TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Udate ጅግጅጋ⬇️

አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በፌስቡክ ገፁ ይህን ዜና አሰማ⬇️

"ተረጋግጧል! ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የራሱን ስልጣን ለማስጠበቅ ሲል ኢትዮጵያ ሱማሌንና ህዝቧን በህገወጥ መንገድ ለማስገንጠል ሴራ ሲጎነጉን የነበረውን አብዱ ኢሌን በፅኑ ክንዱ ማረከ። በፍቅር፣ በይቅርባይነትና በመደመር በጎ መንፈስ ላይ የተመሰረተው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት በሀገር ህልውና ጉዳይ ምን ይህል ጥርስ እንዳለው ያሳየበት እርምጃ ሆኗል። የህግን ጥሬ ቃል ከእውንተኛ መንፈሱ እየገነጠሉ ለራሳቸው ጥቅም የሀገርን ህልውና መያዣ ለማድረግ ለሚያስቡ የሹም ዶሮዎች ይህ የዛሬው ወታደራዊ እርምጃ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ነው።

ዘገባዎች እንደ ሚሉት ኤታማዦር ሹም ባለአራት-ኮከብ ጄኔራል ሳእረ መኮንን--ዛሬ የጦራቸው እጅ ውስጥ ለወደቀው አብዲ ኢሌ "ወደህ በፍቃድህ እጅህን እንድትሰጥ የ24 ሰዓት ዕድሜ ሰጥቼሀለው "ብለውት ነበር ትናንት። ሳይሰጥ ቀረ፤ በኅይል ተያዘ።"

*ይህን መረጃ በተለያዩ መንገዶች ለማጣራት እየሞከርኩ ነው። እውነትነቱን ሊያረጋግጡ የሚችሉ መረጃዎች ካሉ በፍጥነት አቀርባለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopa
#udate ጅግጅጋ⬇️

አሁን በጅግጅጋ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በስልክ ቆይታ አድርጌ ነበር፦ ያናገርኳቸው ሰዎች ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የተደራጁ ሰዎች ወደ ቤታቸው መጥተው መሉ በሙሉ ያላቸውን ንብረት ዘርፈው ሄደዋል። ድብደባም እንደተፈፀመባቸው ነግረውኛል። "አሁን ህይወታችን ነው የተረፈን ህይወታችችን እየጠበቅን ነው" ብለውኛል ያናገርኳቸው አንድ አባት። በአካባቢው ምንም የመከላከያ ሰራዊት እንደሌለ የገለፁልኝ እኚሁ አባት የክልሉን ፖሊስ ልብስ የለበሱ ሰዎች ከተደራጁ ወጣቶች ጋር ተባብረው ከፍተኛ ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው ሲሉ ገልፀውልኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#udate ከአፋር ክልል⬆️

በአፋል ክልል አምቢራ ወረዳ ሰርካሞ በሚባል ቀበሌ ዛሬ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቶ ነበር። ጎርፉ የሰዎች ቤት ድረስ በመግባት እቃዎችን አበላሽቷል። ይህ ነገር በየአመቱ እንደሚከሰት የቀበሌው ነዋሪ የሆኑ የቻናላችን ቤተሰቦች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#udate ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬇️

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ዛሬ ከጀርመኗ ቻንስለር (መራሂተ-መንግስት) ከክብርት ወ/ሮ አንግላ መርከል ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡

ቻንስለር መርከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጭር ጊዜ እያካሄዱ ላሉት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራዎች በተለይም ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም አድናቆታቸውን በመግለጽ እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋቸዋል፡፡

ቻንስለሯም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀርመን ተገኝተው በአፍሪካ እና በአውሮፓ ጉዳዮች ላይ እንዲመክሩ የጋበዟቸው ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ግብዣውን መቀበላቸውን አረጋግጠውላቸዋል፡፡

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#udate ድሬዳዋ⬇️

በድሬዳዋ ከተማ አንዳንዳንድ ቀበሌዎች ሰዎች ላይ ዝርፊያ እንደሚፈፀም ነዋሪዎች ገልፀዋል። መንግስት የህግ የምበላይነትን ሊያሰፍን እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ከድሬዳዋ ከተማ ያናገረችኝ አንዲት ወጣት ከጥቂት ጊዜ በፊት በኢትዮጵያ ደረጃ በሰላሟ ተወዳዳሪ ያልተገኘላት ድሬዳዋ ከተማ አሁን ለኑሮ አስቸጋሪ እየሆነች መጥታለች ስትል ትናገራለች። ሰዎች ቤታቸውን ለቀው ወደ ተለያየ ቦታ እንደሄዱም አክላ ገልፃለች። መንግስት እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም ጠቁማለች።

"እኔ ተወልጄ ያደኩት እዛው ቀበሌ ውስጥ ነው ቤተሰቦቼ ከ25 አመት በላይ ከኖርንበት ቤታችን ወተን ዘመድ ጋር ተጠግተን ነው ያለነው።" ስትል በእሷና በቤተሰቧ ላይ የደረሰውን ተናግራለች።

📌ከድሬዳዋ ፖሊስ በኩል የሚሰማ ነገር ካለ ተከታትዬ አሳውቃችኋለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#udate ራያ⬆️

በትናንትናው ዕለት በራያ የማንነት ጥያቄ ላይ በአዲስ አበባ የአካባቢው ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ አስመልክቶ በጉዳዩ ላይ የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ #ረዳዒ_ሃላፎም የሰጡት ምላሸ።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia