🔊 #የሰራተኞችድምጽ
🔴 " ቅሬታችን በአስቸኳይ ምላሽ ያግኝ " - የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች
⚫️ " ለክልሉ መንግስት ቅሬታውን አቅርበናል። ነገር ግን ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ መስጠት አልቻለም " - የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰው ኃብት አስተዳደር
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች " በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥቅምት አንድ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ጭማሪ እስካሁን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ተግባራዊ ባለማድረጉ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
በተጨማሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሸን ለሁሉም ሲቪል ሰርቫንት የኑሮ ውድነት መደጎሚያ ያደረገውን ጭማሪ እስካሁን አልተጨመረንም ብለዋል።
ሰራተኞቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለክልሉ ገቢዎች ቢሮ ማቅረባቸውን የገለፁ ሲሆን ጥያቄያችን በቀጠሮ የታጀበ የአመታት ችግር ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።
" የክልሉ መንግስት የተቋሙን ሰራተኞች ድካም እና መስዋዕትነት የተረዳው አይመስለንም። እኛ ተስፋ ቆርጠናል ፣ የሚሰማን አካል የለም፣ እየታገትን እና እየተገደልን ነው ፣ ከማህበራዊ ሂወት ተገለናል " ብለዋል።
አክለውም " እንደሰው መቆጠር ናፍቆናል ፣ ችግሮቻችን በዝተዋል ፣ ችግሮችን የሚፈታልን የለም ፣ እባካችሁ የሚሰማን አካል ካለ የሁለት አመት ቅሬታችን ይሰማ " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
አያይዘውም ሰራተኞቹ መጋቢት 5 / 2015 ዓ.ም " ይወክሉናል " ያሏቸውን ተወካዮች በመምረጥ ለክልሉ ገቢዎች ቢሮ ፣ ለበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ለብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አመራር እንዲሁም ለርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ቅሬታቸውን እንዳቀረቡ ገልፀዋል።
ሰራተኞቹ በሰዓቱ ለአመራሮቹ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች በርካታ መሆናቸውን የገልፁ ሲሆን ከጥያቄዎቻቸው መካከል ፦
- የገቢ ተቋሙ ሰራተኛ በልዩ ሁኔታ በጥናት ላይ የተመሰረተ ልዩ ጥቅማጥቅም ይደረግልን፣
- የእርከን ጭማሪ በአደረጃጃትና በመመሪያ ደረጃ የወረደ ቢሆንም በአፈጻጸም ተግባራዊ ይደረግ
- የሰራተኛውን ጥቅም የሚመለከት ጥናት ሲጠና እስከ ታችኛዉ መዋቅር ያለ ባለሙያ ተሳታፊ ይደረግ የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በመሆኑም በሰዓቱ አመራሮቹ በምላሻቸው ጥያቄው " ተገቢነት ያለው የባለሙያውን ሮሮና ብሶት ያዘለ ስለሆነ በቀጣይ የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ይህንን አካል የግድ ማትጋትና ማበረታታት አስፈላጊ ስለሆነ ጥያቄውን እንፈታለን " ብለውን ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።
" ይሁን እንጂ ቅሬታችንን ሰምቶ የፈታልን አካል የለም " ያሉ ሲሆን " አሁንም ለከፋ ችግር ተጋልጠን እንገኛለን " ሲሉ አክለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ሰራተኞቹ የክልሉን የገቢዎች ቢሮ የሰው ሀብት አስተዳደር ቅሬታችንን ፍቱልን ብለን ጠይቀን ነበር ያሉ ሲሆን ሀላፊውም " ቅሬታችሁ ከአቅማችን በላይ ነው። በአስቸኳይ ምላሽ ይሰጣቸው ስንል ለክልሉ መንግስት ጥያቄ አቅርበናል እስካሁን ግን መልስ የለም " የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
እንደተቋም በቀን እስከ 200 ሚሊየን ገቢ የሚሰበስብ ሰራተኛ አንድ ቀን ስራ ቢያቆም እንኳ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ቀላል መሆኑን ጠቁመዋል።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንደኛው ከደሴ ኮምቦልቻ የደወለልን ባለሙያ ነው።
" ስራችን ከማህበረሰቡ ሂወት ነጥሎናል፣ ከነጋዴዎች አራርቆናል፣ ደመወዝ ሲያልቅብን እንኳ ከነጋዴዎች መበደር አንችልም፣ ቤት ለመከራየት ስንጠይቅ ገቢዎች ቢሮ ከሆነ የምትሰሩት አናከራይም እያሉን ነው፣ አሁን ላይ ችግሮችን መቋቋም አቅቶናል " ሲል ተናግሯል።
ስሙን መጥቀስ ያልፈለገው የደባርቅ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ ደግሞ " የደረጃ እርከን እየተሰራልን አይደለም 2012 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪ እንደተደረገ እስካሁን አልተጨመረንም ፤ በስራ አጋጣሚ ሂወታቸውን የገበሩ ጓዶች አሉ የክልሉን መንግስት ታግሰናል አሁን ላይ ግን ኑሮ ከብዶናል " ሲል ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም የሰራተኞቹን ቅሬታ በመቀበል ለአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰው ሃብት አስተዳደር ሀላፊ ለአቶ ሽመልስ አዱኛ ቅሬታቸውን ያቀረበ ሲሆን እርሳቸውም ምላሽ ያሉትን ሰጥተዋል።
" የሰራተኞቹ ቅሬታ ተገቢ ነው። በኛ በኩል ቅሬታውን እናውቃለን ። ለክልሉ መንግስት ቅሬታውን አቅርበናል። ነገር ግን ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ መስጠት አልቻለም በዚህ ጉዳይ የተለየ መረጃ ልሰጥ አልችልም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የባለሙያዎችን ቅሬታ በተመለከተ የክልሉን መንግስት እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያ እንዲሁም የክልሉን ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ በስልክ አግኝቶ ምላሻቸውን ለማካተት ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም።
በመጨረሻም ሰራተኞቹ " ቅሬታችን በአስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ከየካቲት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስራ የምናቆም መሆኑን እንገልፃለን " ብለዋል።
(ቲክቫህ ጉዳዩን እስከመጨረሻው ተከታትሎ መረጃውን የሚያደርሳችሁ ይሆናል )
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine

#ዶክተር_ፈቀደ_አግዋር🙏
'' በርካታ የልብ ታማሚዎች ወረፋ ሳይደርሳቸው ህይወታቸውን ያጣሉ '' - ዶክተር ፈቀደ አግዋር
በኢትዮጵያ የልብ ህክምና በተሟላ ሁኔታ እየተሰጠ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ በመሆኑ ወረፋ ሳይደርሳቸው ህይወታቸው የሚያልፉ የልብ ታማሚዎች መኖራቸው ይነገራል።
ዶክተር ፈቀደ አግዋር በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል '' የልብ ቀዶ ህክምና '' ሀኪም ናቸው። 800 የልብ ቀዶ ህክምና አድርገዋል።
በሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ደግሞ (HVE) 25 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ነፃ የልብ ቀዶ ህክምና ለ30 ታዳጊዎች ሰርተዋል። በተጨማሪም " የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ " የተሰኘ መጽሐፍም ለአንባቢ አበርክተዋል።
ዶ/ር ፈቀደ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በርሀ በታች ባሉ ሀገሮች ላይ በአሁኑ ሰዓት በተደጋጋሚ በሚከሰት ቶንሲል ምክንያት የሚፈጠር የልብ ህመም ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ድረስ በከፍተኛ ሁኔታ ለልብ ህመም መፈጠር ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።
በቅርቡ በሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) የነጻ ህክምና ተጠቃሚዋ መሆን የቻለችው የ18 አመቷ ታዳጊም የልብ ህመሟ በቶንሲል ምክንያት የተከሰተ ሲሆን 4 ሰዓታት በፈጀው አንድ የግራ ልብ በር ቀዶ ህክምና በቶንሲል ምክንያት ክፋኛ የተጎዳው የታዳጊዋ የልብ በር በመቀየር የተሳካ ህክምና አድርጋለች።
የልብ ቀዶ ህክምና የሚሰጠው ደረት ተከፍቶ፣ ልብና ሳንባ ቁሞ፣ የደም ዝውውር ለማሽን ተሰጥቶ በመጨረሻም ልብ ተከፍቶ ህክምናው እንደሚሰጥና በዚህም ብዙ የህክምና ሂደቶችን እንደሚያልፍ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስረዳሉ።
የልብ ህመም በተፈጥሮ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በዓለም ላይ '' ከ1 ሺ ሰው 10 ሰው '' በተፈጥሮ የልብ ችግር ይኖርበታል ተብሎ ይታሰባል።
በሌላ በኩል ደግሞ በደም ግፊት፣ በስኳር በሽታ ምክንያትም የልብ ህመም እንደሚከሰት የልብ ሀኪሙ ዶክተር ፈቀደ ገልፀዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የልብ ህክምና በተሟላ ሁኔታ የሚሰጠው በአዲስ አበባ በመሆኑ ለታማሚዎች ፈተና እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።
" በሽዎች እሚቆጠሩ ሰዎች ወረፋ ይጠብቃሉ፣ወረፋ ሳይደርሳቸው በርካቶችም ህይወታቸውን ያጣሉ '' ብለዋል።
በመጨረሻም ተሳክቶላቸው ወረፋ ሲደርሳቸው በጣም ያረፈዱና የተወሳሰቡ ህክምና እንድንሰጥ እንገደዳለን ሲሉ ዶ/ር ፈቀደ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
" ለአንድ የልብ ህመምተኛ ህክምና ለመስጠት በርካታ ባለሙያዎች፣ ብዙ ማሽን ጥቅም ላይ ይውላላል ከዚህ አንፃር በአሁኑ ሰአት በኛ ሀገር የልብ ህክምና ገና ጅማሮ ላይ ነው ማለት እንችላለን " ብለዋል።
እንደ መፍትሔ . . .
በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ሁሉንም ነገር ያሟላ የልብ ህክምና የሚሰጠው ተቋም የኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል እንደሆነ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ይናገራሉ።
ይህን ማዕከል አሳድጎ ትምህርት ቤት በማድረግ ብዙ የልብ ህክምና ባለሙያዎችን በማፍራት በየከተማው፣ በየክልሉ እንዲሄዱ በማድረግ ችግሩን መፍታት የሚቻልበት መንገድ ቢፈጠር ሲሉ ኃሳባቸውን ያቀርባሉ።
በተጨማሪም አሁን ላይ ማዕከሉ ያለውን አቅም አሳድጎ ብዙ የልብ ቀዶ ህክምናዎችንም እንዲሰራ ቢደረግ ለበርካቶች መድረስ እንደሚቻልም ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና እና በደም ስር ገብቶ የሚሰራ የልብ ህክምና የሚሰጡት ቅዱስ ጳውሎስ፣ ጥቁር አንበሳና ኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የልብ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#TikvahEthiopia
Via @tikvahethmagazine