TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የኢትዮጵያን ባህል፣ ቅርስና ታሪክ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዲፕሎማቶች ለማስተዋወቅ ያለመ የኢትዮጵያ የባህል ዲፕሎማሲ ቀን ተከብሮ ውሏል። የባህል ዲፕሎማሲ ቀኑ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነን ጨምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ አፍሪካ ሀገሮች አምባሳደሮች ተገኝተዋል። የባህል ዲፕሎማሲ ቀንን በማስመልከትም የእንጦጦ ቤተ መንግስትና ሙዚየም፣ የአዲስ አበባ ቱሪስት መዳረሻ ፓርክ እና ያያ ቪሌጅ ጉብኝት ተደርገዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጥበባትና ባህላዊ እሴቶች፣ ባህላዊ ሙዚቃዎችና ባህላዊ ምግቦች እንዲሁም የተለያዩ ቅርሶች ለበዓሉ ታዳሚዎች ቀርበዋል።

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopiq
ከባህር ዳር...

"ሰላም ጸግሽ እንዴት ነህ? የዛሬው የባህርዳር እና የደደቢት ጨዋታ ፍጹም ሰላማዊ እና ወንድማማችነት የተንጸባረቀበት ነበር!! የባህርዳር ደጋፊም ለ ደደቢት ክብር ሰጥቶ ሲያጨበጭብ ነበር!! አንድ የደደቢት ተጫዋችም፡ሜዳውን እየዞረ ህዝቡን ፍቅር ሲያሳይ ነበር!! እናም በጣም ደሥ ብሎናል!!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊ሰላም🕊

ሚዲያዎች ለሀገሪቱ #ሰላም የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒሰቴር ዴኤታዋ ወ/ሮ #አልማዝ_መኮንን ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ምሁራን ትውልድን በእውቀት በማነፅ ሰላምን ይገነባሉ" በሚል መሪ ቃል በምሁራን በቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ተናግረዋል፡፡

ሰላም ከማህበረሰብ ጋር በመሆን የሚጠበቅ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስቴር ዴኤታዋ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ የህብረተሰቡ አንድ አካል መሆናቸውን ጠቅሰው የሰላም ሚኒስተር ደግሞ ይሄን በማሰብ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡

በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ በዋናነት ሰላም በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ሁለንተናዊ ገፅታ በተለያዩ ምልከታዎች አብራርተውታል፡፡ በፅሁፉ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ ምሁራንና ተማሪዎች ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱም ሰላምን ማስፈን የሁሉም ዜጋ ድርሻ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በአንድ ዳቦ መጋገሪያ ቤት ላይ በተፈጠረ #ፍንዳታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ገደማ በተፈጠረው ፍንዳታ ከ50 በላይ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን 12ቱ የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሑበርት የተባለው የዳቦ መጋገሪያ ፍንዳታው በተከሰተበት ቅፅበት ክፍት እንዳልነበር የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል። ፍንዳው በተከሰተበት ወቅት ጋዝ ከዳቦ መጋገሪያው እየወጣ ነው የሚል ጥቆማ የደረሳቸው የእሳት አደጋ ሰራተኞች መፍትሔ ለመፈለግ ወደ ቦታው በመጓዝ ላይ ነበሩ። አደጋው ሲከሰት ቢጫ ለባሾቹ ተቃዋሚዎች መንግሥትን ለመተቸት አደባባይ ወጥተው ነበር።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ለ2 ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጁልየስ ማዳባዮ ጋር በፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሚመራው ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ የጉብኝት ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በሴራሊዮን መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

ምንጭ፡- ም/ጠ /ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞው የጤና ሚኒስትር ዶክተር #ከሰተብርሃን ‘የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ’ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ። ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ የአፍሪካ ባለራዕይ መሪዎች አጋር በማድረግ በአህጉሩ ልማት፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት፣ የሰለጠነ ሰው ልማት፣ ትምህርት ለምርታማነት እንዲውል እና በወጣቶች የስራ ዕድል ዙሪያ የሚሰራ ተቋም ነው።

via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ዛሬ ጥር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አካባቢዎች በትናንትናው እለት ተከስተው የነበሩት ግጭቶች መረጋጋት አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን በምዕራብ ጎንድር ዞን መተማ ወረዳ ከገንዳውኃ ከተማ በስተ ደቡብ ምስራቅ በኩል በምትገኘዋ ሽንፋ ቀበሌ አሁንም ግጭቱ #አልበረደም፡፡ ከሁለቱም የታጠቁ ሀይሎች (ከቅማንትና አማራ) ወደ ቦታው እየተንቀሳቀሱ ተጨማሪ ግጭት የፈጠሩ ነው፡፡ በዚህ ግጭት ሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ከኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ወደስፍራው በመንቀሳቀስ ግጭቱን ለማብረድ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

Via Asemahagn Aseres
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ #አይታገስም፡፡" ኢ/ር ታከለ ኡማ
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ የህንፃ ተቋራጭ ባለቤቶች እና አማካሪዎች የስራ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለብክነት የተጋለጠ እንደነበርም አንስተዋል፡፡

በግንባታ ላይ ያሉ ነባር ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ውስጥ የማይጠናቀቁ ከሆነ ውላቸው እንደሚቋረጥ ያሳወቁት ኢ/ር ታከለ ኡማ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ የተሰጧቸውን ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ያልቻሉ እና የህዝብን ሃብት ለከፍተኛ ብክነት እየዳረጉ ያሉ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች በቀጣይነት የከተማ አስተዳደሩ በሚያሰራየው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ አንስተዋል፡፡

እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ እንደማይታገስም አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡት ግንባታዎች በአስቸኳይ ኦዲት ተደርገው ለከተማ አስተዳደሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ፕሮጀክቶችን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ አጠናቅቀው እንዲያስረክቡ አሳስበዋል፡፡

via Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ብሄር ተወላጆች ውይይት አደረጉ፦

"የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችንን በማዘመን ሚዲያ ለህዝቦች ትስስርና ለሀገር ግንባታ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ከማድረግ ባሻገር በህዝቦች ዘንድ ግጭት የሚቀሰቅሱ መረጃዎችን #ባለማሰራጨት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት።"
.
.
"የወላይታ ብሔር ተወላጆች #ከሌሎች ህዝቦች ጋር ቀድሞ የነበረውን ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት እና የመቻቻል እሴታቸውን በማጠናከር ለሰላምና ለሀገር #ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከት አለባቸው፡፡"
.
.
"በወላይታ እና #በሲዳማ ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን የሰላም፣ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶችን ለማስቀጠል ተከታታይ ያለው ህዝብን የማወያየት ሥራ ይሰራል።"
.
.
"የወላይታ እና #የሲዳማ ህዝቦች ትስስር በጊዜያዊ ግጭቶች #የሚሸረሸር ሳይሆን ትናንትም የነበረ #ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ ስለሆነም ሰላም በዋጋ የማይተመን ትልቅ ሀብት ስለሆነ እጅ ለእጅ ተያይዘን ድህነትን ለማሸነፍ ልንሠራ ይገባል ብለዋል፡፡"
.
.
"የወላይታ እና ሲዳማ ህዝቦች የግጭት ታሪክ የሌላቸው ከመሆናቸውም ባሻገር በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ ህዝቦች ናቸው፡፡"
.
.
"ሰላም ለአንድ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ የወላይታ ብሔር ተወላጆች በሚኖሩበት አከባቢ ለሀገር ሰላም የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።"

ሀዋሳ ጥር 04/05/2011

https://telegra.ph/የወላይታ-ብሔር-ተወላጆች-01-12
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️

ፖሊስ ይህን ድርጊት በመፈፀሙ እጅግ በጣም እንዳዘኑ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገልፀዋል። በሀገሪቱ ውስጥ የለውጥ ንፋስ እየነፈሰ ባለበት ሰዓት በተማሪዎች ላይ ይህ መፈፀሙ ተገቢ አይደለም፤ ሊታረምም ይገባዋል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሆሳዕና ከተማ ፖሊስ‼️

"በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ በሞተር ላይ ሆኖ የሰውን ቦርሳ እና ሞባይል መቀማት በጣም ተበራክቶዋል። ስለዚም ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ እና ፖሊስም ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየምን ዛሬ  አስመረቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅርሶችን ጠብቃና ተንከባክባ እዚህ አድርሳለች ብለዋል። አሁን ያለው ትውልድ ተንከባክቦ የመጠበቅና ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለበት ሲሉም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስና ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን ዳሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ በበኩላቸው፥ ሙዝየሙን ለማዘመንና ወደ ዲጅታል ላይብረሪ ለማሳደግ በቀጣይ እንደሚሰራ ገልፀዋል። በሐመረ ኖኅ ሙዚየም ውስጥ የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የታሪክ ጉዞና የገዳማት ታሪክ በከፊል የሚያሳዩ እንዲሁም በርካታ ንዋየ ቅድሳት፣ መጽሀፍት፣ አልባሳትና የተለያዩ ረጅም እድሜን ያስቆጠሩ መገልገያ ቁሳቁሶች ይገኛሉ።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የተሰጠ መግለጫ፦

ሰላም ለሁሉም ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎት እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ለዜጎችም ይሁን ለሀገር ልማታዊ እድገት ጉልህ አስተዋፆኦ ያለውን ሰላም የፀጥታ ሀይሉ ጥረት ብቻውን እውን ሊያደርገው እንደማይችል ይታመናል።

እንደ #ሀዋሳ ተጨባጭ ሁኔታም ከተማዋን የፈጣን እድገት ተምሳሌት አድርጎ ቀጣይነቷን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሁሉም የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅበት አያጠያይቅም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ጥቂት ሁከትን ለግል ፍላጎታቸው ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙ ግለሰቦች እና #የተደራጁ_ሀይሎች በተለያዩ ጊዜያት የከተማዋን ሰላም ከማደፍረስ ባሻገር በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲደርስም ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል።

ከእነዚህ የፀረ ሰላም ሀይሎች #እኩይ ተግባራትም መካከል በትናንትናው እለት በከተማዋ በኢትዮጵያ ትቅደም ትምህርት ቤት የተደራጁ ወጣቶች የግቢውን አጥር በመስበር ሁከት ለመፍጠር ያደረጉትን ጥረት የፖሊስ ሀይሉ እና ህብረተሰቡ ባደረገው ርብርብ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

የእኚህ ፀረ ሰላም ሀይሎች አላማ ከውጭ ተደራጅቶ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ በመግባት ሁከቱን ተማሪዎች የፈፀሙት በማስመሰል የግጭቱን ቅርፅና ይዘት ሌላ መልክ እንዲኖረው በማስመሰል የግል ፍላጎታቸውን ማሳካት እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

ሆኖም የአካባቢው ህብረተሰብ ለፖሊስ ባደረሰው #ጥቆማ እና በስፍራው ከነበረው የፀጥታ ሀይል ሌላ ተጨማሪ ሀይል #በማጠናከር ሁከቱን ሊያባብሱ የሚችሉ የጦር መሳሪያዎችን ሳይቀር ፖሊስ በቁጥጥሪ ስር ሊያውል ችሏል። በዚህ የተቀናጀ የፖሊስ እና የህብረተሰቡ ጥረትም ቱርክ ሰራሽ 12 ሽጉጦች በሁለት ግለሰቦች እጅ መያዝ ተችሏል።

በተመሳሳይም ፖሊስ በሁከቱ ግንባር ቀደም በመሆን ሲመሩ ነበሩ ያላቸውን 36 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢው ምርመራም እያደረገ ይገኛል።

ሁከቱን ለመቆጣጠር ፖሊስ ባደረገው ጥረት ምንም አይነት የሰውም ሆነ የንብረት ውድመት ሳይደርስ ማቆም ቢችልም በጊዜው በድርጊቱ ፈፃሚዎች ይወረወሩ የነበሩ ድንጋዮች በተወሰኑት የፀጥታ ሀይሎች ላይ እና በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ግን ሊደርስ ችሏል።

በዚህ አጋጣሚ የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ የፀጥታ ሀይሉ እና የአካባቢው ህብረተሰብ ሁከቱን ለመቆጣጠር ላደረገው ርብርብ ምስጋናውን ማቅረብ ይወዳል።

ፖሊስ ይህን የፀጥታ ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ለከተማዋ ሰላም እና ለዜጎች ደህንነት መረጋገጥ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እየገለፀ ሰላማዊት ሀዋሳን በጋራ እንገባ የሚል መልእክቱን በማቅረብ ነው።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia