TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ዳውሮ ዞን⬆️

በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ዛሬ ማለዳ ላይ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ12 ሰዎች #ህይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከፍተኛ #ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የወረዳዉ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የመሬት መንሸራተቱ በወረዳዉ ጉዛ ቀበሌ ዘማ መንደር በሶስት መኖርያ ቤቶች ላይ መከሰቱን የጽህፈት ቤቱ ኃለፊ ሻምበል አልታዬ አለሙ ገልፀዋል፡፡

በአደጋው ከሞቱት 12 ሰዎች መካከል በህብረተሰቡ ተሳትፎ የ10ሩ አስክሬን የተገኘ ሲሆን፥ የሁለቱ አስክሬን ባለመገኘቱ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉን አራት ግለሰቦች ወደ ተርጫ ሆስፒታል በመውሰድ የህክምና ዕርዳት እንዲያገኙም እየተደረገ ነዉ፡፡

በአደጋዉ ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን፥ በቀጣይ ጊዜያትም በስፍራዉ ያሉ ቤቶች ጥንቃቄ ካልተደረገላቸዉ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሽረ እደስላሴ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ያደገ 3ኛው ክለብ ሆኗል።

📌ዛሬ ሀዋሳ ላይ በተደረገው ጨዋታ ጅማ አባ ቡናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በሌላ በኩል፦ ደቡብ ፖሊስ ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ የዘንድሮ ሻምፒዮን ሆኗል።

©ሶከር ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
#update ኢቦላ⬆️

በኮንጎ #የኢቦላ በሽታ እንደገና በማገረሸቱ የተነሳ ወላጆች በፍርሃት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት #እያስቀሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በኢቦላ ቫይረስ በሽታ ምክንያት በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #የትምህርት ተሳትፎ መቀነሱ ተገልጿል፡፡

የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ወረርሽኙ በነሐሴ ወር ከተከሰተ ወዲህ በኢቦላ #የሞቱ ሰዎች ቁጥር 75 ደርሷል፡፡

ይሄን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረትም በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው መላክ መጀመሩን አልጀዝራ በዘገባው አመልክቷል።

@tsegawolde @tikvahethiopia
#ለፈገግታ

ክቡር ዳኛ - አቶ አብዲ #መከላከያ ማቅረብ ይችላሉ?

አቶ አብዲ - አልችልም ክቡር ፍርድ ቤት #ልዩ_ኃይል ላቅርብ??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጎንደር⬆️

"ሰላም ፀግሽ በአሁን ሰዓት በጎንደር ቀበሌ 18 የአማራ ቴሌቪዥን በኮሎኔል #ደመቀ_ዘውዱ ቤት "የይቅርታ እና የፍቅር ጉዞ" በሚል መሪ ቃል የእንኳን አደረሰህ መልካም ምኞታቸውን እየገለፁለት ይገኛል። አክሊያስ ከጎንደር"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምርቃት #ለፈገግታ

ሹሉቃ - ስማ ሻቃ! እኛ ሀገር ግን #ሙስናን በይፋ ሲያወግዝ የነበረ ሰው ስልጣን ሲይዝ ድምፁን የሚያጠፋው ለምንድነው?

ሻቃ - ባህላችን ነው ወዳጄ! #እየተበላ አይወራም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ታምራት ገለታ⬆️

”ባለአውሊያ” እና ”ባለከራማ” ነኝ በማለት ከአሥር ዓመት በላይ በጥንቆላ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው አቶ ታምራት ገለታ #ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ”ጥፋተኛ” ብሎ ንብረቶቹም ተወርሰው ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ መወሰኑ የሚታወስ ነው

በአንድ ወቅት እጅግ አነጋጋሪ የነበሩት ከጥንቆላ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ለእስር የተዳረጉት አቶ ታምራት ገለታ ባሳለፍነው ሳምንት በምህረት መለቀቃቸውን ካፒታል የእንግሊዘኛው ጋዜጣ ዘግቦታል።

©ድሬትዩብ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአየር ትራፊክ ባለሞያዎች⬇️

ትናንት በቁጥጥር ሥር የዋሉት 9 የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የተያዙት ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት እሥራት ሊያስቀጣ በሚችል #ጥፋት መሆኑ ተገለጸ፡፡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ናቸው ይሕን ያሉት። ኮሚሽነሩ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሠራተኞቹና በአሠሪያቸው ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በድርድር ለመፍታት ጥረት መደረጉንና ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ጣልቃ ገብቶ ማደራደሩን ተናግረዋል።

“የተወሰኑ የእንቅስቃሴው መሪዎች ሠራተኛው #አድማ እንዲመታ በማስተባበር ቀጥለውበታል” ያሉት ኮሚሽነሩ “የኢትዮጵያን አየርም ሆነ የአየር መንገዱን ዝና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ
መልዕክቶችን ለዓለምአቀፍ ድርጅቶች ሲያሠራጩ ቆይተዋል” ብለዋል።

©ዋዜማ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውሻ እንኳን ለሰው ልጅ ይሄን ያህል ፍቅር አለው...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጻጻሳት ዘኢትዮጵያ 30ኛ አመት በአለ ሲመት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት ተከብሯል።

©ጴጥሮስ አሸናፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለመከረም 5ቱ የሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርት ከመንግስት ፍቃድ ማገኘቱን ገልጿል።

©ቴዎድሮስ ካሳሁን
@tsegabwolde @tikvahethiopia