TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
AASTU🔝የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከተቋሙ አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጠ/ሚ ፅ/ቤት🔝የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መገናኛ ብዙሀን ኮርስፖንዳንት ቡድን...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ🔝

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት ክብርት ወይዘሪት #ብርቱካን_ሚደቅሳ ከቦርዱ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ።

በትውውቅ ፕሮግራሙ ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደገለፁት በተቋሙ ሪፎርም የሚያስፈልጋቸው ስራዎች በመለየት መስራት እንደሚያስፈልግ፣ የተጀመሩት ምርጫን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው ከፊት ለፊታችን የሚጠብቁንን ስራዎች ከመላው ሰራተኞች ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በበኩላቸው የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት ክብርት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለተቋሙ ትክክለኛ ሰው መሆናቸውን ገልፀው ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት የሚችሉ መሆናቸውን ተናግሯል።

ክብርት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ለተቋሙ በሁሉም መመዘኛ ትክክለኛ ሰው መሆናቸውን እና እሳቸው ወደ ተቋሙ በመምጣታቸው በጣም ደስተኛ መሆናቸውንና በአገራችን ዴሞክራሲ ስርዓት የራሳቸውን ዓሻራ ማሳረፍ እንደሚችሉ የቦርዱ አባላትና ሰራተኞች አስተያየታቸውን ገልፀው፤ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ማዕከላዊ ኮሚቴው በኦሮሚያ ክልል #የሰላም ሁኔታ ላይ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ፈረጃ ቶነር! የተለያዩ የኘሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ቀለምች በተሻለ ዋጋ አሉን። በ+251911276145 ይደውሉ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️

የዕርቀ ሰላም፣ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሊቋቋም ነው። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ የተነጋገረው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን እና የማንነትና የወሰን ኮሚሽን እንዲቋቋም ወስኖ እንዲፀድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን ተከትሎ ነው፡፡

በምክር ቤቱ ስብሰባ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽንና የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ለማቋቋም በቀረበ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ የፌደራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ማሻሻያ ተመልክቷል።

ከምክርቤቱ ስቡክ ገጽ ላይ እንዳገኘነዉ በምክር ቤት ውሎ ሁለቱ ኮሚሽኖችን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ለውጭ ሰላምና ደህንናት እና ለህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ምልከታ መርቶታል፡፡

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦዴፓ🔝የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዲፒ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን እያካሄደ መሆኑን የፓርቲው የገጠር ፓለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል። ፓርቲው በስብሰባው ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን የሚያስችሉ #ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። እንዲሁም የህግ የበላይነትን ለማስከበር፣ የሀገር አንድነትን ለማስቀጠል እና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ይገመግማል ተብሏል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH እስከ ታህሳስ 29 ድረስ ለሶስት ዜጎች እጅግ በጣም አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለእየንዳንዳቸው የ150,000 ብር ድጋፍ ለማድረግ ይንቀሳቀሳል።

የምንረባረበው እጅግ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ለሚገኙት ነው‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia