#update የመን⬇️
በየመን ከሶስት ዓመታት በፊት የእርስ በርስ #ግጭት ተከስቷል፡፡ እንደ ሳኡዲ አረቢያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ያሉ ሀገራት በጦርነቱ እጃቸዉን አስገብተዉ ንጹሀን ዜጎች ላይ የአየር እና የምድር ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል በሚል ከሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ክስ ይነሳባቸዋል፡፡
የመን ወደ ቀድሞ መረጋጋቷ መመለስ ባለመቻሏ የግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ተስተጓጉለዋል፡፡ ከዉጭ ሀገራት የሚላኩ የምግብ እና የሰብዓዊ አርዳታዎችን በጦርነቱ ምክንያት ለየመናዊያን በበቂ ሁኔታ ማድረስ አልተቻለም፡፡
በዚህም ከ13 ሚሊየን በላይ የመናዊያን የከፋ #ረሀብ ስጋት እንደተጋረጠባቸዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተ.መ.ድ) አስታዉቋል፡፡
የዉጭ ሀገር ጣልቃ ገብነት ሀገራት እና እርስ በርስ የሚዋጉ የመናዊያን የረሀብ አደጋ የተጋረጠባቸዉን ዜጎች ለመታደግ ግጭቱን እንዲያቆሙም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ቢቢሲ በዘገባዉ እንዳሰፈረዉ በየመን በተቀሰቀሰዉ ግጭት ከ10ሺህ በላይ ሰዎች #ህይወታቸዉን አጥተዋል፤ ሚሊዮኖች ደግሞ ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia