TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በፈረንሳይ ፓሪስ በ1999 ዓ.ም ፊቷ ላይ ከፍተኛ የአሲድ ጉዳት ደርሶባት የነበረችውን #ካሚላት_መህዲን አግኝተው አነጋግረዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ተወልደ‼️

"አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀላፊነት ተነስተዋል የሚለውን ነገር ለማጣራት የአየር መንገዱ Chief Operating Officer (COO) የሆኑት አቶ መስፍን ጣሰው ጋር አሁን ደውዬ ነበር። በመልሳቸውም: "እኔ የማውቀው ነገር የለም። #የሀሰት ዜና ይመስለኛል። ቀኑ ሙሉውን ከአቶ ተወልደ ጋር ነው የዋልኩት።" ሌላ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ጋር ጥይቄም "He is in duty" የሚል መልእክት ደርሶኛል። የቦርድ ስብሰባ ግን በዚህ ሰአት እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እስካሁን ያለው ነገር ይህን ይመስላል።"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፓሪስ አሁን‼️

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አሕመድን በፓሪስ ኢሊዜ ቤተመንግሥት በወታደራዊ ማርሽ #ከፍተኛ አቀባበል አደረጉላቸዉ። ሁለቱ መሪዎች በአሁኑ ሰዓት በሁለቱ ሃገራት የወዳጅነት ግንኙነት ላይ እየተወያዩ እንደሆን ቦታዉ ላይ የምትገኘዉ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ወኪሏ ሃይማኖት ጥሩነህ ገልፃልናለች።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በ2021 ስልጣን ይለቃሉ‼️

የጀርመኗ መሪ #አንጌላ_ሜሪከል ከሀገሪቱ መራሄ መንግስትነት በፈረንጆቹ 2021 እንደሚለቁ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

“የስልጣን ዘመኔ ሲያልቅ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ሃላፊነት አልፈልግም፤ እለቃለሁ” ነው ያሉት ሜሪከል።

የሚመሩት ፓርቲ ክርስቲያን ዴሞክራቲክ ዩኒየን ፓርቲ በቅርቡ በተካሄዱ አካባቢያዊ ምርጫዎች ውጤት ማጣቱ ተነግሯል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሜሪከል በመጪው ታህሳስ ወር የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ዩኒየን ሊቀመንበር ምርጫ ሲካሄድ እሳቸው እንደማይወዳደሩ ገልጸዋል።

ፓርቲያቸው በቅርቡ በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ ለነበረው የውጤት መዳከም ሙሉ #ሃላፊነቱን እንደሚወስዱን ነው የጠቆሙት።

ከፈረንጆቹ 2000 ጀምሮ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆንም እያገለገሉ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቄለም ወለጋ ዞን⬇️

በቄለም ወለጋ ዞን #ጊዳሚ ወረዳ ቄለም በምትባል አነስተኛ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጅ እንደሚሉት ከሆነ በሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና በኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ታጣቂዎች መካከል ዛሬ ጠዋት #ግጭት ነበር።

ነዋሪው እንደሚሉት የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን የያዙ ስድስት ኦራል መኪኖች ዛሬ ጠዋት ወደ ከተማዋ ገብተዋል።

''እንደ መትረየስ ያሉ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ድምጾች ሲተኮሱ ይሰማል። ትናንት ቤጊ ወረዳ ውስጥ ከፍተኛ ውጊያ እንደነበረ ሰምተናል። ዛሬ ጠዋት ቄለም ከተማ ግጭት ነበር።'' እኚህ የከተማው ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱን በመሸሽ ተሽሽገው ይገኛሉ።

ጊዳሚ ወረዳ ግራኝ ሶንካ በምትባል መንደር ውስጥ የሚኖሩ ሌላኛው ነዋሪ ከትናንት እሁድ ጀምሮ የተኩስ ድምጽ ሲሰሙ እንደነበረ ይናገራሉ።

''ከትናንት ጠዋት ጀምሮ በቤጊ እና ቄለም ወረዳዎች መካከል ባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ነበረ። እንደሰማነው ከሆነ ግጭቱ በሃገር መከላከያ እና በኦነግ ሠራዊት አባላት መካከል ነው'' ይላሉ። ከእኚሁ ነዋሪ እንደሰማነው እሳቸውን ጨምሮ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ከነቤተሰባቸው ወደ ሌሎች ስፍራዎች ሽሽተዋል።

የቄለም ወለጋ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ታመነ ኃይሉ በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ በሃገር መከላከያ እና በኦነግ ሠራዊት አባላት መካከል የተደረገ ምንም አይነት ግጭት የለም ይላሉ። ''ኦነግ ትጥቅ መፍታት የለበትም የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በቅርቡ ተካሂደዋል። ሰልፎቹም
በሰላማዊ መንገድ ተጠናቀዋል። ከዚህ ውጪ ምንም አይነት ግጭት የለም። በፌስቡክ ላይ የሚወራ ወሬ ነው'' ብለዋል።

አቶ ታመነ የሃገር መከላከያ ሠራዊት በዞኑ ውስጥ ለምን በስፋት ተሰማራ ተብለው ለተጠየቁት ''ከዚህ ቀደምም የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በስፋት ተሰማርተው ይገኛሉ። ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም። ጊዳሚ ወረዳ ለደቡብ ሱዳን ድንበር ቅርብ ናት ለዚህም ነው የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በቦታው የሚገኙት'' በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ታመነ ''ኦነግ ትጥቅ መፍታት የለበትም'' ተብሎ በተወጣው ሰልፍ ምክንያት ዛሬ ጠዋት ድረስ በዞኑ አንዳንድ ከተሞች መንገድ ዝግ ሆኖ ቆይቷል። መንገድ ለማስከፈት ኃይል ከመጠቀም ይልቅ በሃገር ሽማግሌዎች አማካኝነት መፍትሄ ለመፈለግ ጥረት እየተደረገ ነው''
ብለዋል።

በሌላ በኩል የደምቢዶሎ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ክብረት ዋቅጋሪ ትናንት ምሽት ሦስት የፖሊስ አባላት በቦንብ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላቸው እንደመጡ ይናገራሉ።

''ከለበሱት የደንብ ልብስ መረዳት እንደቻልኩት የፖሊስ አባላት ናቸው። ምናልባትም የደንቢ ዶሎ ከተማ ፖሊስ አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም። ሦስቱም በቦንብ የተጎዱ ሲሆን፤ እግራቸው ላይ እና ጀርባቸው ላይ ክፉኛ ቆስለዋል። የቦንቡ ፍንጣሪ ሰውነታቸው ውስጥ ይገኛል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ይህንን ሁኔታ በተመለከተ ከኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎች፣ ከሃገር መከላከያ ሠራዊትም ሆነ በቅርቡ ከተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

የኦነግ ባለስልጣናትም በክስተቱ ላይ ለጊዜው አስተያየታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለቴፒ‼️

የክልሉ መንግስት እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት በቴፒ ያለውን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ለTIKVAH-ETH የተላኩ መልዕክቶች ያስረዳሉ። ሁኔታዎችን አሁን ካሉበት ወደሌላ ደረጃ ሳይሸጋገሩ መንግስት መፍትሄ ሊያበጅ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ የመቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሰዎች ህይወት #አለፈ። ከዋና ከተማዋ ጃካርታ መብረር ከመጀመሩ 13 ደቂቃ በኋላ በሰሜናዊ ጃቫ ደሴት #ከተከሰከሰው አውሮፕላን #የተረፈ ሰው አለመኖሩ የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደኢህዴን‼️

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የ5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤን አስመልክተው መግለጫ ተሰጥተዋል፡፡

የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ከጥቅምት 20 እስከ 24/2011 ዓ.ም ድረስ ያካሂዳል፡፡

ጉባዔውን አስመልክተው የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ #ህይወት_ኃይሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ በሐምሌ ወር በተደረገው መደበኛ ጉባዔ ውይይት ሊደረግባቸው የሚገቡ አጀንዳዎች ባለፉት ወራት በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ውይይት እንዳልተደረገባቸው ጠቁመው በአሁኑ ጉባዔ ውይይት እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል፡፡

አፈ ጉባዔዋ አያይዘውም አሁን በክልሉ አንጻራዊ #ሰላም መስፈኑን ተናግረው በየአካባቢው የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር የምክር ቤቱ አባላትሚና የጎላ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ከጥቅምት 20 እስከ 24/2011 ዓ.ም ምክር ቤቱ በሚያካሂደው ጉባዔ የሚወያይባቸው አጀንዳዎችም፡-

1ኛ የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ረቂቅ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2010 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ፣

3. የክልል መንግስት የ2ዐ10 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2ዐ11 በጀት ዓመት ዕቅድ፣

5. የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2ዐ10 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ፣

6. የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2ዐ10 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ፣

7. ልዩ ልዩ አዋጆች፣ ደንብና የውሳኔ ሀሳብን በተመለከተ፡-

ሀ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ፣
ለ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ የዋና ኦዲተር መ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅን እንደገና
ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
ሐ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ /ጠቅላይ አቃቤ ህግን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
መ/ የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
ሠ/ በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖችን ለማቋቋም የቀረበ የውሳኔ ሀሳብና
ረ/ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ለማሻሻል የወጣ ደንብ

8. የክልል ጥያቄን በተመለከተ፣

9. ሹመት እና የዳኞች ስንብት የሚሉ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ደኢህዴን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር ከአንድ ወር በኋላ #ይቃለላል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መረጃዎችን፣ ድርጅታዊ ማስታወቂያዎችን እና በማንኛውም ጉዳይ ሀሳቦችን ለመለዋወጥ ከ @tsegabwolde በተጨማሪ በስልክ ቁጥር 0919 74 36 30 ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኤማኑኤል ማክሮን በፓሪስ ሲገናኙ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update በአዳማ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ 6መቶ ቤቶች ላይ #እርምጃ መወሰዱን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Sport ሰበር ዜና‼️ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኙን #ጁሊያን_ሎፕቴጊን አሰናበተ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በወንድ #ጥረት ብቻ የተገነባ ሀገርም፣ ቤትም የለም!" ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወቃይት ጠገዴ⬆️

ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው #ጎንደር ከተማ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት #ተፈናቃዮች መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ይስጠንና ወደቀያችን እንመለስ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።  ቁጥራቸው ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ አብዛኛዎቹ ደግሞ በአፍላ የወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ እነዚህ ተፈናቃዮች በጎንደር ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ በተዘጋጀላቸው ጊዚያዊ መጠለያ ውስጥ ነው ያሉት - በተጨናነቀ ሁኔታ።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia