TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት በይፋ ተመሰረተ።

ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ የመረጠ ሲሆን የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ደጀን በርሀ (ዶ/ር) በከፍተኛ ድምፅ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል። 

የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት የማቋቋም ሃሳብ የክልሉ ምክር ቤት የሚያፈርሰው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋምያ ሰነድ ጥር 2015 ዓ.ም ሲፀድቅ የተነሳ ሃሳብ ነው።  

ሃሳቡ በድጋፍ እና በተቃውሞ ለሁለት አመታት ያህል ሲናጥ ቆይቶ ዛሬ ጥር 25/2017 ዓ.ም በይፋ ተመስርቶ መሪዎቹ መርጠዋል። 

በምስረታ ካውንስሉ መልእክት ያስተላለፉት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ የሚገኙ የኢሮብ እና ኩናማ ብሄረሰቦች የተወከሉበት ካውንስሉ ዘግይቶም ቢሆንም መመስረቱ መልካም ሆኖ አቃፊ ፣ አሳታፊ እና የሃሳብ ብዙህነት የሚንሸራሸሩበት መድረክ መሆን ይገባዋል ብለዋል። 

የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተቀመጡት የትግራይ ህዝብ ጥቅሞች በተሻለ እና በአስተማማኝ እንዲመለሱ አጋዥ ሃይል ለማሰባሰብ አልሞ መቋቋሙን የጠቆሙት ፕሬዜዳንቱ " ልዩነቶቻችን በማጠበብ ለተሻለ ነገ በጋራ መስራት ወቅታዊ የትግራይ ጥያቄ ነው "  ብለዋል። 

የካውንስሉ እድሜ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ መሆኑ ያስረዱት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ይህንን ታሳቢ በማድረግ የትግራይ ፓለቲካዊ ምህዳር ማስፋት እና ለነገ ማመቻቸት ዋነኛ ስራው መሆን እንደሚገባ አክለዋል።   

ካውንስሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች መሬት ላይ እንዲወርዱ አጋዥ ሚና ከመጫወት በተጨማሪ የትግራይ ተደማጭነት እና የመደራደር አቅም የሚያጠናክር አቅጣጫ መከተል ይገባዋል ብለዋል ፕሬዜዳንቱ። 

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት ለመምራት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ቃለ ማህላ ፈፅሟል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት መመስረት በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት እና ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ እና ሌሎች ተቃውሞውታል

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከፕሬዜዳንቱ እና ካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል "- አቶ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ

በትግራይ ከጊዚያዊ አስተዳደር " ከፕሬዜዳንቱ እና ከካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል " ሲሉ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ ተናገሩ።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ባያውጅም መቐለ ጨምሮ በመላ ትግራይ በስሙ መጠራት ያለበት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አለ " በማለት አክለዋል።

ከህዳር 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የመቐለ ከንቲባ ሆነው በጊዚያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ የተሾሙት እና ህዳር 23/2017 ዓ.ም አንድ ጊዜ ብቻ ቢሯቸው ከገቡ በኋላ ያልተመለሱት ከንቲባው " ላዛ ትግርኛ " ለተባለ ሚድያ ሰፊ ቃለመጠየቅ ሰጥተዋል።

" ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ከመንግስት በላይ ሆኖ ከንቲባ ስራውን እንዳይሰራ ፤ ህዝብ ከከንቲባ ማግኘት ያለበት አገልግሎት እንዳያገኝ መከልከል የህግ ተጠያቂነት ከማስከተል በተጨማሪ በታሪክ ያስወቅሳል " ብለዋል።

ከ8 ወራት በፊት ሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ፤ ከ4 ወራት በፊት ማእከላዊ ዞን እንዲያስተዳድሩ በጊዚያዊ መንግስት ፕሬዜዳንት ፊርማ የተመደቡ ሃላፊዎች ተግባራቸው እንዳይፈፅሙ ስሙ ባልጠቀሱት ወታደራዊ አዛዥ የሚታዘዙ ጠበንጃ ባነገቡ ታጣቂዎች እንደተስተጓጎሉ ጠቅሰዋል።

እሳቸውም " ከፓሊሰ አቅም በላይ ያልሆነውን ጉዳይ የመቐለ አስተዳደር ዙሪያ በታጣቂዎች በማጠር ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ከሁለት ወር በላይ መከልከላቸው እጅግ አሳዛኝ እና የመንግሰት ትእዛዝ የጣሰ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ብለዋል። 

ፕሬዜዳንቱና ካቢኔው ሦስት ጊዜ ወደ ስራ ገበታቸው ገብተው ስራቸው እንዲሰሩ ቢያዝም አስተዳደሩን እንዲጠብቁ በታዘዙ ታጣቂዎች መከልከላቸው እጅግ እንዳሳዘናቸው እና እንዳበሳጫቸው ተናግረዋል።

" መንግስት መንግስት መምሰል አለበት ትእዛዝ እና ውሳኔ በማክበር እና በማስከበር ከመንግስት በላይ መሆን የሚፈልገውን አካል ማቆምን ማስታገስ  ይገባዋል " ብለዋል።

" ከፕሬዜዳንት እና ከካቢኔ በላይ በመሆን ታጣቂዎች በአስተዳደሩ ዙሪያ ያስቀመጠ አካል የወጣቶች ቁጣ እና መልእክት ተቀብሎ ያሰማራቸው ታጣቂዎች በአስቸኳይ ማንሳት አለበት " ያሉት ከንቲባው " ጉዳዩ ፓሊስን ይመለከታል ከፓሊስ አቅም በላይ ከሆነ የአድማ ብተና ሃይል ይሰማራል ፤ ከዚህ ውጭ ከአቅሜ በላይ ሆኗል የሚል ጥያቄ ባልቀረበበት ታጣቂ ሰራዊት ማስቀመጥ ከህግ በላይ መሆንን ያመለክታል " ሲሉ ስሙ ያልጠቀሱት ታጣቂዎች አሰማርተዋል ያሉትን አካል ተችተዋል።

መቐለ ካሉዋት 7 ክፍለ ከተሞች እና  33 ቀበሌዎች ዙሪያዋ የተወጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ከንቲባ ስራውን እንዲጀምር ፤ ህዝቡ መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ ፤ የጊዚያዊ አስዳደሩ ትእዛዝ እንዲከበር ድምፃቸው አስምተዋል ያሉት ከንቲባ ብርሃነ  " አሁንም መልስ ካላገኙ ከበፊት በላቀ ቁጥር ወጥተው ድምፃቸው ማሰማታቸው ይቀጥላሉ " ሲሉ ዝተዋል።

መቼ ወደ ተመደቡበት ስራ እንደሚገቡት ለቀረበላቸው ጥያቄ የተቆረጠ ቀን እንደማያወቁ  ተናግረዋል።

" ትግራይ ከገባችበት ፓለቲካዊ ቀውስ የምትወጣበት እንዱ እና ዋነኛ መንገድ መንግስት ሲኖራት የመንግስት ትእዛዝ እና ውሳኔ ሲከበሩ ነው ስለሆነም ከህግ እና መንግስት በላይ በመሆን ታጣቂ ያሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ " ሲሉ አሳስበዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እና በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደቡላት ከንቲባዎች ከስራ ውጭ ሆኖዉባት ከንቲባ ያጣቸው የትግራይ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ከተማ የሆነችው መቐለ የከንቲባዋ ፅህፈት 'ታሽገዋል ' የሚል ወረቀት ተለጥፎለት   በግራና ቀኝ በቆሙ ፓሊሶች እንዲሁም ዙሪያዋ በታጣቂዎች ለ24 ሰዓት መጠበቅ ከጀመረች 64 ቀናት ተቆጥረዋል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አድርሶናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ " ተጠርጣሪው ተይዞ ለክልሉ ፖሊስ ተላለልፎ ተሰጥቷል " - ፖሊስ የ19 ዓመትዋን ወጣት በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ፥ ጥቅምት 19 /2017 ዓ.ም ሓበን የማነ የተባለች ፍቅረኛውን በተከራዩት የሆቴል ክፍል በጬቤ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ከቀናት ፍለጋ በኃላ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። በአሰቃቂ…
#Update

የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

ሓበን የማነ የተባለች ወጣትን በጭካኔ በመግደል ክስ የተመሰረተበት ዳዊት ዘርኡ የተባለ ወንጀለኛ ዛሬ ጥር 28/2017 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።

ፍርዱን ያሳለፈው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ነው።

አሰቃቂ ግድያው በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነበር የተፈፀመው።

ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል በቢላዋ ተገድላ መገኘቷንና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብር ስነ-ሰርዓት መከናወኑ በወቅቱ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ፓሊስ አሰቃቂ የግድያ ተግባሩ አስመልክቶ በወቅቱ በሰጠው መረጃ ፤ የነፍስሄር ወጣት ሓበን የማነ አስከሬን ከ2 ቀን በኋላ ነው በተገደለችበት የሆቴል ክፍል የተገኘው።

ገዳይ ወንጀለኛው አሰቃቂ ተግባሩ በመቐለ ከተማ ከፈፀመ በኋላ በአማራ ክልል በኩል በድብቅ ለውጣት ሲያሴር ደሴ ከተማ በአማራ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ለትግራይ ክልል ፓሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል።

በወቅቱም ለደሴ ህዝብና ለአማራ ክልል ፖሊስ ምስጋና ቀርቦ ነበር።

ፓሊስ ጉዳዩ  አጣርቶ አቃቤ ህግ ክሰ መስርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ዛሬ እሮብ ጥር 28/2017 ዓ.ም የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ባዋለው ችሎት ወንጀለኛው በዕድሜ ልክ ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ህዝቡ ያለፈው አልበቃ ብሎት የትናንት ቁስሉ ሳይሽር አሁንም በሽብር እና በጦርነት ወሬ ስሜት ወስጥ ይገኛል ! " - የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር  የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ለትግራይ ህዝብ በተለይ ደግሞ ለልሂቃን መልእክት እና ምክር አስተላልፈዋል።  ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥር 26/2017 ዓ.ም በፅሁፍ ባስተላለፉት ጠንካራ መልእክት እና ምክር ትግራይን እና ህዝብዋን " የጥንታዊ…
ትግራይ ?

🔴 "  በትግራይ በማንኛውም መመዘኛ ጦርነት የሚጋብዝ አንዳች ሁኔታ የለም " - በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት

🚨" በአሁኑ ወቅት በትግራይ በማንኛውም ደቂቃ በሆነ ሰው በሚፈጠር ስህተት ለግጭት የሚዳርግ ሁኔታ ሰፍቷል " - አቶ ጌታቸው ረዳ


ከቀናት በፊት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ተንተርሶ ለትግራይ ህዝብ በተለይም ለትግራይ ሊህቃን ጠንካራ መልዕክት እና ምክር ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ፥ " ህዝቡ ያለፈው አልበቃ ብሎት የትናንት ቁስሉ ሳይሽር አሁንም በሽብር እና በጦርነት ወሬ ስሜት ወስጥ ይገኛል " ብለዋል።

በፓለቲካ ፣ በንግድ ፣ ፀጥታ ፣ አካዳሚ እና ሚድያ እና በሌሎች የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ የትግራይ ልሂቃን ወገኖች ባስተላለፉት መልዕክት " የትግራይ ህዝብ እስከ ዛሬ የተሰቃየው የከፈለው ዋጋ ይብቃው ፤ ልዩነትን በመነጋገር እና በውይይት የመፍታት ባህልንና ልምድ ታጠቁ " ብለዋል።

ልሂቃኑ ከፌደራል መንግስት እና ሌሎች ሃይሎች ያላቸው ልዩነት በአገሪቱ ህገ-መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመግባባት ለመፍታት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ለዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ሄር ምላሽ ያሉትን ሰጥተዋል።

ምላሹን የሰጡት 50ኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው።

በደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት  ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ሄር ምን አሉ ?

➡️ " ጠቅላይ ሚንስትሩ የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ህልውና የነበረው ተሳትፎ አስመልክተው የተጠቀሙበት አገላለፅ ልክ ነው። የትግራይ ህዝብ ሚና ባሉት ደረጃ ነው መገለፅ ያለበት ብለን እናምናለን። የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ ነፃነት ፣ ልማት እና ዴሞክራሲ የከፈለው ዋጋ እጅግ ውድ ነው። እሳቸው በፅሁፋዊ መልእክታቸው የተጠቀሙበት አገላለፅ የምንጋራው እና ክብር የምንሰጠው ነው " ብለዋል።

➡️ " የመልእክታቸው አንኳር ነጥብ ህዝቡ ጦርነት ስለማያስፈልገው የትግራይ መሪዎች እና ልሂቃን ልብ ግዙ ተመካከሩ የሚል ነው።  የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ህዝብ ጦርነት አይወድም ፤ አይገባውም። በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብም ጦርነት አያስፈልገውም። ይሁን እንጂ የትግራይ ህዝብ ባለፉት 100 ዓመታት ከማእከላዊ መንግስቱ ያደረጋቸው ጦርነቶች ከመሬት ተነስቶ ያደረጋቸው ተንኳሽ እንደሆነ በሚያደምጥ መልኩ በደብዳቤው የቀረበ አገላለፅ ልክ ነው ብለን አንወስድም " ሲሉ ተናግረዋል።

➡️ " የትግራይ ህዝብ ላለፉት 100 ዓመታት እና ከዛ በላይ የተዋጋው የሚወሩትን ፣ መብቱን የሚነፍጉትን እና ድምፁን የሚያፍኑትን ለመከላከል ሲባል መሆኑ ልብ ማለት ይገባል።  ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ጦረኛ እና ተንኳሽ በሚመስል መልኩ  የቀረበ አገላለፅ ልክ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ትናንት ፣ ዛሬ ይሁን ነገ አይገዛም አይምበረከክም። ልግዛህ ላምበረክክህ ለሚለው ወራሪ መልሱ እምቢ ነው። ከዚህ ውጭ  ጦርነት ጀማሪ ሆኖ አያውቅም ፤ ማንንም ሄዶ አይወርም ልግዛህ አይልም  ፤ ስለሆነም ጦርነት ጀማሪ በሚመስል የቀረበው አገላለፅ ልክ አይደለም " ብለዋል።

➡️ " እኛ እንወረራለን እንጂ አንወርም ፤ ጦርነት ይከፈትብናል እንጂ በማንኛውም ህዝብ ላይ ጦርነት አንከፍትም " ሲሉ ገልጸዋል።

➡️ " ማንኛውም የትግራይ ፓለቲካዊ ፓርቲ ፣ ስቪክ ማህበር እና ህዝቡ ከማንኛውም ህዝብ በላይ በጦርነት የወደመ የተጠቃ ፣  ጦርነት እጅግ አፍራሽ መሆኑ ስለሚያውቅ አሁንም የጦርነት ፍላጎት የለውም " ብለዋል።

➡️ " በትግራይ በኩል ለጦርነት የሚጋብዝ አንድም ምክንያት የለም ። እርግጥ ነው በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ልዩነት እና መሳሳብ አለ።  ይህንንም በሰለጠነ የፓለቲካ አግባብ ይፈታ እንደሆነ እንጂ ወደ ጦርነት የሚመራ ምክንያት ሊሆን አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

➡️ " ያለንን የፓለቲካ ልዩነት በውይይት እና በሰለጠነ የፓለቲካ አግባብ እንፈታዋለን እንጂ ወደ ጦርነት የሚያስገባን አይሆንም " ብለዋል።

➡️ " ከፌደራል መንግስት ጋር የሚያገናኘን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ነው። ስምምነቱ ማእከል በማድረግ የጎደለን ነገር በውይይት ለሞምላት ነው 'እንወያይ ' የሚል ጥሪ እያቀረብን ያለነው። እንወያይ የፕሪቶሪያ ስምምነት ተፈፃሚ ይሁን ፣ ወራሪዎች በሃይል ከያዙት ግዛታችን ይውጡ ፣ የግዛት አንደነታችን ይከበር ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ ፣ የሁለትዮሽ ፓለቲካዊ ውይይት ይጀመር ወደ መደበኛው ህገ-መንግስታዊ  ስርዓት የምንመለስበት ሁኔታ ይፍጠን ብሎ መጠየቅ የጦርነት መንስኤ ሊሆን አይችልም " ብለዋል።

➡️ " የ2013 ዓ.ም ጦርነት ከመጀመሩ ጥቂት ሳምታት ቀደም ብሎ በጠቅላይ ሚንስትሩ የአሁኑ አይነት ተመሳሳይ የፅሁፍ መግለጫ ተሰጥቶ ነበር። ያኔም ' ወደ ትግራይ ማሰክ እንጂ የጥይት ቁምቡላ አንልክም ' ተብሎ ነበር። ቅኔ ነው የነበረው። አሁንም በውጭ ሲታይ ለስላሳ እና ጣፋጭ ውስጡ ሲታይ ግን ' ተጠንቀቁ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ሁኔታ ነው ያለው ' የሚል እንድምታ ያለው ደብዳቤ ነው የተሰራጨው " ብለዋል።

➡️ " ደብዳቤው ሆን ተብሎ ህዝብ ለማሸበር የተደረገ ነው። ይህ በትግራይ ህዝብ ላይ እየቀጠለ ያለውን በደል አካል አድርገን ነው የምንቆጥረው። የትግራይ ህዝብ ማስፈራራት አይገባም። አሁንም ' መጣሁብህ ገደልኩህ ' ማለት ለትግራይ ህዝብ ተገቢ አይደለም። የትግራይ ህዝብ አሁን የሚያስፈልገው የበደል ካሳ ፣ ሰላም ፣ ልማት እና ውይይት ነው  በመሪዎች መካከል የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰለጠነ ውይይት መፍታት ያስፈልጋል " ብለዋል።

➡️ " በአሁኑ ወቅት ህወሓትም ሆነ የትግራይ ህዝብ የጦርነት ፍላጎት የላቸውም። በመላው ትግራይ ጦርነት የሚጋብዝ እንዳች ምልክት የለም። መብታችን ፣ ማንነታችን ይከበርልን ፣ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ሁሉም ነገር ይፈፀም የሚል ግን ጥያቄያችን አስኪመለስ ድረስ የምናቆመው አይደለም  ይህ ዓይነት ጥያቄ በፍፁም የጦርነት መንስኤ ሊሆን አይችልም " ብለዋል።

➡️ " በትግራይ ለጦርነት የሚጋብዝን አንዳች ነገር የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት 50ኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 በጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማክበር እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት በማስመልከት የክልሉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

አቶ ጌታቸው በዚሁ ወቅት በህወሓት አመራሮች መካከላል ባለው ክፍፍል የግጭት ስጋት ስለመኖሩ ጠቋሚ ቃል ሰጥተዋል።

" በአሁኑ ወቅት በትግራይ በማንኛውም ደቂቃ በሆነ ሰው በሚፈጠር ስህተት ለግጭት የሚዳርግ ሁኔታ ሰፍቷል " በማለት ነው ስጋታቸው የገለጹት።

ትግራይ ክልል ከአስከፊው ጦርነት ገና በቅጡ ያላገገመ ሲሆን አሁን ደግሞ ህዝብን በከፍተኛ ስጋት ላይ በጣለ የአመራሮች ክፍፍል እየታመሰ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ፈጣሪ ምን ይሳነዋል ? የማይገመተው በሱ ፍቃድ ሆኗል። በወጣትነቴ ያጣሁትን የልጅ ጥማት በእርጅና ጊዜ መልሶልኛል ፈጣሪ ይመስገን ! ልጄን የማሳድግበት ጤና ይስጠኝ እድሜ ይጨምርልኝ " - በ76 ዓመታቸው ወንድ ልጅ የወለዱት ወ/ሮ መድህን ሓጎስ

የመቐለ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መድህን ሓጎስ በ76 ዓመታቸው ወንድ ልጅ የመታቀፋቸው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።

የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን በእናቲቱ መኖሪያ የተዘጋጀውን የክርስትና ድግስ ላይ ተገኝቶ ያጠናቀረውን ፕሮግራም ከትላንት ጀምሮ በሰፊው ህዝብ ጋር ሲዳረስ ነበር።

እናቲቱ በ76 ዓመታቸው መውለዳቸው በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ያለመ የ ' X ' ዘመቻም አለ።

የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች " እናቲቱ በተለመደው ተፈጥሯዊ መንገድ ነው የውለዱት " ፤ " የለም በህክምና ቴክኖሎጂ በመታገዝ ነው ልጃቸውን የታቀፉት " የሚሉ ክርክሮች በማንሳት ሲፅፉ ታይተዋል።

እናቲቱ በድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን እና ሰግለለት ለተባለ ዩቱብ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የተከራካሪዎቹን ጥያቄ ያልመለሰ ድፍን ያለ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

የመቐለው አባላችን ፤ እናቲቱ በትግርኛ ቋንቋ ለሚድያዎች የሰጡት ቃለ-መጠይቅ እና የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ያገኘውን መረጃ ከታማኝ የመረጃ ምንጭ ጋር ለማቀናጀት ጥረት አድርጓል።

ወ/ሮ መድህን ሓጎስ ከዚህ በፊት ልጅ  እንዳልወለዱ ፤ የአሁኑ የመጀመሪያ ልጃቸው መሆኑን በልጃቸው ክርስትና ቀን በአንደበታቸው አረጋግጠዋል። 

ወ/ሮ መድህን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ፅንሳቸውን እስከ 8 ወር ድረስ ደብቀውት እንደነበር ከመግለፅ ባለፈ በተለመደው መንገድ ነው የወለዱት ወይስ በህክምና የታገዘ የስነ ተዋልዶ ዘዴ (IVF or In Vitro Fertilization) ጥበብ ያሉት ነገር የለም።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከታማኝ ምንጭ ባገኘው መረጃ እናቲቱ የወለዱት በኢንቪትሮ ፈርትላይዜሽን (IVF) ማለትም የወንዱ ዘር እና የሴቷን እንቁላል አውጥቶ ከማህፀን ውጪ በላብራቶሪ ውስጥ እንዲዋሃዱ የሚደረግበት በህክምና የታገዘ የስነ ተዋልዶ ዘዴ መሆኑን ተረድቷል።

ወ/ሮ መድሂን ህክምናውን ለማግኘት ወደ ህንድ ተጉዘዋል።

በዚያው ፅንሱ የ3 ወር ዕድሜ እስኪ ሞላው ድረስ ቆይተዋል።

ከሦስተኛው እስከ ወሊድ ባሉት ጊዜያት የፅንስ ክትትል በመቐለ በሚገኝ አንድ የግል ህክምና ተከታትለው በቀዶ ህክምና ለመውለድ መቻላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

በኢትዮጵያ የወሊድ ህክምና በህግ የተፈቀደው IVF / In Vitro Fertilization የህክምና ጥበብ በመቐለ ጨምሮ በአዲስ አበባ እንደሚሰጥ እየታወቀ እናቲቱ ለምን ውጭ ድረስ ለመጓዝ እንደፈለጉ የታወቀ ነገር የለም።

በ76 ዓመታቸው ልጅ ለማቀፍ የቻሉት ወ/ሮ መድህን ሓጎስ እሳቸውም ልጃቸውም በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።


" ፈጣሪ ምን ይሳነዋል ? የማይገመተው በሱ ፍቃድ ሆኗል። በወጣትነቴ ያጣሁትን የልጅ ጥማት ፤ በእርጅና ጊዜ መልሶልኛል ፈጣሪ ይመስገን። ልጄን የማሳድግበት ጤና ይስጠኝ እድሜ ይጨምርልኝ " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ. በመስረከም 7/2019 የህንድዋ አንድህራ ፕራደሽ ግዛት ተወላጅ የሆኑት ወ/ሮ ማንጋያማ ያራማቲ በ73 ዓመታቸው በIVF ልጅ በማግኘት በእድሜ ትልቋ ተብለው ነበር።

ባለፈው ዓመት ሳፊና ናሙኩዋያ የተባሉ ኡጋንዳዊ ሴት በIVF ህክምና የመንትያ ልጆች እናት መሆን እንደቻሉ በስፋት ተዘግቦ ነበር።

እንደ አንድ የጤና መረጃ አሜሪካ ውስጥ ከሚወለዱት ህጻናት 2% የሚሆኑት በIVF, or  In Vitro Fertilization የህክምና መንገድ ሲሆን ከ8 ሚሊዮን በላይ ህፃናት በዚህ መንገድ ተወልደዋል።

NB. ኢንቪትሮ ፈርትላይዜሽን (IVF) ማለት የወንዱ ዘር እና የሴቷን እንቁላል አውጥቶ ከማህፀን ውጪ በላብራቶሪ ውስጥ እንዲዋሃዱ የሚደረግበት በህክምና የታገዘ የስነ ተዋልዶ ዘዴ ነው። በላብራቶሪ ውስጥ የተፈጠረው ፅንስ በሚፈለገው ደረጃ እድገቱን ከቀጠለ በኋላ ወደ ሴቷዋ ማህፀን በማስገባት የተፈጥሮ እርግዝና ሂደቱን እንዲቀጥል የሚደረግ ይሆናል፡፡

በዚህ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ የጤና ባለሙያ ማብራሪያ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

በእንዳስላሴ ሽረ ከተማ በህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ የእጅ ቦምብ 10 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉደት ደረሰባቸው።

የሰው ህይወት አለማለፉን ለመረዳት ተችሏል።

የቦምብ ጥቃቱ አድራሾች እና ግብረ አበሮቻቸው ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እና ምርመራ እያደረግኩ ነው ብሏል ፖሊስ።

ጥቃቱ መቼና ? የት ? እንዴት አጋጠመ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፤ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞችን አግኝቶ አነጋግሯል።

ጥቃቱ የካቲት 3/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ቀበሌ 05 በሚገኝ የአንድ ግለሰብ የመዝናኛ ስፍራ ነው የደረሰው።

የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ሰሞኑን ከማያወቀው ሰው በሞባይል እየተደወለ የማስፈራርያ መልእክት ይደርሰው እንደነበር ፤ የመልእክቱ አንኳር ነጥብ " እስከ 400 ሺህ ብር እንዲከፍል " ይህንን ካላደረገ ግን አደጋ እንደሚደርስበት የሚገልጽ ማስጠንቀቅያ ነው።

ግለደቡ የማስፈራርያ ዛቻውን በሰዓቱ ለፓሊስ ያደርስ እንደነበረ ነው የተነገረ ሲሆን ጥቃቱ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት ሳይቀር ዛቻውን ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር።

የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ስጋቱ አይሎበት ፓሊስ ጣብያ ድረስ በመሄድ የጉዳዩን አሳሲበነት አስረድቶ ፓሊስ በተባለው አከባቢ ከየካቲት 2/2017 ዓ.ም በመከታተል እያለ ቦምቡ መጣሉ ከከተማው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ ያመልክታል።

የተጣለው ቦምብ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አንድ ሴት የምትገኝባቸው ሦስት ሰዎች ላይ  ከባድ ፡ ሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የከተማው ፓሊስ ተጠርጣሪዎች ከግብረ አበሮቻቸው ጋር ለመያዝ ክትትል እና ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ገልፆ ህዝቡ መረጃ በመስጠት ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።

ከቀናት በፊትም በከተማዋ በአስፋልት ዳር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች አንድ ሰው ተገድሎ መገኘቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አጋርቶናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በእንዳስላሴ ሽረ ከተማ በህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ የእጅ ቦምብ 10 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉደት ደረሰባቸው። የሰው ህይወት አለማለፉን ለመረዳት ተችሏል። የቦምብ ጥቃቱ አድራሾች እና ግብረ አበሮቻቸው ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እና ምርመራ እያደረግኩ ነው ብሏል ፖሊስ። ጥቃቱ መቼና ? የት ? እንዴት አጋጠመ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፤ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞችን…
" 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፖሊስ

በቦንብ ፍንዳታ የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ፓሊስ አስታውቋል።

ትናንት የካቲት 3/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ በአንድ የህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ ቦምብ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ሞት አላጋጠመም።

አደጋው ከተከሰተበት ጀምሮ ከክልል እስከ ወረዳ የተቀናጀ የወንጀል አጣሪ ቡድን አቋቋሞ መንቀሳቀስ መጀመሩ የጠቀሰው ፓሊስ ፤ ከፍነዳታው ጋር በተያያየ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ አስታውቀዋል። 

የቢንጎ ማጫወቻ መሆኑ በተጠቀሰው የህዝብ መዝናኛ ማእከሉ ሰዎች በብዛት እንደሚሰባሰቡበት የጠቀሰው ፓሊስ ባለፈው ጥር ወር በተመሳሳይ ቦንብ ተጥሎ ሳይፈነዳ በመቅረቱ አደጋ አላደረሰም ብሏል።

ፓሊስ " ጥቃቱን አድርሰዋል " በማለት በጠረጠራቸው ሰዎች ላይ ውጤታማ የሆነ የማጣራት በማካሄድ ጉዳዩ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልፆ የህዝቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
" ጊዚያዊ መንግስት ይሁን ጊዚያዊ አስተዳደር ተቀባይነት የለውም ! ... ፃድቃን  ከ93 ዓ.ም ጀምሮ  የCIA አባል በመሆን ህወሓት ለማጥፋት ተንቀሳቅሰዋል  ተው ብለው እምቢ ብሎኛል"  - የህወሓት ታጋይ እና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ

በኢትዮጵያ ፓለቲካ በአነጋጋሪነታቸው የሚታወቁት ከቀንደኞቹ የህወሓት ነባር ታጋዮች አንዱ የሆኑት ከ80 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩት ስብሓት ነጋ የካቲት 11/2017 ዓ.ም የህወሓት 50 ዓመት የትግል ምስረታ ምክንያት በማድረግ የደርጅቱ ልሳን ለሆነው ወይን ጋዜጣ ቃለ-መጠይቅ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ 90 ደቂቃ ያህል ርዝማኔ ያለው የህወሓት ነባር ታጋይ ስብሓት ነጋ በትግርኛ የሰጡት ቃለ-መጠይቅ ተከታትሎታል።

ህወሓት ከተመሰረተ ጀምሮ ውስጣዊ የአመራር መከፋፈል ፈተና እንዳልተለየው የገለፁት አቦይ ስብሓት ነጋ ፥ " በ1969 ዓ.ም  እንደ አንድ የፓለቲካ ድርጅት በተመሰረተ ማግስት ያጋጠመው የአመራር መከፋፈል በመጋዳደል ሳይሆን በፓለቲካዊ ክርክር ነው የፈታው " ብለዋል። 

" ህወሓት ከመመስረትዋ በፊት ሁሉም ይንቁን ነበር " በማለት ይንቁዋቸው የነበሩት በስም ያልጠቀሱት ስብሓት " እንደ ሰው የሚቆጥረን አልነበረም ፤ ' ትግራይ ከበላ ከጠጣ ፓለቲካዊ ስልጣን ምን ይፈይድለታል ? ' የሚለውን ስላቅ የቀየረው ህወሓት ነው " ብለዋል።  

" ህወሓት ሁሌ ተማሪ ህዝባዊ እና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በመሆኑ ይታወቃል ያሉት የቀድሞ ታጋይ " ባለፉት 50 ዓመታት በህወሓት ላይ ያልተሞከረ ክፋት አልነበረም፤ ድርጅቱ ግን ህዝብ መሰረት ያደረገ ትግል በማካሄድ ችግሮቹ ተሻግሮዋቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከ1969 ዓ.ም እስከ 1971 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ኢድዩ (የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት ) የተባለ ፓርቲ ህወሓትን ከገፀ ምድር ለማጣፋት ያለመ ያልተሳካ ዘመቻ ማወጁ ፣ 1977 ዓ.ም ከባድ የአመራር መከፋፈል አጋጥሟት እንደነበረ ያወሱት ስብሓት " ፈተናዎቹ በፅናት እና በዴሞክራሲያዊ ክርክር መታለፍ ችለዋል " ሲሉ አብራርተዋል።    

" ቀደም ሲልም አሁንም ከህወሓት ያፈነገጡት አመራሮች ከጠላት በላይ ጠላት ናቸው " ሲሉ የፈረጁት ስብሃት " ፃድቃን ከ93 ዓ.ም ጀምሮ  የCIA አባል በመሆን ህወሓት ለማጥፋት ተንቀሳቅሰዋል  ፤ ተው ብለው እምቢ ብሎኛል " ሲሉ ከሰዋል። 

ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደ ከሃዲ ፣ ቂመኛ የህወሓት እና የትግራይ መንግስት መዋቅር አፍራሽ መሆኑን በመግለፅ እንደማይቀበሉት እና በፅኑ እንደሚቃወሙት አሳውቀዋል።

ስብሃት " የፌደራሊዝም የፓለቲካዊ አስተዳደር ስርዓት በማሞካሸት ፤ ህወሓት የፌደራል ስርዓት ለማጠናከር ከመሰል የፓለቲካ ፓርቲዎች በማበር እንዲታገል እና ችግሮቹ እንዲፈታ " ብለዋል።

የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ሳይሸራረፍ እንዲተገበር እና እንዲከበር ህወሓት መታገለ እንዳለበተ የተናገሩት ስብሓት " መሪዎች ከህዝብ መነጠል የለባቸውም ፤ ህዝባቸው እንዳይከፋፈል መታገል መምራት አለባቸው የህወሓት ድምፅ ይሰማ " ሲሉ ለወይን ጋዜጣ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም በተካሄደው የትግራይ ጦርነት በፌደራል መንግስት ተማርከው በእስር ከቆዩ በኋላ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ በምህረት የተለቀቁት የቀድሞ የህወሓት ታጋይ እና ከፍተኛ አመራር ስብሓት ነጋ አሁን ለህክምና በአሜሪካ ይገኛሉ።

ስብሓት ነጋ ከ ቀድሞው የደርግ ስርዓት መውደቅ በኋላ የኢፈርት ኢንደውመንት የባለ አደራ ቦርድ  ሰብሳቢ ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሰላም እና ምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተርነት ጨምሮ በበርካታ የስልጣን እርከኖች የቦርድ አባል በመሆን ሰርተዋል።

ህወሓትን በሊቀ-መንበርነት የመሩት ስብሓት ነጋ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ለቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በራሳቸው ፍቃድ የሊቀመንበር ስልጣናቸው አሳልፈው መስጠታቸው በፓርቲያቸው ይነግርላቸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የህወሓት አመራሮች ዛሬ በመቐለ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኝተዋል። የፊት ለፊት ግንኙነቱ በክልሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች የተመራ ነበር። ጥዋት በመቐለ ኖርዘርን ስታር ሆቴል አዳራሽ  የነበረው የፊት ለፊት ውይይት ግማሽ ቀን የፈጀ እንደነበር ታውቋል። የሃይማኖት አባቶቹ ፥ " ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ባቀረብናላቸው ጥሪ መሰረት ተገናኝተው ችግራቸውን በፓለቲካዊ እና በህጋዊ አሰራር እንፈታለን…
#Tigray

" ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች

የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ።

ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ የካቲት 7/ 2017 ዓ.ም በመቐለ በሰጡት መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የሃይማኖት አባቶቹ በመግለጫቸው " አመራሮቹን ለማቀራረብ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ውይይት ስምምነት ላይ አድርሷቸዋል " ብለዋል።

በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ችግር ለመፍታት ከሁለት ወር በላይ ጥረት መደረጉ ያብራሩት የሃይማኖት አባቶቹ መሪዎቹ ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል ሲሉ ገልጸዋል።

አመራሮቹ በመካከላቸው የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ መስማማታቸው አስመልክቶ በሃይማኖት አባቶች የተሰጠው መግለጫ ብዙ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ያላቸው ደስታ እና ድጋፍ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከወራት በፊት ችግሮቻቸው ለመፍታት በሃይማኖት አባቶች ፊት ቢጨባበጡም ጠብ የሚል ለውጥ ማምጣት ባለመቻላቸው ምክንያት ህዝቡን ወደ ከፍተኛ ጭንቀት እና ወጥረት መክተታቸው የሚታወስ ነው።

አሁንስ ቃላቸው ጠብቀው ልዩነቶቻቸው ጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት ለህዝብ አገር እፎይታ ይሰጡ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ 2 ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ህወሓት ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ታገደ። በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ተወስኗል። የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ። ፓርቲው በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት  6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ…
#Update #TPLF

" ቦርዱ ከፌደራል መንግስት ጋር የጀመርነውን ተከታታይ ውይይት ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት  6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር  ፤ ይህንን ባለማድረጉ ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታደግ ፤ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ መወሰኑ ተከትሎ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። 

ህወሓት ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረ አንጋፋ ፓርቲ መሆኑ የገለፅው መግለጫው ፤ " ጥቅምት 23/2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካዋ የፕሪቶሪያ ከተማ የሰላም ውል ከተፈራረመ ጀምሮ ህጋዊነት የተመለሰ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ህወሓትን በአዲስ ህግ እንደ አዲስ ፓርቲ " መዝግቤዋለሁ ማለቱን " አስገራሚ እና ተቀባይነት የሌለው ፤ ፓርቲው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ማግስት ህጋዊነቱ ያረጋገጠ ነው " ብሏል።

" የምርጫ ቦርድ አካሄድ በመሰረቱ ተቀባይነት የሌለው ፤ ህግን መሰረት ያላደረገ ተቀባይነት የሌለው ትርጉም አልባ ውሳኔ ነው " ብሎታል።

" ህወሓት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ተሰጣጥቶ የሰላም ውል የፈረመ ፓርቲ ነው " ያለው ህወሓት ፤ " ከኢፌዲሪ መንግስት ተከታታይ የፓለቲካ ውይይት በማካሄድ ላይ ነን። ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሰላማዊ ውይይቱ ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ " ሲል አቋሙ ግልጿል።

ህወሓት ከኢፌዴሪ መንግስት በተከታታይ በማካሄድ ላይ ያለው ውይይት ውጤታማ በቅርቡ ወደ ፍሬ የሚቀየር መሆኑ የገለፀው ህወሓት " የምርጫ ቦርድ ይህንን መልካም ሂደት የሚፃረር አካሄድ በመሄድ ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል።

የኢፌዴሪ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመተግበር ህገ-መንግስቱ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠየቀው ህወሓት ፥ የምርጫ ቦርዱ ውሳኔ 50ኛው የፓርቲው የምስረታ በዓል ከማክበር እንደማያግደው በመግለፅ " ህዝቡ በዓሉ ለማክበር የጀመረው እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥል " ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ የካቲት 11 በዓል ምን አሉ ?

" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) 50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል በማስመልከት በትግርኛ ቋንቋ ለመላው የትግራይ ህዝብ " የእንኳን አደረሳችሁ " መልእክት አስተላልፈዋል።

በአገር ውስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙት የትግራይ ተወላጆች እና ወዳጆች " ለ50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል እንኳን አደረሳችሁ " በሚል መልዕክታቸውን ያስቀደሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፥ የትግራይ ህዝብ ባለፉት ዘመናት ተጋድሎ ለአገር  ሉአላውነት እና ዳር ደንበር መከበር የከፈለውን መስዋእትነት በታላቅ ክብር አስታውሰዋል። 

በአገራችን ታሪክ ፓለቲካዊ ልዩነቶች በህግ ወይ በመግባባት የመፍታት የዳበረ ልምድ እንዳልነበረ ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ ማህበረሰቡ በየብሄሩ እና አከባቢው የሚፈጠሩት ልዩነቶች በእርቅ እና ሽምግልና መፍታት በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች የተዘወተረ ነው ብለዋል። 

" ይህ ሆኖ እያለ ፓለቲካው ከባህል አፈንግጦ ሁሉም ልዩነቶች በግጭት ብቻ መፍታት ፓለቲካዊ ባህል ሆኖ ለዘመናት ቆይተዋል አሁንም ፈተና ሆኖ ቀጥለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ፓለቲካዊ ልዩነት በውይይት ፣ በእርቅ እና መግባባት ብሎም በህገ -መፈታት አለበት የሚለው አቋም ከለውጡ በኋላ እንደ መንግስት የተያዘ አቋም ነው  ጠቅላአቋመያዝ በዘለለ ሕጋዊ እና ተቋማዊ አሰራር ተበጅቶለት በመተግበር ላይ እንደሚገኝ " ገልፀዋል። 

" አሰራሩ ጅምር ላይ መሆኑ ልብ ማለት ይገባል " ያሉ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ጭቆና በምክክር እና ህጋዊ አሰራር መፈታት በማይችልበት ወቅት የነበረው ብቸኛ አማራጭ ጠብመንጃ በማንሳት ዴሞክራሲ እና እኩልነት ለማስፈን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በማበር የየካቲት 11 ትግል ለማካሄድ መገደዱን አስታውሰዋል። 

" ጠበመንጃ በማንሳት የሚካሄድ የግጭት መንገድ በመሰረቱ የሚደገፍ ባይሆንም በወቅቱ የነበረው ፓለቲካዊ እና ህጋዊ ሁኔታ ግን ጠብመንጃ ለማንሳት የሚያስገድድ ነበር " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ " የካቲት 11 የተቀጣጠለው በጠብመንጃ የታገዘ ፓለቲካዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማቆም ልየነቶች በውይይት ለመፍታት ያለመ በመኖሩ ከሱ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩት ትግሎች ሲነፃፀር ይለያል " ብለዋል።  

ስለሆነም ማንኛውም ልዩነት በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት እና በህጋዊ መንገድ መፍታት የየካቲት 11 ፍሬዎች መሆናቸው መገንዛብ ያሻል ሲሉ አክለዋል።

" ባለፉት የቅርብ ዓመታት ያጋጠሙን መቃቃሮች ለመፍታት የተከተልነው የግጭት  መንገድ ፤ ከየካቲት 11 ዓላማዎች የወጣ መሆኑ ግልፅ ነው ፤ ይሁን እንጂ ከባድ ዋጋ ከፍለንም ቢሆን ወደ ውይይት መመለሳችን የሚደነቅ እርምጃ ነው ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ፓለቲካዊ ልዩነት በጠንጃ ለመፍታት የመፈለግ ዝንባሌ መታየቱ አልቀረም " ብለዋል።

" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በትግራይ አመራሮች መካከል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለውጤት እንዲበቃ ያላቸው መልካም ምኞት ገልፀዋል።

ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ፣ የተስተጓጎለው ልማት ተጠናክሮ በህዝብ ወደ ተመረጠ መንግስት ሽግግር እንዲደረግ  ከልብ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።  

የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በተገለፀው የውውይት መንፈስ ማሰብ ከጀመሩ ፤ ትግራይ ወደ መደበኛ የህገ-መንግስት ስርዓት በመመለስ በሃገረ መንግስቱ ያላትን ተሳትፎ  አጠንክራ  የምትቀጥልበት ጊዜ በጣም አጭር እና ተጨባጭ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

መልካም የየካቲት 11 በዓል እንዲሆንም በፅሁፋቸው ተመኝተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ። ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ…
#Update

" በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት " ቡድን " ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ " መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው " ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል። 

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray

ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል።

በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ያጋጠመ ሞት የለም።

ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ? 

በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት አስተዳዳሪዎች አሉ። አንዱ የቆየ ሲሆን ሌላው ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾመ ነው።

ሁለቱም ማህተም ይዘው በየፊናቸው " እኔ ነኝ ህጋዊ የቀበሌው አስተዳደር " በማለት ህዝቡን ለሁለት መክፈላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ " ህዝቡ አማርሮ እንድንታደገው ጠይቆናል አዛዦቻችንም ይህንን እንድንፈፅም ልከውናል" ያሉ 9 የሰራዊት አባላት ወደ ቀበሌው ደርሰው ሁለቱ አስተዳዳሪዎች ማህተም እንዲያስረክቡ ይጠይቃሉ።

" ታስረክባላችሁ አናስረክም " በሚል እልህ በነዋሪዎች እና የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ይነሳል። ነዋሪውም ደንጋይ መወርወር ይጀምራል። የትግራይ ኃይል አባላትም ጥይት ይተኩሳሉ።

በዚህ መካከል በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው እጁ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ሲገባ ሌሎች 20 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በትግራይ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት የደረሰባቸው አሉ። 

የወረዳው አስተዳደር ለክልሉ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ የካቲት 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 13 ታጣቂዋች ወደ ወረዳው አስተዳደር በመምጣት የጊዚያዊ አስተዳደር ማህተም እና የፅህፈት ቤት ቁልፍ እንዲያስረክቡዋቸው መጠየቃቸውን እና ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር እንዲቆም ጠይቋል።

ከህወሓት ወደ ሁለት መሰንጠቅ በኋላ የክልሉ ዋና ከተማ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የገጠር እና የከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ ስልጣን ያላቸው ሁለት አሰተዳዳሪዎች መስማት የተለመደ ነው።

በአንዳንድ ዞኖች ያሉ ወረዳዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩ እና የደብሪፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት የተሾሙ አስተዳዳሪዎች ለሁለት ተከፋፍለው ይተዳደራሉ።

የትግራይ መሪዎች በተለይም የህወሓት አመራሮች ከዚህ መሰል ህዝብ የሚከፋፍል አደገኛ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች ፤ የትግራይ ኃይል አባላት አንዱን ቡድን ደግፈው ሌላው ቡድን ማውገዝ ተጨማሪ ቀውስ እና ጥፋት ስለሚያስከትል የገለልተኝነት ሚናቸው እንዱወጡ አበክረው እያሳሰቡ ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል። በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። ያጋጠመ ሞት የለም። ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ?  በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት…
#UPDATE

" ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር

" ሃይል በመጠቀም የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ የሚደረግ ህገ-ወጥ እርምጃ ተቀባይነት የለውም " አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ። 

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ የካቲት 13 /2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ ገበሬ ማህበር የትግራይ ኃይል አባላት በነዋሪ አርሶ አደሮች ላይ ያደረሱትን ጥቃት አውግዟል።

" የተወሰኑ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ እየታዘብን ነው " ያለው መግለጫው " በሰሓርቲ ወረዳ የተከሰተው አሳዛኝ ተግባር እንደ አንድ ማሳያ መውሰድ ይቻላል " ብሏል።

" ሰራዊቱ የህዝብ ህልውና ለመጠበቅ እንጂ የአንድ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት የተሰለፈ አይደለም " ያለው ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " ሲል አስጠንቅቋል።

" ማንኛውም የህግ ወይም የአስራር ክፍተት ሲኖር የሚሊሻና የፓሊስ ሃይል ከህዝባቸው በመተባበር የሚፈቱት እና የሚያርሙት እንጂ ሰራዊት ወደ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ማሰማራት የሚያስገድድ ሁኔታ ፈፅሞ እንደሌለ የለም " ሲል ገልጿል።

" ይህንን ህገ-ወጥ አካሄድ የሚያበረታቱ እና የሚያግዙ ፓለቲከኞች እና የሰራዊት አመራሮች አደብ እንዲገዙ " ሲልም አስጠንቅቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia