TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sport ሰበር ዜና‼️

የሌስተር ሲቲ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት ሂሊኮፍተር በኪንግ ፓወር ስታዲየም የመኪና ማቆሚያ ስፍራ #መከስከሱ ተሰማ። የአደጋው መንስኤ እና በውስጡ ስለነበሩ ሰዎች ማንነት ለጊዜው የተሰማ ነገር የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዶክተር አብይ ጉዞ ወደ አውሮፓ‼️

ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ ዛሬ ማምሻውን ለመጀመሪያ የአውሮፓ ጉብኝታቸው ከሀገር ይወጣሉ። ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ማክ ሮን ጋር ላላቸው የሰኞ ጠዋት ቀጠሮ ጥቂት ሰዓታት ሲቀራቸው አውሮፕላናቸው #ፓሪስ ያርፋል። ከሳቸው ጋር የውጭ ጉዳይ፣የገንዘብና የሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስትሮች አብረው ይጓዛሉ።

ዶክተር አብይ ማክሰኞ ጀርመን ይገባሉ። በርካታ የአፍሪካ መሪዎች በሚሳተፉበት መድረክላይም ይካፈላሉ። ከዛ በኋላ ከ20ሺ የማያንሱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ይገናኛሉ። ዝግጅቱ ፍራንክፈርት ከተማ ነው የሚደረገው።

©ከአለምነህ ዋሴ(መጠነኛ የቃላት ለውጥ የተደረገበት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በባሕር ዳር፣ጎንደር፣ደብረ ብርሃን ፣ ወልዲያ እና ደሴ እና በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፉ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

🔹ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን ማውደም በማንነታችን ላይ የተጋረጠ ጥቃት ነው፡፡
🔹የማንነት ጥያቄዎች መፍትሄ ያግኙ!
🔹ጣናን እና ላሊበላን እንታደግ የሚሉ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ዛሬ ጠዋት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ:- ከክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ከክቡር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው፣ ከክቡር ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ ከክቡር ዶ/ር ስለሺ በቀለ፣ ከክቡር አቶ ኡመር ሁሴን እና ከሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን #በጣና ሀይቅ ዙሪያ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን የእንቦጭ አረም ወረራ ጎበኙ።

በጉብኝታቸውም:- አረሙ በሀይቁ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን፣ የክልሉ አመራሮችም ህብረተሰቡን #በማስተበር ጉዳቱን ለመቀነስ እያደረጉ የሚገኙት ጥረት አበረታች መሆኑን፣ የፌዴራሉ መንግስትም ጥረቱን በማገዝ በጥትና ላይ የተመሰረተ #እርምጃ እንደሚወስድ፣ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ:- ከክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ከክቡር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን ከጎርጎራ ጀምሮ ደንቢያ እና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎችን እና በሊቦ ከምከም ወረዳ አግት ቅርኛ ቀበሌ ላይ በመገኝት በጣና ሀይቅ ዙሪያ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን #የእንቦጭ አረም ወረራ ጎብኝተዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia