TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ⬆️በአሁኑ ሰዓት በሀዋሳ ከተማ መስቀል አደባባይ ለሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) ከፍተኛ አመራሮች የአቀባበል ስነ ስርዓት በመደረግ ላይ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• ከንግዲህ ትኩረታችን ወጣቱን የስራ ባለቤት ማድረግ ነው

• ፊታችንን ወደ ስራ ለማዞር የማብሰሪያው ዕለት ነው #ዛሬ

• የልማት እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ማድረግ የመንግስት ዋነኛው ስራ ነው

• የኢንዱስትሪ ልማት ሲስፋፋ ቦታው ለትራንስፖርት ምቹ መሆኑ ይታያል፤ አዳማን የሚያህል ምቹ ስፍራ የለም፤ የባቡር መስመር፣ ፈጣን መንገድ፣ ወደፊት በቅርብ ርቀት የሚሰራው ትልቁ የአየር ማረፊያ

• የአዳማ ወጣትና ነዋሪ ላለፉት ጊዜያት በተካሄደው ትግሉ ካለአንዳች ጥፋት ተቃውሞውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልፅ የቆየ ነው

• የባለሀብቶች ዋነኛው ጥያቄ መንገድ አለ ወይ ሳይሆን ሰላም አለ ወይ በመሆኑ ሰላማችሁን መጠበቃችሁን አትዘንጉ

• በተለመደው መንገድ በኦሮሞ ባህል ባለሀብቱን የመሳብ የማቀፍ ስራችሁን ቀጥሉ

• ከወራት ትግል በኋላ ወጣቱ አሁን ፊቱን በሙሉ ልብ ወደ ስራ ደወ ልማት ወደ እድገት ማዞር ይኖርበታል፡፡ የትግል ሱስ ያለበት የለምና፡፡

• ዶ/ር አርከበ ሰርቶ የሚያሳይ ብቃት ያለው ከፖለቲካ ሻጥር ራሱን አውጥቶ በስራ የተጠመደ ክቡር ሰው ነው

• ቀበቶአችሆን አጥብቃችሁ ለሚጠብቀን ቀጣይ ስራ ተዘጋጁ

• ዶ/ር መሰለ ኃይሌ በታላቅ ጥረት ውጤት እንድናመጣ እያገዘን ያለ በመሆኑ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል

• አዳማ የሰላም የፍቅር አብሮ የመኖር አብነት በመሆኑ ባለሀብቶች ወደ አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፊታችሁን እንድታዞሩ እመክራችኋለሁ

• ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ ተግባራት ላይ ብትሰማሩ መንግስት ከፍተኛ እገዛ ያደርግላችኋል

• የኢትዮጵያ እውነተኛ የተሃድሶ በርግጥም ከፊታችን እየመጣ ነው

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ዶ/ር አርከበ #ሰርቶ የሚያሳይ ብቃት ያለው ከፖለቲካ ሻጥር ራሱን #አውጥቶ በስራ የተጠመደ ክቡር ሰው ነው።"

▪️▪️▪️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ▪️▪️▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• የኢንዱስትሪ ልማት የአገራችንን ጎስቋላ ገፅታ የሚለውጥ ነው

• ግብርና እንዲዘምንና በሂደትም ለኢንዱስትሪ መሪነቱን እንዲለቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው

• መንግስት ለኢንዱስት ልማት ትኩረት ሰጥቷል

• በዘርፉ ተጨባጥና ፍሬያማ ስራዎች እየተሰሩ ነው

• የተመቻቸ የኢንዱስትሪ ፓርክ ባለሀብቶች በአጭር ጊዜ ስራ እንዲጀምሩ ያስችላል

• የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፋና ወጊ ከሆኑት መካከል ነው

• በጠርቃጨርቅና አልባሳት ስፔሺያላይዝ ያደረገ ፓርክ ነው

• ለባቡር፣ አየር፣ የብስ ትራንስፖርተ ቅርበት ያለው ከተማ ነው አዳማ

• ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል፣ የአርሶ አደሩን ገቢም የሚያሻሽል ፓርክ ነው

• በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀስ ሲጀምር ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል

• የቴክኖሎጂ ሽግግርኽ የጥናትና ምርምር ማዕከል ይሆናል ፓርኩ

• የላቀ የብቃት ማዕከል እንዲሆን እንሰራለን

• ወጣቶች በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ተደራጅተው ለኢንዱስትሪ ፓርኩ ግብዓት እንዲያቀርቡ ይመቻችላቸዋል

• የክልሉ መንግስት ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሊ/መንበር በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ2000
ሄክታር በላይ መሬት ላይ ያረፈ ፓርክ ነው

• ከሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና ከሌሎች ቀደም ሲል ከተሰሩት ፓርኮች ልምድ ተቀምሮ የተሰራ ነው

• በዋናው የኢትዮ-ጅቡቲ የኤክስፖርት ኮሪዶር ላይ የሚገኝ ፓርክ ነው

• ትላልቅ ዓለም አቅፍ ኩባንያዎች የሚስተናገዱበት ፓርክ ነው

• ከአፍሪካ ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አንዱ ነው

• ኢትዮጵያ በ2012 በድምሩ 30 ፓርኮች ይኖሯታል

• በኢንዱስትሪ ፓርኮች የኃይል አቅርቦት እጥረት ስላለ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት

• በዘርፉ የሰው ኃይል ልማትም ሌላው ወሳኝ ጉዳይ ነው

• የአዳማና አካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች ፓርኩን እንደ ዓይናቸው ብሌን ሊጠብቁት ይገባል

• ለዚህ ፓርክ ልማት ተነሺዎች የስራ ዕድል መፍጠር መንግስት ያስቀመጠው አቅጣጫ በመሆኑ ይህንኑ አቅጣጫ ይዘን እንሰራለን

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ላሊበላ⬆️የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች የቅዱስ ላሊበላ ቅርሶች ዓለም እንዲታጋቸው ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፡፡ "ላሊበላ የዓለም ቅርስ ነው፡፡ ታሪክን ሳይጠብቁ ታሪክ መስራት አይቻልም፡፡" የሚሉ ሀሳቦች ተንጸባርቀዋል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ⬇️

"የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረትን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በፕሬዘዳንትነት እየመራ 2010 ያሳለፈ ሲሆን በአሁን ሰዓት ህብረቱ ለሁለህ አመት የሚመሩ የስራ አስፈፃሚ ምርጫ እያደረገ ይገኛል። በመጀመሪያ 9 ስራ አስፈፃሚ ተመርጦ የተመረጡትም ህንረቶች ስትራቴጂክ ፕላናቸውን አቅርበው ውጤት በመስማት አዲሱን የምርጫ ውጤት ዛሬ የሚታወቅ ይሆናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደንረ ብርሃን⬆️የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች በደብረ ብርሃን ከተማ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብን⬆️የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ በከሚሴ፣ ደብረሲና፣ ሸዋሮቢት፣ በቢቻና እና በሌሎችም ቦታዎች ዛሬ ህዝባዊ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
*አስቸኳይ የሰብዓዊነት ተግባር ላይ ይሳተፉ*

(ሼር ይደረግ!)

ከቤኒሻንጉል #ለተፈናቀሉ ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በህይወት ለመድረስ የአዲስ አበባ እና የአካባቢው ነዋሪዎች የእርዳታ ማስተባበሪያ መርሐ ግብር በመልካም ሁኔታ እየሔደ ነው።

የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ መስከረም 28 እና 29 በሀገር ፍቅር ቴአትር ከሚሰበሰበው እርዳታ #በተጨማሪ ቅዳሜና እሁድ ብቻ ለሚመቻቸው ወገኖቻችን ከዚህ በታች ባሉ ግዚያዊ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ያዘጋጃችሁትን እርዳታ እያስመዘገባችሁ መለገስ ትችላላችሁ።

ለማስታወስ ያህልም የእርዳታ አይነቶቹን በድጋሚ እናስታውቃለን።

#የማይበላሹ_ምግቦች
መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች
ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት
ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ
የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)
በመሆኑም ከዚህ በታች በተቀመጡት ተጨማሪ አድራሻዎች ቅዳሜና እሁድን ብቻ የቻሉትን በአቅራቢያዎ መለገስ ይችላሉ።

🔹ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ ~0911219235 ቦሌ ኤድና ሞል ዝቅ ብሎ ምስራቅ በር ስጋ ቤት @Blen Sahlu

🔹ኮልፌ እና 18 ማዞሪያ ፍቅሩ አብጤ +251911319571

🔹ሰባተኛ የአማኑኤል ታክሲ መያዣ 0911793475 ደንበል ጀርባ ከ ላፓሪዝያን ፊት ለፊት ሶሎሞን ሞባይል +251912634363 @Solomon Mengesha

🔹ፒያሳ ማስታወቂያ ሚንስቴር አካባቢ ተስፋዬ ለማ ~+251912914748
ለበለጠ መረጃ መሐመድ ካሳ ወይንም ያሬድ ሹመቴን በ0930 36 52 44 ማግኘት ይችላሉ።

ጫካ ያደሩ ህፃናትና እናቶች፤ አረጋውያንና ደካሞች ከምንም በላይ "የኢትዮጵያዊያን ያለህ!" እያሉ ነው።

#ሰብዓዊነት_ይቅደም !!

(ከአንድ ግዜ በላይ ሼር በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ!)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia