TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የለገሰው 1 ሚሊዮን ብር #ተመላሽ ተደርጓል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲየ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የለገሰው 1 ሚሊየን ብር ከአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመሆን አስፈላጊ የሆኑ #ግዢዎችን ለማድረግ በጋራ እየተሰራ ይገኛል። ቢሮው እጅግ በጣም አንገብጋቢ ናቸው ያላቸውን የሚገዙ ነገሮች ዝርዝር አውጥቶ ከአለ በጅምላ ለመግዛት ዝግጅት ማለቁንም ከያሬድ ሹመቴ ሰምተናል።

የሚገዙት አስፈላጊ ቁሳቁሶችና የእህል አቅርቦቶች በሙሉ ለተገቢው ጥቅም መዋላቸውን በግልጽ ቁጥጥር በማድረግ ላይ የምንገኝን ሲሆን፤ አላስፈላጊ ግዢዎችና #ብክነቶች እንዳይኖሩ በመመካከር በጋራ እየተሰራ ነው።

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቡራዩ ነዋሪዎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ የፀጥታ ሐይል የፈጸመው #ግድያ እንዲመረመር ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀረር⬆️

"ፀግሽ ይህ የምትመለከተው የቆሻሻ ክምር መላ ሐረር ከተማን ላይ ከሶስት ወር በላይ በየአካባቢው በመቆየቱ ከተማዋ ለመጥፎ ሽታ እና ከባድ ጉንፋን መሰል ህመም ህዝቡን እየዳረገ ይገኛል የከተማዋ ማዘጋጃም ሆነ የከተማው አስተዳደርም ይህን ችግር ለመፍታት አልቻሉም። ደረጀ ነኝ ከሐረር"

@tsegabwolde
#update በአዲስ አበባ ከተማ እየተደርገ ያለው ወጣቶችን በቀጥጥር ስር የማዋል እንቅስቃሴ ትላንትም መቀጠሉን ለመስማት ተችሏል። ባለፉት 3 ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተሰምቷል።

ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱኝ አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ⬆️

ለህክምና ፈላጊዎች ጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከኦፕሬሽን ስማይል ጋር በመተባበር ከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ላለባቸው ህፃናት እና አዋቂዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ከጥቅምት 25 እስከ ህዳር 05 ለማድረግ አቅዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
43ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም!
.
.
"ታላቅ ስጦታ የሆነውን ደም እንለግስ፤ ህይወት እናድን"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢህአፓ⬆️

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮች ከ40 አመታት በላይ የውጪ አገር ቆይታ በኋላ #ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በውጪ ያሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር ግንባታ ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይህን ጥሪ ተከትሎ ነው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ከደርግ ዘመን ጊዜ ጀምሮ ከነበራቸው የብዙ አመት የውጪ ቆይታ በኋላ ዛሬ ወደ አገር ቤት የገቡት።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ በላይነህ ንጋቱ፣ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሃመድ ጀሚል እና ኢንጂነር ሰለሞን ገብረስላሴን የያዘ ከፍተኛ አመራር አባላት ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ተቀብለዋቸዋል።

ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ንጋቱ እንዳሉት፤ ፓርቲው በአገሪቱ አሁን የተጀመረውን ለውጥ መሰረት እንዲይዝ የሚችለውን ያደርጋል።

በተፈጠረው እድል ህጋዊ ሆኖ ለመንቀሳቀስ ፓርቲው ዝግጁ መሆኑን የገለፁት ሊቀመንበሩ ከአሁኑ የለውጥ አመራር ጎን በመሆን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር #በትጋት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ሚናቸውን በአግባቡ ለመወጣትም ከቀድሞ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ከወጣቱ ጋር የጋራ ምክክር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

የህግ የበላይነት እንዲከበርና ዴሞክራሲ የበለጠ እንዲሰፋ ፓርቲያቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር #ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የፓርቲው አመራሮች ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥና ሻማ የማብራት ስርዓት ያከናውናሉ ተብሏል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቡራዩ⬇️

"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ...በቡራዩ ነው የምኖረው እና በቀደም ተፈጥሮ በነበረው አላስፈላጊ ድርጊት ለይ ተሰማርተው የነበሩ በርካታ ሰዎች እየተያዙ ነው በተለይ በስርቆት ለይ ተሰማርተው የነበሩ ከነሰረቁት እቃ በቡራዩ ቄሮ ወጣቶች እና በኦሮሚያ ፓሊስ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች መግቢያ ጥቅምት 01 እና 02 ሲሆን የአዲስ ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደሴ⬆️የአርበኞች ግንባር 7 ንቅናቄ አመራሮች በደሴ ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

©Amir
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ⬆️ለአፋር ህዝብ ፓርቲ ዛሬ በሰመራ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪ ደማቅ አቀባበል አድርጓል። የተደርገው አቀባበልም #በሰላም ተጠናቋል።

በሌላ በኩል...

ዛሬ 9:00 በሰመራ ሉሲ አዳራሽ Dr. Konte Musa የፓርቲው መስራች እና ሊቀመንበር ከህዝቡ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።

©Samarians ከሰመራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia