ወንጀል ነክ መረጃ‼️
በዱቄት መልክ #አደገኛ_ዕጾችን ሲያዘዋዉር የተያዘው ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ። ለሰው ልጅ ጤና ጉዳት የሚያደርሱ የተከለከሉ አደገኛ ዕጾችን ማዘዋወር ወንጀል የተከሰሰው የውጭ ዜጋ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ሚስተር ዳኒ ቺካ ኑዋዱኬ የወንጀል ህግ አንቀጽ 525 /1/ለ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወር፣ በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደውን የኮኬይን እጽ ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከብራዚል ሳኦወፖሎ ወደ በመነሳት ወደ ቦሌ አየር መንገደ ለትራዚተ ባረፈበት ወቅት በተደረገው ፍተሻ በያዘው የጉዞ ሻንጣ ውስጥ በዱቄት መልክ የተዘጋጀውን 5.2 ኪሎ ግራም እና በሆዱ ውስጥ ደግሞ 87 ጥቅል ፍሬ የሆነውን ኮኬይን የተባለውን እጽ ድብቆ በመያዝ ወደ ኢንጉ ከተማ ሊሄድ ሲል የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው መርዛማ እና አደገኛ ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ተከሳሹ ማንነቱ ተረጋግጦ ክሱ ደርሶትና በችሎት ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ የክስ መቃወሚያ የለኝም ባለቤቴ መንታ ልጁ ስለወለደች በቸግር ምክንያት ድርጊቱን ፈፀሜለሁ ጥፋተኛ ነኝ በማለት ተናግራል፡፡ዐቃቤ ሕግን ተከሳሽ ድርጊቱን ባመነው መሰረት ሌላ ማስረጃ ማሰማት ሳያስፈል ጥፋተኛ ይባል ብሏል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ በተከሰሰበት አንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ በመላት የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና በገንዘብ ችግር ምክንያት መሆኑን በማቅለያነት በመቀበል በ8 አመት ጽኑ እስራትና በ8000 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia