TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬇️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ #ቅዳሜ ነሕሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከሰዓት ከ9:00ሰዓት ጀምሮ ከሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን #ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሊሰረዝ ነው⬇️

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊያደርገው የታቀደው ኮንሰርት #ሊሰረዝ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹልኝ ብሏል።

እንደ ዘ-ሀበሻ ምንጮች ዘገባ #ቴዲ ለአዘጋጆቹ "በዚህ የሃዘን ወቅት መድረክ ላይ ወጥቼ የመዝፈን አቅም የለኝም - አልችልምም" ብሏቸዋል ተብሏል።

ድምጻዊው ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሊደረግ የነበረ ሲሆን ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ወደ ፊታችን #ቅዳሜ ተዘዋውሮ ነበር።

ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይኸው ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ የማይካሄድ ሲሆን መቼ እንደሚደረግ እንደማይታወቅ ታውቋል።

ሰው እየሞተ መዝፈን አልችልም ያለው ቴዲ አፍሮ በነገው ዕለት ጠዋት በመድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት በቡራዩና በአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን እንደሚጎበኝ በተጨማሪም የገንዘብ እርዳታ እንደሚያደርግ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።

@tsegabwklde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ጉባኤ‼️

የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በመጪው #ቅዳሜ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስታወቁ።

አፈ ጉባኤው አቶ #ላክደር_ላክባክ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት አስቸኳይ ጉባኤው የሚካሄደው የክልሉን መንግስት የሚመራው ጋህዴን በቅርቡ ባካሄደው ግምገማ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ነው።

ለአንድ ቀን በሚካሄደው ጉባኤ የክልሉ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች ያቀረቡት የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

በምትካቸውም አዲስ ዋናና ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንደሚሾሙ ይጠበቃል ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመቀለ ሰልፍ ሊካሄድ ነው‼️

በመቀለ ከተማ የፊታችን #ቅዳሜ የሚከበረው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህግ የበላይነትና ህገ-መንግስቱ ይከበር የሚል መልዕክት የሚተላለፍበት መሆኑን የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅህፈት ቤቱ በበአሉ አከባበር ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ #ዘመንፈስቅዱስ_ፍስሃ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት የዘንድሮ የብሔሮች ፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በክልል ደረጃ የፊታችን ቅዳሜ በመቀሌ ከተማ በህዝባዊ ሰልፍ ይከበራል።

“በህዝባዊ ሰልፉ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ዘርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ይቁሙ፤ የህግ የባላይነትና ህገ-መንግስቱ ይከበር የሚሉ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ነው” ብለዋል።

“የትግራይን ህዝብ ለማምበርከክ የሚደረጉ ሴራዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው በሰልፉ መልዕክት ይተላለፋል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“በማንነት ጥያቄና በአዋሳኝ አካባቢዎች ምክንያት በማድረግ የክልሉን ህዝብ የሚነኩ ትንኮሳዎች ተቀባይነት የላቸውም” ያሉት ኃላፊው በውጭ ጣልቃ-ገብነትና የውስጥ ሴራዎች እንዲቆሙ የሚያስገነዝቡ መልዕክቶች በሰልፉ እንደሚተላለፉ አመላክተዋል።

“ህዳር 29 ህገ-መንግስቱ የፀደቀበት በመሆኑ የህገ-መንግስቱ ልዕልናን የሚያጎሉ መልዕክቶች በሰልፉ ጎልተው ይወጣሉ” ብለዋል።

በዓሉን በህዝባዊ ሰልፉ በ”ባሎኒ” ስታድዮም በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የገለፁት ኃላፊው በሰልፍ ላይ ከ200 ሺህ በላይ የከተማውና አካባቢው ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia