TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሲዳማ ዞን አስተዳደር⬇️

የዞናችን ሕዝቦች ከዚህ እንደቀደመው ሁሉ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ነቅቶ እንዲጠብቅና ለረጅም ዓመታት ያጎለበተውን እንግዳ ተቀባይነት ባህሉን እንዲያሳይ የሲዳማ ዞን አስተዳደር አሳሰበ።

እንደሚታወቀው ከፊታችን መስከረም 18-21/2011 ዓ.ም የዴኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ እና ከመስከረም 23-25/2011 ዓ.ም የኢህአዴግ ድርጅታዊ #ጉባዔ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል። በእነዚህ ጉባኤዎች የጉባኤ ተሳታፊ እንግዶች ፣ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ከሀገር ውስጥና ውጭ ታላላቅ ሚዲያዎች የሚታደሙበት ጉባዔ በመሆኑ እንግዶችን ለመቀበል የሲዳማ ዞንና #የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል በሀገራችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ተስፋ ሰጪና የመላው ዞናችን ሕዝብ #ተስፋ ያለመለመ በመሆኑ ሕዝባችንን ከለውጡ ጎን እንዲሰለፍ አስችሏል። ይህ የለውጥ ህደት ያልተመቻቸው እየፈነጠቀ ያለውን የተስፋ ብርሃን ለማጨለም በተለያዩ ጊዜያት በዞናችንም ሆነ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በለውጥ #አደናቃፊ ኃይሎች የተቀነባበረው ትንኮሳና መሰሪ ዓላማቸው በፀጥታ ኃይሉና በሕዝባችን ብርታት
እየመከነ በዞናችን ውስጥ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር መቻሉ አንዱ ማሳያ ነው።

ጉባዔዎቹ #በሰላም መጠናቀቅ የሕዝባችንን ሰላም ወዳድነቱን፣ እንግዳ ተቀባይነቱን ከማጉላት ባሻገር የሲዳማ ሕዝብ ለጠየቀው ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኝና በሀገራችንም የተጀመረው የለውጥ ጅማሮን ለማስቀጠል ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም አልፎ አልፎ የለውጥ አደናቃፊ ኃይሎች በኀብረተ ሰቡ ውስጥ ስጋት ለመፍጠር በሚያደርጉት ትንኮሳ ሳይደናበር መላው ሕዝባችን ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እኩይ ዓላማቸውን እንዲያመክንና ለጉባዔው በሰላም መጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የሲዳማ ዞን አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል።

መስከረም,16/2011 ዓ.ም
ሀዋሳ,ሲዳማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia