TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
WALTA TV! ዋልታ ቴሌቪዥን ከጀዋር መሀመድ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ እየተላለፈ ነው።

walta tv፦ freq=11512 vertical 27500
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Venture Addis
This Saturday, Live Roots Reggae, Jungle Bar
@VentureAddis
Audio
#update አማሮ⬆️

ደቡብ ክልል ውስጥ በአማሮ ወረዳና በምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት #ለማብረድ ከገቡ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ሦስቱ #መገደላቸውንና ሁለት መቁሰላቸውንም የተናገሩት አስተዳዳሪው አቶ አማኑዔል አብደላ “ታጣቂዎቹም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰዎች ስለ መሆናቸው መረጃ ደርሶናል” ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ስለጉዳዩ መረጃ እንደደረሳቸው የተናገሩት የኦነግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ “ድርጊቱ የተፈፀመው ‘በኦነግ ሠራዊት ነው፤ አይደለም’ የሚለውን በማጣራት ላይ ነን” ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

የጀርመን የመኪናዎች አምራች ድርጅት #ቮልስ_ዋገን ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቮልስ ዋገን ኩባንያ አመራሮችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይታቸውም ኩባንያው በኢትዮጵያ ፋብሪካ ለማቋቋም በጥናት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ለአውቶ ኢንዱስትሪ አመቺ ሁኔታ ከተፈጠረ ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ መንግስት ለመኪና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደረግ ገልጸው ኩባንያው በተቻለ ፍጥነት ጥናቱን አጠናቆ የኢንቨስትመንት ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ምክር ቤቱ ነገ ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ.ም በሚያካሂደው የ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ዋና አፈጉባኤውን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዱል ጃባርበደቡባዊ ተገደሉ‼️
#update አብዱል ጃባርበደቡባዊ ተገደሉ‼️

በአፍጋኒስታን የምርጫ እጩ ተወዳዳሪ #ከታሊባን በተሰነዘረው ጥቃት ተገደሉ።

እጩ ተወዳዳሪ #አብዱል_ጃባርበደቡባዊ አፍጋኒስታን የሄልማንድ ግዛት በፈነዳው ቦንብ ጥቃት ነው ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር የተገደሉት፡፡

አብዱል ጃባር ቅዳሜ ለሚካሄደው የምክርቤት ምርጫ ዝግጅት በማድረግ ላይ እያሉ በላሽካርጋህ ከተማ ተገድለው መገኘታቸውን የሄልማንድ አስተዳዳሪ አስታውቀዋል፡፡

የሄልማንድ አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ ኦማር ዝዋክ ከሟቾቹ በተጨማሪ ሰባት ሰዎች በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለፁ ሲሆን ጥቃቱን የፈፀመው ምርጫው እንዳይካሄድ ጥረት በማድግ ላይ የሚገኘው የታሊባን ታጣቂ ቡዱን ሳይፈጽመው እንዳልቀረ ተጠቅሷል፡፡

የታሊባን ታጣቂ ቡዱን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ቅዳሜ በሚካሄደው ምርጫ እንዳይሳተፉ #ያስጠነቀቀ ሲሆን በትምህርት ቤቶች የምርጫ ማእከላት እንዳይኖሩም አስጠንቅቆ ነበር፡፡

ከምርጫው ጋር ተያይዞ ባለፉት ሁለት ወራት አብዱል ጃባርን ጨምሮ 10 የምርጫ እጩዎች #የተገደሉ ሲሆን ሁለት እጮዎች ተሰውረዋል ተሰውረዋል፡፡

249 የምክርቤት አባላት የሚመረጡበት የአገሪቱ ምርጫ ለሶስት ዓመታት የዘገየ ሲሆን የፊታችን በያዘነው ወር ኦክቶበር 30 ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ ለግድቡ ሊሰራቸው የነበሩ ሶስት የሀይል ማመንጫ ተርባይኖችን ውል #ለጀርመን ኩባንያ በጨረታ ሰጥቷል።

ምንጭ፦fbc
@tsegawolde @tikvahethiopia
እናስተውል! በ1 ደቂቃ ውስጥ በሀሰት መረጃ ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት ቀላል ነው የተጣሉትን ህዝቦች ለማስታረቅ ግን 100 አመት ላይበቃ ይችላል። ግጭት መፍጠር ቀላል ሊሆን ይችላል ያን ግጭት ማስቆም ግን አስቸጋሪ ነው። መፍትሄ ማምጣት እንደ ችግር መፍጠር ቀላል አይደለም።

እናስተውል!!

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን⬆️በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ መክፍቻ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባደረጉት ንግግር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ ለተነሱላቸው ጥያቄዎችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተጨማሪ #ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ታገሰ_ጫፎ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሶሻል ሚዲያን በተመለከተ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሚድያዎችና ማህበራዊ ድረገጾች በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ የተነሱ አንኳር ነጥቦች፡-

•አንዳንድ ጋዜጠኞች ስራቸውን ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ግለሰቦች እንዳሉ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁሉንም በአንድ መጨፍለቅ ተገቢ አይደለም፡፡

•የሚድያዎች አሁን የመጣውን ለውጥ ሀላፊነት ወስደው እንዳይቀለበስ ሊሰሩ ይገባል፡፡

•የሚድያ ነጻነት ተጠናቅሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ሚድያው የሚያጠፋውን ጥፋት ብቻ እያያን ከምንሄድ።

•ሚድያዎች ሃብት ዕጥረት እንዳይገጠማቸው ዕጥረት ማህበረሰቡ ሊያግዛቸው ይገባል፡፡ በተለይም ፍትሃዊ የሆነ የማስታወቂያ ስርጭት ያስፈልጋል፡፡ ከልሆነ ግን ገንዘብ ያላቸው አካላት መጠቀሚያ ሊሆኑ ይችላሉ።

•አክቲቪስት እና ጋዜጠኝነትን መለየት ያስፈልጋል፡፡ አክቲቪስቶች ቢተቹም ችግር ያለባቸው፡፡ ጋዜጠኝነት ግን በመርህ የሚመራ በመሆኑ ያንን ተከትሎ መስራት ይገበዋል፡፡

•የማህበራዊ ሚድያዎች የአለም አቀፍ ስጋቶች ናቸው፡፡ በኛ አገር ያለው ሁኔታ የተደራጁ የጥላቻ ንግግር ስራዎች የሚደረጉበት ነው።

•አንዱ መፍትሄው ትክክለኛ መረጃ ወዲያው መስጠት ነው፡፡

•በኢትዮጵያ ጥላቻ ስራዎች የሚያራሚዱ የማህበራዊ ድረ ገጾ ተካታይ አላቸው፡፡ በኛ አገር የፖለተካ ፓርቲዎች በማህራዊ ድረገጾች ዋነኛ መጠቀሚያ ያደርጋሉ፡፡

•በኛ አገር ማህበራዊ ድረገጾች ለበጎ አለማ የማዋል አዝማሚያው ዝቅተኛ ነው፡፡ አብዛኛው #ለጥፋት አላማ ነው የሚውለው ፡፡

•ጥላቻን የሚያስፋፉ የማህበራዊ ድረ ገጾች የአንዳንዶች የገቢ ምንጭ በመሆኑ መተባበር አይገባንም

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወታደሮቹን በተመለከተ‼️

በቅርቡ የደመወዝ ጭማሬ ለመጠየቅ ወደ ቤተ መንግስት ስለመጡት ወታደሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለፓርላማው የተናገሩት ፡-

• የታጠቀ ወታደር ወደ ቤተ መንግስት የመጣው አገራዊ ለውጡን #ለማደናቀፍ ታስቦ የተደረገ ነበር፡፡

• ይሁን እንጂ ሁሉም የመጡት ይህን እሳቤ ይዘው ነው የመጡት ለማለት ያስቸግራል፡፡ በአንዳንድ #ተንኮለኞች ሴራ ተጠንስሶ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡

• በዕለቱ የተወሰደው እርምጃ በጥንቃቄ ባይሆን ኖሮ አገርን ወደቀውስ የሚከት ክስተት ነበር ፡፡

• አሁን ላይ ራሱ ወታደሩ በሴራው ውስጥ የነበሩትን የድርጊቱን መሪ እየለየ አሳልፎ እየሰጠ ነው፡፡

• በወቅቱ የወታደሮቹን አመጣጥ ወታደራዊ ጥበብ በሚጠይቀው መልኩ አረጋግቶ መመለስ መቻሉ አገርን የማትረፍ ወሳኝ እርምጃ አድርጌ ነው የምወስደው፡፡

• እየተዝናነሁ፣ እየሳቅኩ ቃለ መጠይቅ የሰጣሁት መንግስታችን ተነከ ብለው ከተለያዩ አቅጣጫዎች ህዝቡ ለመዋጋት እየመጠ ስለነበረ እነሱን ለማረጋጋት ነበር፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወጣቶቹ ከጦላይ ተለቀቁ⬇️

በአዲስ አበባ ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።

ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩት 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መለቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር #ፋሲካ_ፋንታ ለfbc ተናግረዋል።

የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው፥ ዛሬ ማለዳ ላይ የጋራ ውይይት ከተደረገ በኋላ ተጠርጠጣሪዎቹን ወደ አዲስ አበባ የሚመልሱ ተሽከርካሪዎችን በማቀረብ እንዲለቀቁ ተደርጓል ብለዋል።

ወጣቶቹ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆኑ፥ በቆይታቸውም የተለያዩዩ ስልጠናዎችን ሲወስዱ መቆየታቸው ተመልክቷል።

በዚህም መሰረት ወጣቶቹ በጦላይ ለአንድ ወር እራስን ከወንጀል ስለማራቅ እና ተያያዠ ስልጠናዎችን ለመስጠት የተያዘውን የጊዜ ሰሌዳ በማጠናቀቃቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ የማጓጓዝ ስራ ተጀምሯል ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia