TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

“አባ ቶርቤ” በሚል መጠሪያ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድብቅ በመንቀሳቀስ ሰዎችን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በዛሬው እለት ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ “አባ ቶርቤ” (ባለሳምንት) በሚል መጠሪያ በመደራጀት ሰላማዊ ዜጎችን፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና የፀጥታ ሀይሎችን #ሲገድሉ እና #ሲያስገድሉ ነበር በሚል ነው ተጠርረው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የተጠርጣሪዎቹን ማንነትና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰው ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኸርባል ኮልጌት የተባለ ተመሳስሎ የተሰራ መድሃኒት በህገወጥ መንገድ አምርቶ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ አንድ የኮስሞቲክስ ማምረቻ ባለቤት #በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ክትትል ሲያደርግና ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፌዴራል የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት፣ ከኢንተር ፖል እና ከአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በወሰደው እርምጃ መሆኑን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን አብርሃም ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሶማሌ ላንድ ተነስተው በቶጎጫሌ ወደ ጅግጅጋ ሲያመሩ የነበሩ ኮድ-04046፣ ኮድ-05759 ሁለት ቅጥቅጥ አይሱዙዎች እና ኮድ-39416 የጭነት ተሸከርካሪ ግምታዊ ዋጋቸዉ 550ሺ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፤ ምግብ ነክ፣ ጨርቃ ጨርቅ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነዉ በህገወጥ መንገድ ወደ ጅግጅጋ ለመግባት ሲሞክሩ በፌደራልና በክልል ፖሊሶች እንዲሁም በጉምሩክ ሰራተኞች ክትትል ታህሳስ 23/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 እስከ ምሽት 2 ሰዓት ባለዉ ጊዜ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ #ደመላሽ_ተሾመ አያይዘዉ እንደገለጹትም በድርጊቱ ተሳታፊ የነበረዉ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ዉሎ አስፈላጊዉ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዉ በቀጣይም ህብረተሰቡ ይሄን መሰል ድርጊቶች በንቃት በመከታተል ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Via~EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጋቦን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ #መክሸፉን ተከትሎ በርካታ ባለስልጣናት #በቁጥጥር ስር ዋሉ። የምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ጋቦን ወታደሮች በዛሬዉ ዕለት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን መቆጣጠራቸዉን ገልፀዉ ነበር። ወታደሮቹ ለጥቂት ሰዓታት ተቆጣጥረዉት በነበረዉ የሀገሪቱ የሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ እንደተናገሩት፣ መፈንቅለ መንSስቱን ያደረጉት ከጎርጎሮሳዉያኑ 2009 ዓ/ም ወዲህ በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ አምባገን አገዛዝ ለማብቃት እና በምትኩ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ነበር። ይሁን እንጅ፣ ይኸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን የሀገሪቱ የጋቦ መንግስት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ገልጿል። ይህን ተከትሎም የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ እና ሌሎችአራት የጦር መኮንኖች በመዲናዋ ሊብረቪል በሚገኘው የሀገሪቱ ብሄራዊ የሬዲዮ ጣቢያ አጠገብ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ገልፀዋል። የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መህመትና የፈረንሳይ መንግስትn የመፈንቅለ መንግስቱን ሙከራ አዉግዘዉታል። የጋቦ ፕሬዚደንት ቦንጎ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በሞሮኮ ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን እንደደረሰበትና ከፈፃሚዎቹ ጥቂቶቹን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው እንደገለጹት፥ በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተደርሶበታል።

በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ ከተሳተፉት ውስጥም ጥቂቶቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸወን አስታውቀዋል።

የወንጀሉ ፈፃሚዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በተለያየ መንገድ በእጃቸው እንደሚያስገቡ የጠቆሙት ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው፥ የወንጀሉ ተሳታፊዎችን በማጋለጥ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ዩንፎርም ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው የጎረቤት አገራትም የደንብ ልብሱ ለወንጀል መፈፀሚያነት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ እየሰሩ ያሉ ጥቂት ግለሰቦችም በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

ፖሊስ በተያዘው ወር ለሚካሔዱት የጥምቀት በዓልና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል።
ለዚህም ስኬት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩንና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያሳይ በማለት ኮሚሽነሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia