TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ብናልፍ_አንዱዓለም እንደገለጹት ብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት #በባሕር_ዳር ከተማ ያካሂዳል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሞተራይዝድ ዊልቼር በመስቀል በዓል #በስጦታነት አበርክተዋል።

Source:-Fitsum Arega,Chief of Staff, Prime Minister's Office - FDRE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰው ክቡር ነው! #ፈጣሪን ካከበርክ ሰውን #ታከበራለህ። ሰውን ስታከብር ብሄሩን፣ ማንነቱ፣ ቋንቋውን፣ ባህሉን እና ሀሳቡን እንዲሁም የኔ መገለጫ ነው የሚለው ነገር ሁሉ ታከብራለህ። የቱንም ያህል #ልዩነት ቢኖር #ሰውነት ሁሉንም ልዩነት ባዶ ያደርገዋል። ሰውነት #ይቅደም! ሰው እንደሰው ከተከበረ የሰውየው የሆኑ ነገሮች ሁሉ ይከበራሉ። አክቲቪስት ነን ባዮች፤ ፖለቲከኞችም ጭምር በዚህ ወቅት ከምንም ነገር በፊት ለወጣቱ ልታስተምሩት የሚገባው ስለሰው ክቡርነት መሆን አለበት። ሰው ሲከበር #ግጭት አይኖርም፤ ሰው ሲከበር ጥላቻና ክፋት አይኖርም! ሰው መሆን ይከበር!
.
.
#ETHIOPIA
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍል 2-ኃላፊነት የጎደለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከፍለው ዋጋ!

ማኅበራዊ ሚዲያ በኢትዮጵያ፦

በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው የኢንተርኔት ተደራሽነትና የስማርት ሞባይል ስልኮች መስፋፋት ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዕድገት እንዲኖር አድርጓል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ እንደሚያሳየው፣ አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 67.5 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 65.7 ሚሊዮን የሚሆኑት የሞባይል ተጠቃሚ ናቸው፡፡ 17.8 ሚሊዮን ደግሞ የኢንተርኔትና የዳታ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 1.2 ሚሊዮን የመደበኛ ስልክ ደንበኞች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የስማርት ስልኮች ተጠቃሚነት ከዓለማችን የመጨረሻው ቢሆንም (ከአጠቃላይ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች አራት በመቶው ብቻ የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ናቸው)፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ ነው፡፡ ሆኖም ከዓለም አንፃር አናሳ ነው፡፡

ኩዋርትዝ አፍሪካ በየካቲት ወር 2010 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አጠቃላይ የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር ብዙ ቢሆንም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ግን ከአራት ሚሊዮን አይበልጥም፡፡ ይሁንና እያደገ በመጣው የተጠቃሚዎች ዕድገት በመሳብ ግለሰቦችም ሆኑ የመንግሥትና የግል ተቋማት ማኅበራዊ ሚዲያ ወደ መጠቀም አዘንብለዋል፡፡ በዚህም በአነስተኛ ወጪ መረጃዎችን ለበርካቶች ተደራሽ ያደርጋሉ፡፡

በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከሚውሉ የማኅበራዊ ሚዲያዎች በቀዳሚነት የሚነሳው ፌስቡክ ሲሆን፣ 93.7 በመቶ የሚሆነው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የፌስቡክ ተጠቃሚ ነው፡፡ በመቀጠል ዩቲዩብ፣ ፒንተረስት፣ ትዊተር፣ ጉግል ፕላስና ሊንክደን ይከተላሉ፡፡

በዓለም እንደሚታየው ሁሉ የማኅበራዊ ሚዲያው በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ በኢትዮጵያም ራሱን እየገለጠ ነው፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያን ሥራቸውን ለማስተዋወቅ፣ ጠቃሚ ማረጃዎችን ለማቀበል፣ ለማዝናናት፣ አገራቸውንና አካባቢያቸውን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙበት እንዳሉ ሁሉ፣ የጥላቻ መልዕክቶችን ለማሠራጨት፣ #ዘረኝነትን ለመስበክ፣ ሃይማኖትና ብሔርን #ለማንቋሸሽ#ለመሳደብና #ለፀብ ለማነሳሳት የሚጠቀሙበት ትንሽ አይደሉም፡፡ ፌስቡክና የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰጡትን ሐሳብን ያለገደብ የመግለጽ መብት በመጠቀም፣ የአንድ ወገን በደሎችን ብቻ የሚያጎሉ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ሳይታክቱ የሚሠሩ በርካቶች ናቸው፡፡

በርካታ ተከታዮች ኖረዋቸው ለእነዚህ ተከታዮቻቸው ለፀብ የሚያነሳሱ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች፣ እነዚህ መልዕክቶቻቸው የሚያደርሷቸው ጥፋቶች እነርሱ ላይ ጉዳት ስለማያስከትሉ ሰዎች እየሞቱ፣ ንብረቶች እየወደሙና በርካቶች ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉ በምቾት የጥፋት ሥራዎቻቸውን ያከናውናሉ፡፡

ይኼንን በማድረጋቸውም ለማኅበረሰብ መብት ተቆርቋሪ ተደርገው ይቆጠራሉ፣ የነፃ አውጪነትን ማዕረግን ይሸለማሉ፡፡ ይህ በተለይ የፖለቲካ አክቲቪስት ነን በማለት ጎራ ለይተው የቃላት ጦርነት እያደረጉ፣ በአካል ጦርነቶችን በማነሳሳት የሚሠሩ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ተጠቃሚዎች ላይ በጉልህ ይታያል፡፡ በአንዱ ጎራ የእኔ ብሔር ተጠቃ አጥቂውም የእገሌ ብሔር ነው እያሉ ጣት ሲቀሳሰሩ፣ ለበርካታ ዓመታት ተዋልዶና ተፋቅሮ በኖረ ማኅበረሰብ ዘንድ ጠላትነትን ይዘራሉ፡፡ ይህ ድርጊት የማይናማር ቢን ላዲን የተባለን ግለሰብ በደቡብ ምሥራቅ እስያ እንደፈጠረ ሁሉ፣ ተመሳሳይ አዛሳኝ ታሪክ በኢትዮጵያ ሊደገም እንደማይቻል ምንም ማስተማመኛ እንደሌለ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ከልማታቸው እኩል ለዴሞክራሲና እንደ መናገር ላሉ መርሆች ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ዕሙን እንደሆነ ባለሙያዎች ቢስማሙም፣ ከሰላም የሚበልጥ የለምና የሕዝቦችን አብሮ የመኖርና ሰላም የሚያደፈርስ ጉዳይ ከተከሰተ መላ ሊባልና ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚያስፈልግ ያትታሉ፡፡

የክፋት ዓላማ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ባገኙት አጋጣሚ ፍርኃትን በመንዛት ከፍተኛ ጥፋት ለመፍጠር የሚችል የጥፋት ሠራዊት እንደሚገነቡ፣ ዴሞክራሲን ፈተና ላይ ሊጥሉ እንደሚችሉ የማኅበራዊ ሚዲያ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ክፉ ሐሳብ ያላቸው ተጠቃሚዎች ደግሞ የሕግ፣ የሥነ ምግባር ወይም የሞራል ተጠያቂነት ስለሌላቸው ያለ ገደብ የበላይነታቸውን ይዘው ሁሉንም ለግል ጥቅማቸው ሲሉ እንደሚያደርጉም ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ለኢትዮጵያም ሊሠራ የሚችል ነው፡፡
.
.
ክፍል 3 ይቀጥላል🔄

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ደመራ ከማብራት ስነ ስርዓት ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ምንም አይነት የእሳት አደጋ #እንዳልተከሰተ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላለከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ገልጿል።

©ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETV Zena Live! የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ 12ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

📌የድርጅቱ ጉባኤ ‹‹የለውጡ ቀጣይነት ለአማራ ህዝቦች ተጠቃሚነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነት›› በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍል 3-ኃላፊነት የጎደለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከፍለው ዋጋ!

ፈተናዎችና መፍትሔዎች፦

እንዲህ ዓይነት ጥፋቶችን ለመከላከል ሲሉ እንደ ፌስቡክ ያሉ የማኅበራዊ ሚዲያ ተቋማት የጥላቻ መልዕክቶችን፣ ሰቅጣጭ ምሥሎችንና የሐሰት መረጃዎችን ለመለየትና ለማጥፋት የሚያስችሏቸውን መፍትሔዎች አስቀምጠዋል፡፡ የመጀመርያው በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (በሮቦት) የታገዘ የልየታና የማስወገድ ሥራ ነው፡፡ ይህ በዋናነት ለእንግሊዝኛና ለአውሮፓ ቋንቋዎች በብቃት የሚሠራ ውጤታማ መፍትሔ ሲሆን፣ ለበርማና አማርኛን ለመሳሰሉ ቋንቋዎች መፍትሔ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ፕሮግራም የተደረጉ ሮቦቶች በቋንቋዎቹ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ባህርያትንና ትርጉሞችን የመለየት ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ ስለዚህ በሁለተኛ አማራጭነት የተቀመጠው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ተጠቅሞ ማጣራት ነው፡፡ ተጠቃሚዎች የሚያጋጥሟቸውን ያልተገቡ ይዘቶች ለሚመለከታቸው በመጠቆም ዕርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ነው፡፡

በሦስተኛ ደረጃ ቁጭ ብለው የሚለዩ ባለሙያዎችን መጠቀም ነው፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተቀጥረው የሚቀመጡ ሰዎች በየቋንቋዎቻቸው እየገቡ የሚያገኟቸውን ያልተገቡ መልዕክቶች ያስወግዳሉ፡፡ ነገር ግን ይህ በበቂ የሰው ኃይል ስለማይሠራ ውጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው በማይናማር ያ ሁሉ እልቂት እየተፈጸመ ፌስቡክ የነበሩት ስድስት በማይናማር ቋንቋ የሚሠሩ የልየታ ሠራተኞች ብቻ መሆናቸውና የጥላቻ መልዕክት የሚያስተላልፉትን መነኩሴ ገጽ ለመዝጋት መለሳለስ ማሳያታቸው ነው፡፡

የተጠቃሚዎች ሚና

የፌስቡክም ሆነ የተለያዩ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ተጠቃሚዎች፣ እነዚህን ገጾች በሚጠቀሙበት ወቅት በራሳቸው ጽሑፎችም ሆነ ከሌሎች ወስደው በሚያጋሯቸው ጽሑፎች ውስጥ ያሉ የጥላቻ መልዕክትና የተለያዩ የጥፋት ይዘቶችን በመለየት ከጥፋት የመከላከል ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በርካታ ተጠቃሚዎች ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ለበጎ ዓላማ ለማዋል ቢያሰጡም፣ ቢጀምሩም፣ ከፍተኛ ተፅዕኖ ባላቸው ተጠቃሚዎች ሊጠለፉ ስለሚችሉም ጥንቃቄ በማድረግና በጎ ተፅዕኖ ከሚፈጥሩ ግለሰቦችና ከሚያውቋቸው ጋር ትስስርን እንዲፈጥሩ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ያሳስባሉ፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ዋጋቸው አነስተኛ በሆኑ ስማርት ስልኮች አማካይነት ይበልጥ ስለሚስፋፋም በጎ ዓላማ ያላቸው ተጠቃሚዎች ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸውን እያጎሉ እንዲመጡ አጥኚዎች ይመክራሉ፡፡

#የመንግሥት_ኃላፊነት

ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ የመንግሥት የመጀመርያው ተግባር የዜጎቹን የደኅንነት ማስጠበቅ ነው፡፡ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል የትኛውም ሥጋት ሊወገድ ይገባል ይላሉ፣ ማኅበራዊ ሚዲያም ቢሆን፡፡ ከዚህ በተቃራኒ የሚቆሙ አካላት ደግሞ መንግሥት የዜጎችን ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ከማፈን ይልቅ፣ ኅብረተሰቡን ማስተማር ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት፣ ማኅበራዊ ሚዲያውንም ሆነ ኢንተርኔት መዝጋት ከቴክኖሎጂ ጋር የሚደረግ ትግል ስለሆነ በድል የሚወጡት ጦርነት አይደለም ይላሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን በመጡበት ሰሞን ከመከላከያ ከፍተኛ መኰንኖች ጋር በነበራቸው ውይይት፣ አንድ አሜሪካ ባለ አንድ ፌስቡክ ያለ ተቋም አማካይነት የአገር ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ይወድቃል ብለው ነበር፡፡ ስለዚህም የመከላከያ ኃይሉ የአገር ሉዓላዊነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ክስተቶችን የማስቆም አቅሙ ማደግ አለበት፡፡ ይህ ግን እንደ ባለሙያዎች ዕይታ በሕግ መታገዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ማለት መንግሥት በአገር ውስጥ የሚካሄዱ ጉዳዮችን መቆጣጠር ስለላለበት፣ የሕግ ማዕቀፍ አውጥቶ መድረኮቹ ለበጎ አገልግሎት እንጂ ለጥፋት እንዳይውሉ ማድረግ አለበት፡፡

ከዚህ በዘለለ መንግሥት ቁጥጥሩን ተቋማዊ በማድረግ አገርን ከጥፋት መከላከል አለበት ሲሉም ይመክራሉ፡፡ ለዚህ ተሞክሮ ከግብፅ መውሰድ እንደሚቻልና ግብፅ የፌስቡክ ሚኒስቴር በማቋቋም የቁጥጥር ሥራ እንደምታከናውን ያመለክታሉ፡፡ በዚህም የሐሰት ምሥሎችን በሚለጥፉ፣ የውሸትና የፈጠራ ወሬዎችን በሚያሠራጩና ጥፋትን በሚያነሳሱ ላይ ዕርምጃ መውሰድ እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀረር⬇️

በሐረር ከተማ የሚስተዋለውን #የቆሻሻ ክምችት በሚቀጥሉት ጥቂት ጊዜያት ውስጥ በዘላቂነት ለመቅረፍ እንደሚሰራ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የጤናው ዘርፍ የ2010 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል፡፡

በአጠቃላይ በቀረበው ሪፖርት ላይ ለጤና ልማት ሰራዊት ግንባታ እየተሰጠ ያለው ትኩረት ፣የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ፣ የመድሃኒት እና የደም አቅርቦት አናሳ መሆን እንደ ችግር የተነሱ ሲሆን በተጨማሪም በከተማው የሚስተዋለው የቆሻሻ ክምችት በህብረተሰቡ ጤና ላይ እያስከተለ ያለው የጤና ችግር ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጿል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ እንደተናገሩት በጤናው ዘርፍ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ያለውን የሰው ሀይል በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡

የዘርፉ አመራር ለስራው የሚሰጠውን ትኩረት ሊያጠናክር እንደሚገባ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ በተሠጠው ስራ ልክ የሚመዘን እና
ተጠያቂነትን የሚፈጥር ስርዓትን መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በከተማው የሚስተዋለው የቆሻሻ ክምችት በዘላቂነት ለመቅረፍ በሚቀጥሉት ጥቂት ጊዜያት ይሰራልም ብለዋል፡፡

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ገቢሳ ተስፋዮ በበኩላቸው የእናቶች እና የህጻናት ሞትን ለመቀነስ በጤና ተቋማት እንዲወልዱ ከማድረግ አንጻር በቂ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
ለዘርፉ ውጤታማነት ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም አክለው ገልፀዋል፡፡

ከደም አቅርቦት ጋር በተያያዘ የክልሉ ደም ባንክ ኃላፊ ወ/ሮ አረፋት ማህዲ በበኩላቸው የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አናሳ መሆኑን ገልፀው በበጀት አመቱ የተፈጠረውን እጥረት ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በበጀት አመቱ መልካም አፈጻጸም ላስመዘገቡ አላካላት የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሐረሪ ክልል በቄሮና በፋኖ ስም ተደረጅተው ህገ-ወጥ ተግባራትን የሚፈፅሙ አካላት ከድርጊታቸው #እዲቆጠቡ የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬇️

የብአዴን ሊቀመንበርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በብአዴን 12ኛው የመክፈቻ ንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች፦

o ብአዴን ይህን ጉባኤ በሚያካሂድበት ታሪካዊ ወቅት ሲደርስ የማይታለፉ ይመስሉ የነበሩትን ችግሮች እያለፈ ዛሬ ድረስ ዘልቋል፡፡

o ብአዴን ህዝብና አገርን የመታደግ ልምድ አለው፣አሁን ለመጣው የለውጥ ሂደት የነበረው ድርሻ ጉልሀ ነው፡፡

o የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያ ስትጀመር አብረን ጀምረናል ፣ኢትዮጵያ የምትባል ታላቅ አገር መገንባታችን ያኮራናል፣የደሃ አገር ባለቤት መሆናችን ያሳፍረናል፣ ከድህነታችን ጋር ትግል መጀመራችን ያፅናናል ፣የጀመርነው የለውጥ ጉዞ በትልቅ መስዋዕትነት የመጣ ለቀጣይነቱም ቁርጠኝነት ብአዴን ያለሰለሰ ጥረት ያርጋል፡፡

o አካሄዳችን ከይል ይልቅ በሀሳብ አሳማኝ በሆነ መልኩ እንዲሆን አድርጎ በአዴን ይጓዛል፡፡

o ድህነትንና ኃላ ቀርነትን ከማንነት ጋር አስተሳስሮ ወቅቱ የሚጠይቀውን ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግ ጊዜ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው፡፡

o ዛሬም ሀገራችን በሁለት ፅንፈኛ አመለካከቶች ውስጥ ትገኛለች ብሔረሰባዊ ማንነትን ከሌሎች መነጠያ በማድረግ እደረሰ ያለውን ፈተና፣ ብሄረሰባዊ ማንነት በፅንፈኝነት በሚቀነቀንበት በአሁኑ ጊዜ መገኘታችን የአማራ ህዝብ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ተከባብሮ የመኖር ባህሉን በማክበር ለመምራት በአዴን በጠራ አቋም ላይ ይገኛል፡፡

o የአማራ ህዝብ እኔን መስሎ ይወጣልኛል በሚል በብአዴን ተስፋ ጥሎበት ጉባኤያችንን እየጠበቀ ነው፡፡

o አባላቱም ይህን የአማራ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሌት ተቀን መታተር ይጠይቃል፡፡

o 12ኛው ጉባኤችን ያለፉትን የ38 ዓመት ታሪኩን በማጤን በአዲስ ምዕራፍ ላይ በመገኘት ለአማራ ህዝቦች ጥያቄ ለማስራት መልካም አጋጣሚ የሚፈጠርበት መድረክ ነው፡፡

o የህዝባችን ጥያቄ እንዲመለስ ካስፈለገ ከመጠላላት ይልቅ በመተባበር ወደፊት በጋራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

o ስልጣንን ለቡድናዊ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚሹ ወገኖች እንደማይተኙ በማጤን ወደፊት በለውጥ መንፈስ ውስጥ መገስገስ ያስፈልጋል፡፡

o ጥሪ ተደርጎላችሁ ወደ አገር ውስጥ የገባችሁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት አቅጣጫችሁ ወዲፊት በመጓዝ ይሁን፡፡

o የለዉጡ መሰረት ውስጣዊ በመሆኑ አፍርሶ መስራት አይሻም፣ከስኬትም ከውድቀትም ትምህርት መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡

o የምንሮጠው ሩጫ ከችግሮቻችን አቅም በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

o ብአዴን ለውጡን ማስቀመል በአዳዲስ ኃይል የተገነባ አመራር ያስፈልገዋል፡፡

o መድረኩ የታሰበውን ለውጥ እንዲያመጣ ሁለችሁም የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ፡፡

o ልንሰራ ሲገባን ያልሰራናቸው ስራዎች የስራ እድል ፈጣራ፣ የዲሞክራሲ ፍኖትን ማስፋት፣ አስተማማኝ ሰላምን ማስፈን፣ መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ ህዝባች በጉጉት እየጠበቃቸው ያሉ የዛሬ አጀንዳዎች ናቸው፡፡

o እዚህም እዚያም የምናያቸው ችግሮች የአዲሱና የአሮጌው ማንነታችን የርስ በርስ ፍልሚያ ውጤት ነው አዲሱ ማሸነፉ አይቀሬ ነው፡፡

o የለውጡን ጥሪ ተቀብለው ለመጡና ለሌሎች የውስጥ ኃይሎች ሩጫቸው ወደፊት ይሁን ወደፊት መሮጥን መንገድ ይቀንሳል፡፡

o ጉባዔው ለውጡን በአጥጋቢ ሁኔታ ማስቀጠል የሚችሉ አመራሮች መምረጥ መቻል ይኖርበታል።

o ብአዴን የለውጡ መሪ ሆኖ የሚወጣበትና የአስተሳሰብ አንድነት የምንገነባት መድረክ ሆኖ እንደሚጠናቀቅ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጊምቢቹ⬆️

"ትላንት ረቡዕ ምሽት በጊምቢቹ (ከሆሳዕና 32 ኪሜ) እና አካባቢዎች ባሉ ቦታዎች በጣለው ከፍተኛ ዝናብ እና በረዶ ምክንያት አካባቢው በበረዶ ተሸፍኗል። Dagi ነኝ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia