TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጎነደር ዩኒቨርሲቲ🔝

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ችግር #ለመፍታት የሀይማኖት አባቶች ተማሪዎችን አነጋግረዋል። የፀጥታ አስከባሪዎችም በግቢ ውስጥ በመዘዋወር ተማሪውን ለማረጋጋት እና ግቢውን ሙሉ ወደሙሉ ወደቀደመው እንቅስቃሴ ለመመለስ እየሰሩ ነው።

©Nathy
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሞት የተነሳው ኢትዮጵያዊ🔝

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ አንድ ግለሰብ ህይወቱ ካለፈ በኋላ መነሳቱ ተገለፀ። ሟች አቶ #ሂርጳ_ነገሮ ለረጅም ጊዜ በፅኑ ህመም ሲሰቃይ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ ማለትም ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ህመሙ ፀንቶበት ህይወቱ ያልፋል። በአካባቢው ባህል መሰረትም ሳይገነዝ ለ1 ሰዓት አከባቢ ከቆየ በኋላ አስከሬኑ ተገንዞ ወደ ተዘጋጀለት ሳጥን ይገባል። የቀብር ስነ ስርዓቱን ለመፈፀምም ቤተሰቦቹ ሩቅ ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መልዕክት ይልካሉ።

በመቀጠልም ወዳጅ ዘመዶቹ ቦታው እስኪደርሱ ቤተሰቦቹ የተለያዩ የሀዘን ስነ ስርዓቶችን እያከናወኑ ቆይታ አድርገዋል። ሥርዓቱ እየተከናወነ አስከሬኑ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በግምት ከ5 ሰዓት በላይ ከቆየ በኃላ ግን አንድ አስደንጋጭ ነገር ተፈጠረ።ግብዓተ መሬቱ ሊፈፀም ስዓታት የቀሩት ሟች ከአስከሬን ሳጥኑ ወስጥ ድምፅ ማሰማት መጀመሩ ተነግሯል፡፡

ምንጭ: ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት🔝

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወይዘሪት #ብርቱካን_ሚደቅሳን የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እጩ አድርገው ሲያቀርቡ መልዕክቱ ግልጽ ነው፤ መንግሥት ለቀጣዩ ምርጫ ነጻና ፍትሐዊ መሆን ከማንም በላይ ቁርጠኝነት እንዳለው የሚያሳይ ትልቅ እርምጃ ነው።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉ የገጠር መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረ ግለሰብ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራትና በገንዘብ #እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ባዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበረው አቶ መልካሙ ታደሰ ላይ ነው።

ግለሰቡ ለመንገድ ሥራ የሚውሉ መሳሪያዎች ግዢ ለመፈፀም በወጣ ጨረታ የግዢ ስርዓቱን ባለመከተል ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረጉ ውሳኔው እንደተላለፈበት በችሎቱ ተመልከቷል።

የተሰጠውን የመንግስት ኃላፊነት አለአግባብ በመጠቀም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ2008 እስከ 2009 ዓ.ም የተለያዩ መስሪያዎችን ግዢ ለመፈፀም ባወጣው ጨረታ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈበት የውል ማስከበሪያ ሳያቀርብ ውል እንዲገባ በማድረግ የውሉን 30 በመቶ ቅድመክፍያ እንዲፈፀም ትዕዛዝ መስጠቱ ተጠቅሷል።

በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ተቀብሎ በገባው ውል መሰረት መሳሪያዎቹን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሳያቀርብ መቅረቱም በችሎቱ ተመልክቷል፡፡

ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በአምስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሶማሌ ክልል‼️

በሶማሌ ክልል ከ2004 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የክልሉን አሰራር ክፍተትን የተቃወሙ 200 የክልሉ ተወላጆች የፀረ ሰላም ኃይሎች ተብለው #መገደላቸውን በምርመራ ማረጋገጡን ፓሊስ ለፍርድ ቤት ገለፀ።

መርማሪ ፓሊስ የኢትዮጵያ ሰሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የአራት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ላለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት እስካሁን ያከናወነውን የምርመራ ስራ ለችሎቱ አቅርቧል።

በዚህም ፓሊስ ከሀምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ዘርና ሀይማኖት እየተለየ በክልሉ የተፈፀመውን ወንጀልና በጅምላ የተቀበሩትን ከጳውሎስ ሆስፒታል ባለሙያ በመውሰድ አስከሬን ማስመርመሩን በመግለፅ ይህንንም የሚያመላክት የፎቶ ማስረጃ ለችሎቱ አቅርበዋል።

ፓሊስ በጅግጅጋና አካባቢው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ጉዳት 300 ሚሊየን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት አጋጥሟል ሲልም ነው ለፍርድ ቤት የገለፀው።

እንዲሁም በክራውን ሆቴል 42 ሚሊየን ብር ውድመት ማጋጠሙን ፓሊስ የገለፀ ሲሆን፥ በተመሳሳይ በስፖንጅ ፋብሪካ ላይ ኪሰራ ማጋጠሙን ለችሎቱ አብራርቷል።

መርማሪ ፓሊስ ቀሪ የምርመራ ቡድን ወደ ጅግጅጋ በመላክ አሰራሩን የተቃወሙና እንዲገደሉ የተደረጉትን ዜጎች ቤተሰብ የማፈላለግ ስራ ለመስራትና ሌሎች ቀሪ የምርመራ ስራዎችን ለማከናወን 14 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ከ2004 ጀምሮ ተብሎ የቀረበው ምርመራ አዲስና ከፊት ከተጀመረው ምርመራ ጋር ሊካተት እንደማይገባ አንስተዋል።

ጠበቆቹ ፓሊስ ተመሳሳይ ምክንያቶችን እያቀረበ ተጨማሪ ጊዜ እየጠየቀ በመሆኑ ሊፈቀድ አይገባም በማለት ለፍርድ ቤት ጠይቋል።

እንዲሁም ተጠርጣሪዎቹ ከ2004 ጀምሮ በኃላፊነት አልነበሩም ያሉት ጠበቆቹ ከዚህ ጉዳይ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም ብለዋል።

ጉዳዩን የመረመረው ፍርድ ቤትም የፓሊስን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ተጨማሪ ጊዜ ለምርመራ መስጠቱ አሳማኝ ነው በማለት የተጠየቀውን 14 ቀን ፈቅዷል።

በዚህም ለህዳር 27 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ምርመራው ተጠናቆ እንዲቀርብ አዟል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ‼️

የኢትዮጵያ መንግስት፣ በሠብአዊ መብት ጥሰት እና በሙስና የሚጠረጠሩ የቀድሞ ባለሥልጣናት የሚታሰሩበት አዲስ «ከተማ» (እስር ቤት) መገንባት እንደሚያስፈልገዉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐስታወቁ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደነገሩት ኢትዮጵያ ያሏት እስር ቤቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉን «ወንጀለኞች» ለማሠር #በቂ አይደሉም።

አሶሺየትድ ፕሬዝ የዜና ምንጭ (AP) የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር ጠቅሶ እንደዘገበዉ መንግሥታቸዉ ያተኮረዉ ዋና ዋና በሚባሉ ጉዳዮች (ወንጀሎች) ላይ ብቻ ነዉ። «የተቀሩትን በመመሥረት ላይ ለሚገኘዉ ለእርቅ ኮሚሽን ትተነዋል»ብለዋል።

የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንዳስታወቀዉ በሰብአዊ መብት ጥሰት እና በሙስና የሚጠረጠሩ 63 የቀድሞ የመረጃ (የስለላ) እና የጦር መኮንንኖች ታስረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህዝበ ወሳኔ እንዲካሄድ🔝

የሲዳማ ብሔር ክልል ሆኖ #እንዲደራጅ በቀረበው ጥያቄ መነሻ የክልሉ ምክርቤት ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ህዝበ ውሳኔ እንዲያገኝ ለኢፌድሪ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት መፃፉን የተረጋገጠ ሲሆን ደብዳቤው በነገው እለት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ያደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት አስፈፃሚ ኮሚቴዎች #ሪፈረንደም ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮምኒኬሽን መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር የ960 ሚሊዮን ብር #ብድር ስምምነት ተፈራርማለች፡፡ብድሩ በገጠርና በከተማ በጥቃቅንና አንስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ሐሺም ቶፊቅ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️

በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል የሚፈለጉት የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሐሺም_ቶፊቅ
እና ሶስት ሌሎች ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል የሚፈለጉ የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐሺም ቶፊቅ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ገ/ፃድቅ ፣ በወንጀል እንደሚፈለጉ እያወቁ የተጠርጣሪዎችን ሰነድ የደበቁ እና ተፈላጊዎችን አሸሹ በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች ዛሬ ከሰዓት በኃላ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል የሚፈለጉት የደህንነት ከፍተኛ የስራ ኃላፊ በነበሩት ከአቶ ተስፋዬ ገብረፃድቅ ቤት ሰነድ አሽሽተዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ፊልሞን ግርማይ እና ቴዎድሮስ ያዕቆብ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡

ዶ/ር ሐሺም የሚፈለጉ ሰነዶችን በመደበቅና በወንጀል የተጠረጠረችው ባለቤታቸው ዊዳድ አህመድና ወንድሟ ሰሚር አህመድ በተሽከርካሪ ወደ መቀሌ አሽሽተዋል በሚል ፖሊስ ከሷል፡፡

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ተጠርጣሪዎች ከተያዙ ዛሬ 13 ቀናት ሆኗቸዋል፣ቤታቸው ተበርብሯል፣ ፖሊስ ያገኘውን አግኝቷል፣ የተጠረጠሩበት በወንጀል የሚፈለግ ሰው በማሸሽና መረጃ መደበቅ የዋስትና መብት አይከለክልም በሚል በዋስ እንዲለቀቁ
ጠይቀዋል፡፡

ፖሊስ በበኩሉ በአቶ ተስፋዬ ገ/ፃድቅ ሰነድ ማሸሽ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ፊልሞን ግርማይና ተዎድሮስ ያዕቆብ የጦር መሳያና ሁለት ቦምቦችን ከተፈላጊው ቤት አውጥው ሲሸሹ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብሏል፡፡

ወንጀሉ ከባድ በመሆኑና ሰፊ የማጣራት ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ተጠርጣሪዎች ያጠፏቸውን ንብረቶች በየክፍለ ከተማው የማፈላለግና በተለይም በ3ኛዋ ተጠርጣሪ ዶ/ር ሐሺም ባለቤት ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አፍርተዋል የሚል ጥርጣሬ ስላለ ፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቋል፡፡

ችሎቱ ግራ ቀኙን መርምሮ “ይህ ጉዳይ በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀጠሮ ላይ ነው” የሚለውን የጠበቆች አቤቱታ ተከትሎ የአራዳውን መዝገብ ከዛሬው አቤቱታ ጋር መርምሮ በጊዜ ቀጠሮው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ችሎቱ ለህዳር 17፣2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርበኞች እና ግንቦት 7 ተለያዩ‼️

አርበኞች እና ግንቦት 7 #ስለመለያየታቸው በባሕር ዳር አሁን ላይ #መግለጫ እየተሰጠ ነው። ከዚህ ቀደም እንደተለያዩ መግለጫ ቢሰጥም በግንቦት ሰባት አመራሮች በኩል ሁለቱ ድርጅቶች አለመለያታቸው ነበር የተገለጸው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ታዋቂ እና አነጋጋሪ መፅሃፍት በገበያ ላይ ዋሉ‼️መፅሀፍቱን በሁሉም መፅሀፍት ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ። ተጨማሪ በዚህ ስልክ በመደወል መፅሀፍቱን ማግኘት ይቻላል፦ +251911650882
#Update መንግሥት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከአፍሪካ ኅብረት ሰንደቅ አላማ ጎን ለጎን እንዲውለበለብ፤ የሕዝብ መዝሙሩ ደሞ ከኅብረቱ መዝሙር ጋር ባንድ ላይ እንዲዘመር የሚያስችል ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጧል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዐለም ዛሬ
ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ይህኑ በሁሉም መንግሥት መስሪያ ቤቶች ተፈጻሚ ለማድረግ የሕግ ረቂቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia