TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹በማረፊያ ቤት ቆይታችን #ሰብዓ_መብታችንን እና #ክብራችንን የሚነካ ድርጊት #ተፈጽሞብናል›› አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ



አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ ‹‹በማረፊያ ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚነካ ድርጊት ተፈጽሞብናል›› ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ቅሬታ አቀረቡ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሰብአዊ መብት አያያዛቸው እንዲከበርም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ እንደማይወስዱም ነው ተጠርጣሪዎቹ የገለጹት፡፡ በባሕር ዳር ቤት እና ዘመድ ስለሌለን ቤተሰቦቻችን ከአዲስ አበባ ተመላልሰው ምግብ ለማብሰልም ሆነ ለማገዘ አይመቻቸውም ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪ በማረፊያ ጣቢያው ዙሪያ #የተሰበሰቡ ወጣቶች ‹‹ወንጀለኛ፣ ሌባ እና ነብሰ ገዳይ በማለት #ክብራችንን እና ህገ መንግስታዊ መብታችንን የሚነካ ድርጊት ፈጽመውብናል:: በከተማዋ ያለው ድባብ ለደህንነታችን እና ጉዳያችንን በደንብ ተከታትሎ ለመከራከር እክል ይፈጥራል፤ ስለሆነም የክርክሩ ጉዳይ አዲስ አበባ ይታይልን›› ሲሉ ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡ ችሎቱም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ የተጠርጣሪዎቹን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ጉዳያቸውን በባሕር ዳር ሆነው እንዲከራከሩ ወስኗል፡፡

‹‹የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና አመራሮች ወንጀለኛነታችን ሳይረጋገጥ ጉዳዩን በማራገብ የደቦ ፍርድ እንዲደርስብን አድርገዋል›› ብለዋል፡፡ ለአብነትም አቶ በረከት በደብረ ማርቆስ ከተማ በወጣቱ የደረሰውን ሁከት እና ግርግር አንስተዋል፡፡

ጉዳዩን ያየው የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስፈላጊው ጥበቃ እና ክትትል ለተጠርጣሪዎቹ እየተደረገላቸው #በባሕር_ዳር_ማረፊ_ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በመወሰን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia