‼️

ዛሬ በስራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ ምንም አይነት #የትራንስፖርት_ታሪፍ  ጭማሪ #እንደማይኖር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ።

የአዲስ አበባም ሆነ የክልሎች የትራንስፖርት ታሪፍ ባለበት እንደሚቀጥልም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የፖሊሲ ጥናትና የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ መብራቱ እንደገለፁት፥ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ተከትሎ ምንም አይነት የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም።

በህዳር ወር የነዳጅ ማስተካከያ በተደረገበት ወቅት የአገር አቋራጭ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ስለተደረገና የአዲስ አበባውም የዛሬ አመት አካባቢ መሰረታዊ ማስተካከያ ያደረገ ስለሆነ የሚኖር ማስተካከያ አለመኖሩን ነው ያስታወቁት።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት ይህንን አውቀው ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደሌለባቸው ባለስልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ህብተረተሰቡ በቀድሞው ታሪፍ መሰረት የአገልግሎት ክፍያውን እንዲፈፅም አሳውቀዋል።

የንግድ ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert ቴፒ‼️በቴፒ ከተማ በትናንትናው ዕለት ያገረሸው #ግጭት ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ🗓ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ በነገው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የምክር ቤት አባላት ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች #ማብራሪያ ይሰጣሉ።

Via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia