TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማስታወሻ📌Jawar Mohammed ከLTV ጋዜጠኛዋ ቤቲ ጋር ቆይታ አድርጓል። ወሳኝ ጥያቄዎችም ተነስተውለት ምላሽ ሰጥቷል። ይህ Program እሮብ ምሽት 2፡30 ይተላለፋል።

▪️LTV freq👉11512 Symbol Rate 27500 V

©DAN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎቹ መታሰር አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል።

በተቋሙ ከሚሰራ የቻናላችን ቤተሰብ እንዳስረዳኝ፦

▪️ሰራተኞቹ ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩ 8 ዓመት ተቆጥረዋል።

▪️ከሚሰሩት ስራ አንፃር እና ከስራው ጫና አንፃር የሚከፈላቸው ክፍያ ተገቢ እንዳልሆነ ይገልፃሉ።

▪️የሚከፈላቸው ክፍያ ከኢትዮጵያ ከሚያንሱ ጎረቤት ሀገራት ሰራተኞች አንፃር እንኳን ሢታይ ዝቅተኛ ነው።

▪️ጥያቄያቸውን በአግባቡ ቢጠይቁም ምላሽ በማጣታቸው አድማ ለማድረግ መገደዳቸውን ይናገራሉ።

▪️ጥያቄዎቻቸን ለመቀልበስ ብዙ እንደተሞከረ እና ከአመራሮቹም ተገቢ ያልሆኑ ገለፃዎች ሲደረግላቸው ነበር።

▪️ስራውን የማቆም ፍላጎት ባይኖራቸው የአመታት ብሶት ለዚህ እንዳበቃቸው ይናገራሉ።

▪️ተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ።

▪️11 የሚደርሱ ሰራተኞች ገብተው እየሰሩ ቢሆንም ከስራው ጫና አንፃር ይህ ከባድ ሆኗል።

▪️የኢትዮጵያ አቬሽን ባለስልጣን ለሚዲያ የሚናገረው ከእውነት የራቀ ነው። ምንም ችግር እየተፈጠረ አይደለም ሲል የሚያስተባብለው ስህተት ነው።

▪️ለጠ/ሚ ፅህፈት ቤት በሰራተኛው ዙሪያ ሲቀርብ የነበረው ሪፖርት ፍፁም የተዛባ ነበር።

▪️አሁንም የመልካም #አስተዳደር ችግር በሚሰሩበት መስሪያ ቤት አለ ይህንንም መንግስት እንዲፈታው ጠይቀዋል።

📌ትላንት እንደሰማነው ደግሞ ፌደራል ፖሊስ አድማውን አስተባብረዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሏል።

📌የሰራተኞችን ጥያቄ ለማፈን መሞከር ተገቢ አይደለም። አሁንም የሰራተኞቹን ጥያቄ ለመመለስ ተነሳሽነትም የእየታየ አይደለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስጦታ⬆️አርቲስት እና አክትቪስት #ታማኝ_በየነ በራስ ጋይንት የንግዱ ማህበረሰብ የመኪና ስጦታ ተብረከተለት።

©ECADF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🎁የአዲስ ዓመት ሥጦታ #ለእናት ሀገሬ⬆️

አዲስ የተስፋ ቀመር፦

ጥላቻን -
ያለንን ÷
ይቅርታን ×
በፍቅር +

📌የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሚሊኒየም አዳራሽ እየሄዳችሁ በቻላችሁት አቅም ለእናት ሀገራችሁ ስጦታ አበርክቱ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update "የአንበሳ ስጋ ሰረቀ ተባልኩ"

ዶ/ር ሙሴ ክፍሎም⬇️

ባለፈው ቅዳሜ የአንበሳ ግቢ በመሄድ እንስሳዎቹ ያሉበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከተመለከን በኀላ በቅርቡ ከስራቸው የተሰናበቱትን ዶ/ር #ሙሴ_ክፍሎምን ዛሬ ቢሮዋቸው ሄጄ አነጋግሬአቸው ነበር።

ይህንን ነገሩኝ፦

-በሁለት አመት ውስጥ 7 አንበሳ ሞተ የተባለው ፈፅሞ ስህተት ነው። ይኸው ዶክመንታቸውን ባሳይህ ባለፈው 5 አመት ውስጥ አምስት አምበሳ ነው የሞተው... አብዛኞቹ በእድሜ እና አንዱ በህመም።

-አንበሶቹ ከሱ ለተባለው፤ በፊት በሳምንት እስከ 300ኪግ ስጋ ይገባ ነበር። ብዙው ግን ተርፎ ይበላሻል ስለዚህ በእንስሳት አመጋገብ ባለሙያዎች አስጠንተን በቀን ለአንድ አምበሳ 7ኪግ እየሰጠን ነው። ምናልባት የባለሙያዎቹ ግምት ስህተት ከሆነ ብለን ጉዳዩን እያየነው ነበር።

-ፒኮክ የሚገኘውን እና 91 ሚልዮን ብር የጨረሰውን አዲስ የአንበሳ ግቢ ለማጠናቀቅ 3 እና 4 ወር ሲቀረን እኔን ካለ በቂ ማጣራት #ለማባረር መፈለጉ #አልገባኝም። ክሬዲቱን ለማን ለመስጠት ነው?

- ሚድያዎች ዘመቻ አርገውብኛል። እኔ ሸገርን (ወ/ሮ መአዛ ብሩን ጨምሮ) ኑ ዶክመንት ተመልከቱ ብላቸው ማንም አልሰማኝም። በሁዋላ ግን የአንበሳ ስጋ #ሰረቀ ተባልኩ።

© AP - Elias Meseret Taye
@tsegabwolde @tikvahethiopia