TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢህአፓ⬆️

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮች ከ40 አመታት በላይ የውጪ አገር ቆይታ በኋላ #ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በውጪ ያሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር ግንባታ ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይህን ጥሪ ተከትሎ ነው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ከደርግ ዘመን ጊዜ ጀምሮ ከነበራቸው የብዙ አመት የውጪ ቆይታ በኋላ ዛሬ ወደ አገር ቤት የገቡት።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ በላይነህ ንጋቱ፣ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሃመድ ጀሚል እና ኢንጂነር ሰለሞን ገብረስላሴን የያዘ ከፍተኛ አመራር አባላት ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ተቀብለዋቸዋል።

ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ንጋቱ እንዳሉት፤ ፓርቲው በአገሪቱ አሁን የተጀመረውን ለውጥ መሰረት እንዲይዝ የሚችለውን ያደርጋል።

በተፈጠረው እድል ህጋዊ ሆኖ ለመንቀሳቀስ ፓርቲው ዝግጁ መሆኑን የገለፁት ሊቀመንበሩ ከአሁኑ የለውጥ አመራር ጎን በመሆን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር #በትጋት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ሚናቸውን በአግባቡ ለመወጣትም ከቀድሞ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ከወጣቱ ጋር የጋራ ምክክር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

የህግ የበላይነት እንዲከበርና ዴሞክራሲ የበለጠ እንዲሰፋ ፓርቲያቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር #ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የፓርቲው አመራሮች ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥና ሻማ የማብራት ስርዓት ያከናውናሉ ተብሏል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቡራዩ⬇️

"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ...በቡራዩ ነው የምኖረው እና በቀደም ተፈጥሮ በነበረው አላስፈላጊ ድርጊት ለይ ተሰማርተው የነበሩ በርካታ ሰዎች እየተያዙ ነው በተለይ በስርቆት ለይ ተሰማርተው የነበሩ ከነሰረቁት እቃ በቡራዩ ቄሮ ወጣቶች እና በኦሮሚያ ፓሊስ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች መግቢያ ጥቅምት 01 እና 02 ሲሆን የአዲስ ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደሴ⬆️የአርበኞች ግንባር 7 ንቅናቄ አመራሮች በደሴ ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

©Amir
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ⬆️ለአፋር ህዝብ ፓርቲ ዛሬ በሰመራ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪ ደማቅ አቀባበል አድርጓል። የተደርገው አቀባበልም #በሰላም ተጠናቋል።

በሌላ በኩል...

ዛሬ 9:00 በሰመራ ሉሲ አዳራሽ Dr. Konte Musa የፓርቲው መስራች እና ሊቀመንበር ከህዝቡ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።

©Samarians ከሰመራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቡራዩ⬆️

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከነዋሪዎቹ ጋር #የሰላም እና #የልማት ዉይይት እያካሄደ ነዉ። ከቀናት በፊት በከተማዋ ተከስቶ የነበረዉን #አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ ከአገር የሽማግሌዎች፤ ወጣቶች ከተለያዩ አደረጃጀቶች ከተወከሉ ነዋሪዎች ጋር በዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ ምክክር እየተካሄደ ነዉ። የከተማዋ ከንቲባ አቶ #ሰለሞን_ፈየ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና የዜጎች ተዘዋዉሮ መስራት እና መኖር መብት እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና⬆️ከ1997 ጀምሮ ታጥረው የቆዩ 154 ቦታዎች በካሬ 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ የሊዝ ውላቸው #ተቋርጦ ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ግዜ ታጥረው የተቀመጡ በመንግስት፣ በግል ባለሀብቶችና በተለያዩ የዲፕሎማቲክ ተቁዋማት ተይዘው የነበሩ አጠቃላይ ስፋታቸው 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ መሬቶች የሊዝ ውላቸው ተቁዋርጦ ተመላሽ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላለፈ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ ከካቢኔ አባላት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ነው ውሳኔውን ያስተላለፉት።

በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግስት የተያዙ 11 ቦታዎችን። ጨምሮ በድምሩ 154 በተለያዩ የከተማዋ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቦታዎች ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ ይደረጋሉ።

ቦታዎቹ በዝርዝርም:-

1, ከግል ባለሀብቶች 95 ቦታዎችን በካሬ 456,428.00/ አራት መቶ ሀምሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ ስምንት ካሬ/

2, ከመንግስት መስሪያ ቤቶች 19 ቦታዎችን በካሬ 127,140.93/ አንድ መቶ ሀያ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አርባ አንድ ካሬ/

3, የሸራተን ማስፋፊያን ጨምሮ ከሚድሮክ ግሩፕ 11 ቦታዎችን በካሬ 549,241.00 /አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ አርባ አንድ ካሬ/

4, ከዲፕሎማቲክ ተቁዋማት 18 ቦታዎችን በካሬ 250,413.89 / ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ አራት መቶ አስራ አራት ካሬ/

5, ከፌደራል ተቁዋማት መከላከያና ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽንን ጨምሮ 11 ቦታዎችን በካሬ 2,743,200.00 / ሁለት ሚሊየን ሰባት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ካሬ ባጠቃላይ 154 ቦታዎች በካሬ 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ የሊዝ ውላቸው
ተቋርጦ ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።

ቦታዎቹ ከ 1997 እስከ 2004 በተለዬዩ ጊዜያት የተላለፉና እስካሁን ምንም አይነት ልማት ሳይከናወንባቸው ታጥረው የተቀመጡ ናቸው።

📌ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ጨምረው እነዚህና መሰል ቦታዎች የከተማዋን ልማት እንዲጓተት ምክንያት እንደሆኑ ጠቅሰው ይህ ስራ የአንድ ጊዜ ዘመቻ ሳይሆን ከዚ በኹዋላ መስተዳድሩ ቦታ ወስደው ወደልማት የማይገቡ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ባለሀብት ላይ ጥብቅ ክትትል አድርጎ #እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል።

©Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ⬆️

"ሀይ ፀግሽ እንዴት ነህ? ከድሬዳዋ ነው የምልክልህ። ከትላንት ጀምሮ #ሳቢያን የተባለ ሰፈር እኛ ወጣቶች በሰፈራችን ከፖሊስ ጋር በመተባበር በበጎ ፈቃደኝነት በመደራጀት የተጠናከረ ጥበቃ እያረግን እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የድሬዳዋ ሳቢያን ፖሊስ ጣቢያ ስላደረጉልን ትልቅ ትብብር ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ። ወጣቱ ላይ ተጨማሪ ተነሳሽነት የሚፈጥር ስራዎች ቢሰሩ ብዙ የሚፈፀመውን እና ሊፈፀም የታሰበውን ወንጀል በጋራ ተከላክለን ሰላም እና ፍቅር የሰፈነባት ድሬዳዋን መፍጠር እንችላለን ብዬ አስባለሁ። አመሰግናለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia