TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ⬇️

"ጸግሽ....ዛሬ registrar ገብቼ ከregistrar ኃላፊዋ ከጥሩ ወርቅ ጋር ተነጋግሬ ነበር። እናም አርብ ማለትም መስከረም 18 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጠርቷል የተባለው ምዝገባ የማስተርስ ሲሆን የunder graduate ምዝገባ ግን በትምህርት ሚኒስትር ፕሮግራም መሠረት ጥቅምት መጀመሪያ አካባቢ እንደሆነ ለማወቅ ችያለሁ!! ትክክለኛው ቀን ግን በማስታወቂያ እንደሚገለጽ ነግራኛለች።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Very_Urgent

ለ2011 ዓ.ም ለስፔሻላይዜሽን ትምህርት በአዲስ አበባ ዪኒበርስቲ በPediatric and Child Health የተመደባችሁ September 28 ይሰጥ የነበረዉ Online Competency Exam ጥር ወር ላይ ከሌሎች ትምህርት ክፍል ሪዝደንቶች ጋር የሚሰጥ መሆኑን የዩኒበርስቲዉ Academic Affairs Director ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ዶክተር ጋሻው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአአዩ ተማሪዎች ተወካይ⬇️

"ጁሀር ሱልጣን እባላለሁ የአአዩ የተማሪዎች ተወካይ ነኝ! አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በሚመለከት ያልከው መረጃ ትክክለኛ ስለመሆኑ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን በሚመለከት ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያሳውቃል፡፡ Most probably ከወርሀ-ጥቅምት መጀመሪያ በፊት ተማሪዎች እንደማይገቡም ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዉልኛል። አመሰግናለሁ! ጁሃር ሱ."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚዘጉ መንገዶች⬇️

የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር #አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራ መግባቱን – የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽን ኮሚሽነር #ደግፌ_በዲ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች፣ የመንግስት ባለስልጣናት የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ፓሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ኮሚሽኑ ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከእምነቱ ተቋም ጋር #በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡

ህብረተሰቡ እንደዚህ ቀደሙ የዘንድሮ የመስቀል በዓለል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን #ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ የበዓሉ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖርና ወደ በዓሉ አዋኪ ነገሮችን ይዞ መምጣት እንደማያስፈልግ የገለፁ ሲሆን፥ ለዚህም የህብረተሰቡ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ ፕሮግራም ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሚዘጉ መንገዶች
የሚከተሉት ናቸው፦

▪️ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎፒያ

▪️ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው
መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ

▪️ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር መታጠፊያ

▪️ከቸርችር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
ከተክለ ሀይማኖት ፣ ጥቁር አንበሳ ፣ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

▪️ከተክለ ሀይማኖት፣ በሜትሮሎጂ ፣ጥቁር አንበሳ፣ ኢ.ቢ.ሲ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት በር

▪️ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
ከሳሪስ፣ በጎተራ ፣ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ መሾለኪያ

▪️ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር ጉምሩክ አካባቢ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች መንገዶቹ ዝግ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በአመራጭነትም የሚከተሉትን መንገዶች መጠቀም እንደሚቻልም ተገልጿል።

▪️ከቦሌ በመስቀል አደባባይ ወደ 4ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ ቦሌ- ወሎ ሰፈር- ኦሎፒያ- ኡራኤል- ካሳንችስ-አራት ኪሎ

▪️ከቦሌ ፣ በመስቀል አደባባይ ወደ ጦር ኃይሎች መሄድ የሚፈልጉ ቦሌ- ወሎ ሰፈር- ጎተራ ቀለበት መንገድ – ቄራ – ሳር ትንባሆ ሞኖፖል- ሜክሲኮ አደባባይ- ጦር ኃይሎች

▪️ከሜክሲኮ፣ በለገሃር ፣ በመስቀል አደባባይ ወደ 22 መገናኛ መሄድ የሚፈልጉ ሜክሲኮ አደባባይ- ዲአፍሪክ ሆቴል ሳር ቤት ብሄራዊ ቲያትር- ኢትዮጵያ ሆቴል – ፍል ውሃ – ብሄራዊ ቤተ-መንግስት- ካሳንቺስ- ኡራኤል– በ22 መገናኛ

▪️ከሜክሲኮ በለገሃር በአዲስ አበባ ስታዲዬም መሄድ የሚፈልጉ በለሃር መብራት – በአዲሱ ቂርቆስ መንገድ – ርቼ – በቅሎቤት-ጎተራ ወይም
በለሃር መብራት – በአዲሱ ቂርቆስ መንገድ – ጎፋ ማዞሪያ – ጎተራ

▪️ከፒያሳ ፣ በአምባሳደር ፣ ጊዮን ሆቴል ወደ ጎተራ መሄድ የሚፈልጉ አምባሳደር ቲያትር- ፍል ውሃ- ካሳንቺስ- ኡራኤል ቤ/ክር-አትላስ ሆቴል- ወሎ ሰፈር ጎተራ መሆናቸው ታውቋል።

ጥቆማ ለመስጠትም የሚያስችሉ ስልክ ቁጥሮች . 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም፦

011- 1 -11- 01 – 11 ፣
011- 1- 26- 43- 59 ፣
011- 1- 01- 02- 97፣
011-8-69-88-23 ፣ 011-8-69-90-15 ፣ 011-5-54-36-81 ፣ 011-5-54 -36-78 ፣ 011-5-54 -38 -04 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ⬇️

ማስታወቂያ!

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2011 የትምህርት ዘመን የነባር የቅድመና ድህረ-ምረቃ እንዲሁም የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 1-3/2011 ዓ/ም መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዘገባ ጊዜ ወደፊት የሚገለፅ መሆኑን እያሳወቀ በዩኒቨርሲቲው የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ መረጃ በዩነቨርሲቲው ፌስቡክና ድረ-ገፅ ላይ እንድትከታተሉ ያሳስባል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከምዝገባው ቀን ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድና ማንኛውንም አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን በአፅንዖት ይገልፃል፡፡

ምንጭ፦ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስቸኳይ‼️በሰኔ እና በሐምሌ ወር 2010 ዓ.ም መጨረሻ ከተለያዩ የከፍተኛ የመንግሥት ትምህርት ተቋማት #በጤና ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች የምደባ ፕሮግራም!

©የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናትን ዩኒቨርሲቲው ይፋ አድርጓል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

16ኛዉ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት #መክፈቻ በተለያዩ ስነስርዓቶች ተከብሯል፡፡ በስነስርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ እና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች፣ አትሌቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል አባላት ተገኝተዋል፡፡ በተግባሩ የተሻለ እንቅስቃሴ የነበራቸዉ አካላት የማበረታቻ ሽልማትና ስርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ⬆️በዩኒቨርሲቲው ተፈትናችሁ ስማችሁ በድህረ ገፅ ያልወጣላችሁ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ባሉ ጥቂት ቦታዎች ማመልከት ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ አህመድ ሽዴ⬇️

በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ የተሳሳተ መሆኑንና ህብረተሰቡን ለማደናገር የሚሰራ ስራ እንደሆነ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ #አህመድ_ሽዴ
አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

መንግስት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከመስከረም 2 ጀምሮ የፖለቲካ ኃይሎችን ለመቀበል በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ያልተገባ #ፉክክር ግጭቶች መፈጠራቸውን አስታውሰዋል።

እየሰፋ ቤደው ግጭትም በቡራዩ 27 ሰዎች በአዲስ አበባ 28 በጥቅሉ 55 ሰዎች #ህይወታቸው እንዳለፈ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በቡራዩ ከተማ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመና 3 ሺህ 50 ሰዎችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

እነዚህን ግጭቶች የብሄር ማስመሰልና በማህበራዊና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ ግጭቱን ለማባባስ እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ከግጭቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው 170 ሰዎችና በቡራዩ ከተማ ደግሞ 390 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ሁከቱና ብጥብጡን ለማማባባስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ 1200 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ችግሩን ለመቆጣጠር የፍትህና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ችግሩ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል።

#መንግስት በደረሰው የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የተሰማውን #ሀዘን ሚኒስትሩ ገለፀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹መልዕክት ለዳያስፓራ!!
የRingAround Appን በስልካችሁ ላይ ቶሎ በመጫን ወደ ሀገር ቤት ይደውሉ!

ለመጫን
https://ringaround.lpages.co/et-tikvah-downloadringaroundapp

ነፃ! ነፃ! ነፃ!😱😱😱
ዛሬውኑ ሲጭኑት
በሰሜን አሜሪካ $2 የመደወያ ዶላርን በነፃ እንሰጣለን!
በአውሮፓና በአውስትራልያ $1 የመደወያ ዶላርን በነፃ እንሰጣለን!

ይሞክሩን
https://ringaround.lpages.co/et-tikvah-downloadringaroundapp


በተጨማሪ፦ @RobelTDesta
#update የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዥ ትላንት በኒው ዮርክ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን የደርጅቱ ቃል አቀባይ አስታወቁ።

ዋና ጸሐፊ ጉተሬዥ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በዚሁ በውይይታቸው በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀንድ እየተካሄዱ ስላሉ አዎንታዊ ለውጦችና በአካባቢው የቀሩትን ፈታኝ ችግሮች ማስወገድ በሚቻሉባቸው መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል። በቅርቡ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የሰላም ሥምምነት መፈረሙን በደስታ እንደተቀበሉት ገልፀው ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ጠቃሚ ነው ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ የዓለሙ ድርጅት ለእነዚህ በጎ ጥረቶችና ኢትዮጵያ በጂቡቲና ኤርትራ መካከል የሰላም ንግግር እንዲጀመር በማመቻቸቷ ሙሉ ድጋፍ እንደሚስጥ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም. የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናትን ዩኒቨርሲቲው ይፋ አድርጓል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋን ኦሮሞ📌የ5 ኛ ቀን የአፋን ኦሮሞ ትምህርት በ @tikvahethedu ተከታተሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
AASTU⬇️

"Hi tsegab I would like to tell u that the registration date for AASTU students October 1&2 posted in some other social media is false i will tell u the exact date when i receive the message from registrar thank u!!"

የተማሪዎች ተወካይ‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia