TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢንጂነር ታከለ ኡማ⬆️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ታክሲ ተራ አስከባሪዎችን ቁርስ ጋብዘው በሚሰጡት አገልግሎት ዙሪያ አወያይተዋቸዋል። ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በከተማዋ ከነዋሪው እየቀረበ ባለው ቅሬታ መሰረት የታክሲ ተራ አስከባሪዎቹን ያነጋገሩ ሲሆን በከተማዋ መስተዳድር በኩልም መሟላት ያለባቸውን ነገሮች ለማሟላት ቃል ገብተውላቸዋል።

©ዋልታ ሚዲያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ⬆️

የኦሮሞ #አባ_ገዳዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉብኝት ማድረጋቸው ተሰማ። አባ ገዳዎቹ በመቂ ባቱ ህብረት ስራ ማህበር የተመዘገበውን ስኬት በሁሉም መስኮች ላይ ለማስቀጠል ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ለመተካት የሚቻልበትን ሁኔታዎች ላይ ምክክር አድርገዋል ተብሏል።

©Dw Amharic
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦነግ እና ኦፌኮ ተስማሙ⬆️

ኦፌኮ እና ኦነግ በዛሬው እለት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው #ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ያስታወቁት። በዚህም መሰረት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በኦሮሞ እና ኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ነው በመግለጫው ያስታወቁት።

©OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴድሮስ ካሳሁን "ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር" ኮንሰርት የመግቢያ ትኬቶቹን በዳሽን ባንክ በኩል ታገኛላችሁ።

📌ኮንሳርቱ መስከረም 5 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
@tsegbwolde @tikvahethiopia
ዛላንበሳ⬆️

ንመላእ ህዝቢ ትግራይ፣ ህዝቢ #ኤርትራን ህዝቢታት #ኢትዮጵያን እንኳዕ ንሓዱሽ ዓመት 2011 ዓ.ም ብሰላም ኣብፀሓኹም።

ኣብ #ዛላንበሳ ዝነበረ ሓፁር/ድፋዕ/ብኣባላት ምክልኻል ሰራዊት ኤርትራን ኢትዮጵያን ብኸምዚ ብሰላም ምፍራስ ጀሚሩ ኣሎ።

እዙይ ርክብ ኣሓት ህዝብታት ትግራይን ኤርትራን መላእ ህዝብታት ኢትዮጵያን ንምጥንኻር ዝለዓለ ትፅቢት ዝግበረሉ ተግባር እዩ።

ደጊምና ሰናይ ሓዱሽ ዓመት!
.
.
የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ጳጉሜን 5 ቀን 2010 ዓም በዛላምበሳ ድምበር ተገናኝተዋል፡፡ኢትዮ ኤርትራ በመሬት ለማገናኘት ከሚያስችሉ መንገዶች አንዱ ዛላምባሳ ሲሆን በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር በሁለቱም አገራት መሪዎች ስምምነት መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼

©የትግራይ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvavahethiopia
ማስታወቂያ📌ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ⬇️

ቀን 05/13/2010 ዓ.ም

በ2010 ዓ/ም ሁለተኛው ወሰነ ትምህርት የ3ኛ ዓመት የቴክኖሎጅ ተቋም ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየተገበረ ባለው ስርዓተ ትምህርት መሰረት ‘Holistic‘ ፈተና አንፈተንም ማለታቸውን ተከትሎ በተፈጠረዉ አለመረጋጋት ጥፋተኛ በመባላቸው በቴክኖሎጅ ተቋም ሴኔት ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ከተማሪ ወላጆች እና ከተማሪዎች ህብረት ጋር በተደረገ ተከታታይ ውይይት መሰረት ተማሪዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ መነሻነት ዩኒቨርሲቲው የይግባኝ አቤቱታውን ተመልክቶ የሚከተሉትን ውሣኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታ መታገድ የሚለው #ቅጣት በመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ #ተሻሽሎ ተማሪዎች ወደ መደበኛ ትምህርታቸው እንዲመለሱ፣

2. በ2010 ዓ/ም የ2ኛው ወሰነ ትምህርት ያልተፈተኑትን #ማጠቃለያ ፈተና ተቋሙ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሠረት እንዲፈተኑ፣

3. በ2011 ዓ.ም የሚሰጠው ‘’Holistic‘’ ፈተና ተቋሙ ባፀደቀው ስርዓተ ትምህርት እና የአካዳሚክ ህግ መሠረት በሚወጣው የጊዜ ሰሌዳ እንዲፈተኑ፣

ስለሆነም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የቴክኖሎጅ ተቋም ተማሪዎች ይህን ውሣኔ አውቃችሁ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እየገለጽን የመግቢያ ጊዜውን በጥሪ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ #አመራሮች መስከረም 5/2011 ዓ.ም ባሕር ዳር ይገባሉ፡፡ በባሕር ዳር ከተማ ስለሚኖረው የአቀባበል መርሀግብር ኮሚቴው መስከረም 2/2011 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETV ZENA LIVE! ዶክተር አብይ አህመድ! "በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻግር"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ማውጫ⬆️
@tsegabwolde @tikahethiopia