TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም ለገሱ‼️

#በምሥራቅ_ወለጋ_ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም መለገሳቸውን የነቀምቴ ደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ።

ባለፉት ስድስት ወራት ደሙን የለገሱት በስምንት ወረዳዎችና በነቀምቴ ከተማ  የሚገኙ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

የደም ባንክ አገልገሎቱ ኃላፊ አቶ #ዴሬሣ_ባየታ እንደገለፁት ከበጎድቃደኛ ተማሪዎች የተሰበሰበው ደም በምስራቅ፣ ሆሮጉድሩና ቄለም ወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ሆስፒታሎች ተከፋፍሏል።

በግማሽ በጀት ዓመቱ ከትምህርት ቤቶች 4ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ቢታቀድም በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ዕቅዱን ሙሉ ለሙሉ ለማከናወን አለመቻሉን ተናግረዋል።

የነቀምቴ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ሊሊ ተመስጌን በሰጠችው አስተያየት በደም እጥረት ሕይወታቸው የሚያላፍ ወላድ እናቶችን ለመታደግ ባላት ፍላጎት በሁለት ዙር ደም ለግሳለች።

ተማሪ ኢዮብ አሰፋ በበኩሉ ደም መለገስ ከሰብአዊ ድጋፎች ትልቁ መሆኑን በመግለፅ ወደ ፊትም የደም ባንኩ ቋሚ አባል በመሆን ልገሳውን አጠናክሮ የማስቀጠል ዓላማ እንዳለው ተናግሯል ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia