TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የስራ ማቆም አድማ⬇️

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ‹‹ላለፉት ስምንት ዓመታት ላነሳናቸው ፍትሐዊ የሆኑ ከሙያ ዕውቅና፣ ከደመወዝና ከጥቅማ ጥቅም ጋር ለተገናኙ ጥያቄዎች በቂና ወቅታዊ ምላሽ አላገኘንም፤›› በማለት፣ ከሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠዋት ጀምሮ የሥራ ማቆም #አድማ እንደሚያደርጉ አስታወቁ፡፡

በዚህም መሠረት #ከሰኞ ጠዋት አንድ ሰዓት ጀምሮ ከአምቡላንስ፣ ከቪአይፒና ከወታደራዊ በረራዎች ውጪ አናስተናግድም ሲሉም፣ ለባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ባስገቡት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

ተቆጣጣሪዎቹ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባስገቡት ደብዳቤ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው፣ ምላሽ ካላገኙ ግን ሥራቸውን #እንደሚለቁ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

ዞናዊ ስምሪቱ የሚኖሩበትን አካባቢ ያላገናዘበና ፍትሃዊነት የጎደለው መሆኑን በአዲስ አበባ የተሰማሩ ድጋፍ ሰጭ ባለታክሲዎች ተናገሩ።

ቅሬታቸውን ለFBC ያቀረቡ ባለ ታክሲዎች እንዳሉት ዞናዊ የስራ ስምሪቱ የመኖሪያ አካባቢያቸውን ያለገናዘበና ፍትሃዊነት የጎደለው ነው።

ባለ ታክሲዎቹ ስምሪቱ ፍትሃዊ አለመሆኑን ተከትሎም በዛሬው እለት በአንዳንድ አካባቢዎች የስራ መቆም #አድማ አድርገዋል።

ባለ ታክሲዎቹ አንዳንድ መስመሮች በህገ ወጥ መንገድ ለተወሰኑ ግለሰቦች እየተሰጡ መሆኑንም አንስተዋል።

ጠዋትና ማታ እየሰሩ መሆናቸውን የሚግልጽ የስራ መሙያ ፎርም ለመሙላትም የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ተቆጣጣሪዎች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በስራ ቦታቸው ባለገኘታቸው ምክንያት መቸገራቸውንም አስረድተዋል።

በዚህ ሳቢያም በህገ ወጥ መንገድ ላለመቀጣት በሚል ለተቆጣጣሪዎች ገንዘብ እየከፈሉ መሆኑን በመጥቀስ፥ ተቆጣጣሪዎቹ ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባልም ብለዋል።

እንደ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገለጻ ማህበር ለማቋቋም ያደረጉት ሙከራ በተለያየ ምክንያት ባለመሳካቱ መብታቸውን ለማስከበር ተቸግረዋል።

አሁን ላይ ያለው ችግር ይስተካከል ያሉት አሽከርካሪዎቹ ረጃጅም መስመር እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ድጋፍ ሰጭ እንደመሆናቸው መጠን በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ላይ ከሚሰሩበት መስመር ውጭ ወደ ሌሎች መስመሮች እንዲሰማሩም ነው የጠየቁት።

የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በበኩሉ ዞናዊ ስምሪቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በመታገዝ የተሰራ በመሆኑ የፍትሃዊነት ጥያቄ አይነሳበትም ብሏል።

ዛሬ የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ ባለ ታክሲዎችም አነስተኛ ገቢ በሚያስገኙ መስመሮች የተመደቡ መሆናቸውን የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ተናግረዋል።

ምክትል ሃላፊው ዛሬ የተፈጠረውን የታክሲ አገልግሎት እጥረትም የሸገርና ሌሎች ትራንስፖርት ሰጭ ማህበራትን በማሰማራት ለመፍታት ተሞክሯልም ብለዋል።

በቀጣይም የቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመንና ከሰው ንክኪ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የስራ ማቆም አድማ⬆️

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን በመጠየቅ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም #አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰራተኞቹ ለኢቢሲ በስልክ እንደገለፁት በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው #ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ፣ የሰራተኛ አያያዝ ችግር፣ የሰራተኞች ምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ መናር የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ወ/ኪዳን ሰራተኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ለአቢሲ አረጋግጠዋል፡፡

ሰራተኞቹ ያቀረቡትን ችግር ለመፍታት ውይይቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

ከሰዓት በኃላ የግንባታ ተቋራጩን ጨምሮ በሚደረግ የጋራ ውይይት ችግሩ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia