TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደብረ ማርቆስ‼️

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር #መብራት ለአንድ ወር ያክል እንደሚጠፋ በመወራቱ ወፍጮ ቤቶች በወረፋ መጨናነቃቸውን ተሰምቷል።

ስለሚወራው ወሬ አብመድ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን ምዕራብ ሪጂን የትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ውበት አቤን በስልክ አነጋግሯል፡፡

‹‹ሽብር ለመፍጠር የሚነዛ #አሉባልታ ነው፤ በባለፈው በመኪና ክሬን ዋና የኃይል መስመሩ ተነካክቶ ችግር ተፈጥሮ ኃይል ተቋርጦ ነበር፡፡ እሱንም አስተማማኝ በሆነ መልኩ ጠግነን ሥራ አስጀምረናል፡፡ አሁን ለመብራት መጥፋት የሚሆን ምክንያት የለም›› ብለዋል፡፡

የደብረ ማርቆስና አካባቢውን የኃይል አቅርቦት የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ ተጨማሪ ትራንስፎርመር ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ ውበት ኅብረተሰቡ #የሚወራውን ሙሉ በሙሉ ወደ ጎን በመተው መደበኛ ሕይወቱን እንዲመራ አሳስበዋል፡፡

‹‹ለአንድ ወር ቀርቶ ለአንድ ቀን የምናቋርጥበት ምክንያት የለም፡፡ የተለመዱ የደቂቃዎች መቆራረጦችም እንዳይኖሩ አቅማችንን አሟጠን እየሠራን ነው›› ብለዋል አቶ ውበት፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ማርቆስ አገልግሎት መስጫ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ቸኮልም ‹‹ወሬው ሰንብቷል፤ ማን እንዳስወራው ግን አላወቅንም፡፡ ሕዝቡ መደናጥ እንደሌለበት በከተማ አስተዳደሩ በኩልም መረጃ ለማድረስ ሞክረናል፡፡ በዝናብና ዛፎች ንክኪ ምክንያት ድንገተኛ ችግር ካላጋጠመን በቀር የኃይል አቅርቦት ሥራችንን ያለመቆራረጥ እያደረስን ነው›› ብለዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ በጥቅምት ወር አጋማሽ ከአንድ ሳምንት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል።

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia