TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአምቦ ዩኒቨርሲቲው መምህር ስዩም ተሹመ የተገኘ መረጃ...

ዶ/ር አብይ አህመድ እና ፕ/ት #ኢሳያስ_አፈወርቂ #በአቡ_ዲያቢ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
================================
ከአንድ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባልደረባ ባገኘሁት መረጃ መሰረት፣ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትላንት የአልጄርሱን ስምምነት ለመቀበል ያሳለፈው ውሳኔ የኢትዮጲያ መንግስት በተናጠል የወሰደው እርምጃ አለመሆኑን ለመረዳት ችያለሁ። ከዚያ ይልቅ፣ የኢትዮጲያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኤርትራው ፕረዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በአቡ ዲያቢ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ጠ/ሚ አብይ በሳውዲ አረቢያ ያደረጉትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ ወደ አቡ-ዲያቢ ተጉዘው እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ ወቅት የኤርትራው ፕረዜዳንት “ለሕክምና” በሚል ሰበብ ወደ አቡ-ዲያቢ ማቅናታቸው ይታወሳል። ከላይ የጠቀስኩት የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባልደረባ እንደነገረኝ ከሆነ ሁለቱ መሪዎች በአቡ-ዲያቢ ተገናኝተው መክረዋል።

በመሆኑም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርሱን ስምምነት ለመቀበል የወሰነው በተናጠል ሳይሆን በቅድሚያ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመነጋገር የተወሰደ እርምጃ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ቡሬ⬆️

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እና ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረውን እርቅ ተከትሎ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር መካከል ተገኝተው የቡሬ ግንባር ይባል በነበረው ቦታ በጋራ ሆነው ከሁለቱ አገራት የሀገር መከላከያ ሰራዊቶች ጋር የአዲስ አመትን እያሳለፉ ይገኛሉ።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ-ኤርትራ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እና ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ዛሬ በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን በምስራቅ በኩል ከአፋር ክልል ጋር በሚያዋስነው #በቡሬ ግንባር እና በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል ከትግራይ ክልል ጋር በሚያዋስነው #በዛላንበሳ ግንባር በአካል በመገኘት የሁለቱንም አገራት የሰራዊት አባላት ከጎበኙ በሁዋላ ደባይሲማ - ቡሬ እና ሰራሃ - ዛላምበሳ ድንበሮች ለተሽከርካሪ ክፍት መሆናቸውን አብስረዋል። ይህም የአዲሱ ዓመት ታላቅ #ስጦታ ሲሆን የአካባቢው #ሰላም #ጥልቀት እንዲኖረው እንደሚያደርግ ታምኖበታል።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኤርትራ⬆️

በአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ የሚመራው ልዑክ ዛሬ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ጋር ተገናኘ፡፡ ልዑኩ በቆይታው ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን የሁለትዮሽ ግንኙነት #ለማጠናከር የአማራ ክልል የተወሰነ ርቀት እንደተጓዘ ገልጾ፤ ምክር ቤቱ ያለውን ልምድ እንደሚያካፍልም ተናግሯል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ንግግር ተከፍቷል። ፕሬዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ ዛሬ ባደረጉት ንግግር ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዓብይ_አህመድ እና ለኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ #ኢሳያስ_አፈወርቂ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኤርትራን ፕረስ" በሚል ስም የሚታወቀው የፌስቡክ ገፅ በትላንትናው ዕለት እንደገለፀው ከዚህ በሁዋላ በአስመራ ላለው የፕሬዝደንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ መንግስት የሚያደርገውን #ድጋፍ አቁሟል። ምክንያቱ ደግሞ ፕሬዝደንቱ ልጃቸውን #አብርሀም_ኢሳያስን ፅህፈት ቤታቸው ውስጥ አማካሪ አድርገው ወደ ስልጣን ጠጋ ጠጋ እያረጉ ነው በማለት ነው። ገፁ ፕሬዝዳንቱን "አምባገነን" ያላቸው ሲሆን "ሰማእታት ህይወታቸውን የሰጡት የኢሳያስ ስርወ-መንግስት ለመመስረት አይደለም" ሲል አክሎ ገልጿል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(AP)
@tsegabwolde @tikvahethiopia