TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአሜሪካ ኤምባሲ⬇️

ረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ‹‹በአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ ሕዝባዊ ሠልፍ እንደሚኖር ተገምቷል፤›› ብሎ የኤምባሲው ሠራተኞች ከቤታቸው እንዳይወጡ፣ በተጠቀሰው ቀንም ኤምባሲው ሥራ እንደማይኖረው ገልጾ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው ማሳሰቢያ በርካቶችን ግር አሰኝቷል፡፡ ኤምባሲው ከአስተማማኝ መረጃ አረጋግጫለሁ ያለለት ሠልፍም #አልተካሄደም፡፡

ኤምባሲው በድረ ገጹ ሁሉም የቪዛ አገልግቶችና የአሜሪካ ዜጎች አገልግሎት ቀጠሮዎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸውንና አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች በድረ ገጹ አማካይነት ሌላ ቀጠሮ እንዲይዙ ገልጿል፡፡ የኢሚግሬሽን ቪዛ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሌላ ቀጠሮ ተዘጋጅቶ እንደሚጠሩና ከዚህ ውጪ ያሉ የቪዛ አገልግሎት የሚጠይቁ ሰዎች በኤምባሲው ድረ ገጽ ቀጠሮ እንዲያሲዙ አሳስቦ ነበር፡፡

ኤምባሲው ይህን ካለ በኋላ በሠልፉ የሚሳተፉ ዜጎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ መልዕክታቸውን እንዲገልጹ እንደሚያበረታታም አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣውን መግለጫ ያየው የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ ‹‹የአሜሪካ ኤምባሲና የኢንተርናሽናል ኮሙዩኒቲ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን የእግሊዝ ኤምባሲ ሌላ ማሳሰቢያ እስካልወጣ ድረስ መደበኛ ሥራውን ያከናውናል፤›› ሲል በትዊተር ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡ የኤምባሲው መረጃ የደረሳቸው ዓለም አቀፍ ተቋማትም ሠራተኞቻቸው ሥራ እንዳይገቡ ያደረጉ ሲሆን፣ ሌሎች ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያላቸው የአገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞችም በተመሳሳይ ሥራ እንዳልገቡ ሪፖርተር ማረጋገጥ ችሏል፡፡

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ኒክ ባርኔት ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ፣ በተጠቀሰው ቀን ሠልፍ እንደሚኖር አስተማማኝ መረጃ እንደደረሳቸውና በዚህ መረጃ መሠረት ኤምባሲው እንደወሰነ ገልጸው፣ ይኼንን ዓይነት ውሳኔ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ኤምባሲው #በሕግ ስለሚገደድ በይፋ እንዳጋራው ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ሰዎች ኤምባሲው #ድብቅ አጀንዳ እንዳለው አድርገው እንደተመለከቷቸውና ይህ ማሳሰቢያ የዜጎችን ደኅንነት ከማስጠበቅ የዘለለ ሌላ ሚና እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

‹‹ሠልፉ #ሰላማዊ ቢሆን እንኳን ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሰዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ላይችሉና በቤታቸውና በመሥሪያ ቤታቸው መካከል ሆነው መንቀሳቀስ ሊሳናቸው ይችላል፡፡ እኛም አገልግሎቶችን ለመስጠት እንቸገራለን፤›› ሲሉ ባርኔት አስታውቀዋል፡፡ ስለዚህ አስተማማኙ ውሳኔ ሠራተኞቻችን ቤት እንዲቆዩ መምከር ነው ብለዋል፡፡

ይሁንና በአዲስ አበባ ምንም ዓይነት ሠልፍ በሌለበት ጊዜ ኤምባሲው ይኼንን መግለጫ በማውጣቱ በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲተቹና የሐሰት መረጃ አሠራጭ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ለረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የተጠራ ምንም ዓይነት ሠልፍ አለመኖሩን አስታውቋል። መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት በአዲስ አበባ የተጠራ ሠልፍ አለ በማለት ያወጡት መረጃ ሙሉ በሙሉ #የተሳሳተም ነው ብሏል።

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ስለ #ድብቅ_እስር_ቤቶች የማውቀው ነገር የለም፡፡›› የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስለ ድብቅ እስር ቤቶች የማውቀው ነገር የለም ብሏል፡፡

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ያሉ 6 ማረሚያ ቤቶች ቃሊቲ፣ቂሊንጦ ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢት፣ ድሬዳዋና ቃሊቲ የሴቶች ማረሚያ ቤት ብቻ ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ጠቅላይ አቃቢ ህግ በምርመራ ያገኛቸው እስር ቤቶች ከእኛ እውቅና ውጭ ያሉ ናቸው ብለዋል፡፡

የሰብዓዊ መብት አያያዝን ለማሻሻልም ዘመናዊ ማረሚያ ቤቶችን እየገነባን ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia