TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ድሬዳዋ⬇️

የፀረ- ሰላም ሃይሎችን ድብቅ አጀንዳ ነቅተው በመከላከልና ለዘመናት የገነቡትን #ፍቅር በማቆየት የተጀመረውን አገራዊ የለውጥ ሂደት ከዳር ለማድረስ እንደሚሰሩ የድሬዳዋ #ገንደ_ተስፋ ወጣቶችና ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ወጣቶቹ #ከፖሊስ ጋር በመስራትና ድብቅ አጀንዳ ያነገቡ አካላትን ሴራ በማክሸፍ ለአካባቢያቸው ለሰላም መስፈን ግንባር ደቀም ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም ገልፀዋል፡፡

በድሬዳዋ ልዩ ስሙ ገንደ ተስፋ በተባለ አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ማንነታቸው ለጊዜው ባልታወቁ አካላት ልዩ #የቀለም ምልክት መቀባትን ተከትሎ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተው ግጭት እዚህም ሊፈጠር ይሆን በሚል ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ ለችግሩ #መፍትሄ ለማምጣት ውይይት ያደረጉት የአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች በድሬዳዋ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች
ለዘመናት የገነቡት ፍቅር ድብቅ አላማን ባነገቡ ፀረ-ሰላም አካላት ሴራ እንደማይደናቀፍ ተናግረዋል።

©ኤዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በመስቃንና ማረቆ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠሩ ላሉ #ግጭቶች መንግስት ዘላቂ #መፍትሄ እንዲያፈላልግ የግጭቱ ተጎጂዎች ጠይቀዋል። ከሰሞኑ በዚህ አካባቢ በተፈጠረዉ ግጭት የዜጐች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ከቀዬአቸዉ ተፈናቅለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሱማሌ ክልል‼️

በቱሊ ጉሌድ ወረዳ መስተዳደር በጌሪና በጃርሶ ጎሳዎች መካከል የተነሳ #ግጭት ለሰው ህይወት ህልፈትና ለአካል ጉዳት መንስኤ እየሆነ ይገኛል፡፡

በሶማሊ ክልል መስተዳድር በፋፈን ዞን የቱሊ ጉሌድ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩት የጌሪና የጃርሶ ጎሳዎች መካከል በትላንትናው እለት ዳግም ባገረሸ ግጭት ለሰው ህይወት ህልፈትና በርካቶችን ለአካል ጉዳት ዳርጓል፡፡

በዚሁ ግጭት ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ቁስለኞች በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ጅግጅጋ ከተማ የካራመራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ለመስማት ተችሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቱሉ ጉሌድ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩት የጌሪና የጃርሶ ጎሳዎች መካከል ለብዙ ጊዜ እልባት ሳያገኙ የቆዩ #አለመግባባቶች የነበሩ ሲሆን እነዚሁ አለመግባባቶች #ዘላቂ የሆነ #መፍትሄ ባለማግኘታቸው በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ዳግም ግጭት እንዲያገረሽና ለሰው ህይወት ህልፈትና ለአካል ጉዳት የዳረገ መንስኤ ሊሆን ችሏል፡፡

የሶማሊ ክልል አስተዳደር በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ላሉት አለመግባባቶች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ በመስጠት ይኖርበታል።

©rajo
@tsegabwolde @tikvahethiopia