TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአዲስ አበባ ነዋሪዎች #ኢትዮ_ቴሌኮም ወደ እጅ ስልካቸው #በሚልክላቸው አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች ብዛት ተማረናል ብለዋል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮምና የተለያዩ ተቋማት አጫጭር መልዕክቶች ስልካቸውን ስለሚያጨናንባቸው አገልግሎቱን እስከማቆም የደረሱ መኖራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ብዙዎቹ መልዕክቶች የማይፈለጉ፣ የግል መብትን የሚጋፉ፣ ጊዜና ገንዘብንም የሚያባክኑ ናቸው፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ኮሚኒኬሽን ሃላፊ ጨረር አክሊሉ ግን ተጠቃሚዎች የማይፈልጓቸው መልዕክቶች እንዳይደርሷቸው የሚያደርግ አሰራር በቅርቡ እንጀምራለን ብለዋል፡፡ የብሄራዊ ሎተሪ በዕጣና ዕድል ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች መልዕክት እንዲያስተላልፉ ፍቃድ የሰጣቸው አሉ፤ ፍቃድ በሌላቸው ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia