TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ከነገ ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጠጫ መንገዶች ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ይሆናሉ።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፤ በአዲስ አበባ ከተማ በ2ኛው ዙር ከሚለሙት የኮሪደር መስመሮች መካከል የሲሚት- ጎሮ መንገድ አንደኛው መሆኑ አስታውሷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሲ ኤም ሲ- ፔፕሲ - ጎሮ - መንገድ  ልዩ ቦታው ሳፋሪ መብራት አካባቢ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት አጠገብ የመንገድ ቆረጣ እንደሚከናወን ገልጿል።

ከነገ ጥር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጠጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆኑ አሳውቋል።

አሽከርከሪዎች ይህንኑ አውቀው አማራጭ መንገዶችን  እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተወሰነ።

ከዚህ ቀደም የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑ ተገልጾ ነበር።

በዚህ መሰረት ቁጥራቸው 88,717 የሆኑ ግብር ከፋዮች የህትመት ጥያቄ ማቅረብ መቻላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል፡፡

ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸው ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም በውይይቱ ተወስኗል፡፡

እስከ አሁን ድርስ የህትምት ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የህትምት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተባለ ሲሆን የሲስተም መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሲስተም ማሻሻያዎችን ማከናውን፣ የህትመት እና ስርጭት ተግባራት በሚፈለገው ደረጃ ለማከናወን ተጨማሪ የህትመት ማሽኖችን ወደ ስራ ማስገባት እና አትሞ በፍጥነት ማሰራጨት እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" የመክፈያ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብራችሁን ያልከፈላችሁ እንድትከፍሉ እናሳስባለን " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ " በተለመዶ የጣራና ግድግዳ ግብር እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩን ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ እንድትከፍሉ እናሳስባለን " ብሏል።

በዚሁ መግለጫው ግብሩ የከተማ ቦታና ቤት ግብር በከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 መሰረት የሚሰበሰብ ግብር መሆኑ መገንዘብ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን 429 ሺህ 829 ግብርከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል ብሏል።

የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ግብር ከፋይ ነዋሪዎች ያለቅጣት መክፈያው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከየካቲት 30 በፊት እንዲከፍሉ እና ያልከፈሉ ነዋሪዎች ግን ቅጣቱን ከነወለዱ ለመክፈል እንደሚገደዱ " ገልጸዋል።

አቶ ሰውነት " እናት ፓርቲ ካስተላለፈው መልእክት ጋር በተያያዘ እኛን የሚመለከተን ነገር የለም " ያሉ ሲሆን ለቢሮው የደረሰው ምንም አይነት የፍርድ ቤት እግድም ሆነ መመሪያ አለመኖሩን በመግለጽ " ሰው ጋር መዘናጋት ይታያል ይህ ደግሞ ለቅጣት ሊዳርጋቸው ይችላል በቀረው ጊዜ ክፍያችሁን ፈጽሙ " ሲሉ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር መቆም አይቻልም " - የትራንስፖርት ቢሮ

ወደ አዲስ አበባ ከተለያዩ የአፍሪካ ብሎም ዓለም አገራት እንግዶች እየገቡ ናቸው።

ይህን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017  ዓ.ም  ማታ 12:00  ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ፦
- በኤሌክትሮኒክ ታክሲ ስርዓት (ኤታስ) አገልግሎት የሚሰጡ የሜትር ታክሲ፣
- የላዳ፣
- የታክሲ እና መሰል ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር መቆም እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ በሚከናወነው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎች ምክንያት ከነገ ማለትም ረቡዕ የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ ማለትም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ድረስ :-

1. አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ ፤

2. ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል፤

3. በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር መዘዋወራቸውን እና ስብሰባዎቹ እንደተጠናቀቁ ወደ ቀድሞ ቦታዎቻቸው እንደሚመለሰ የአዲስ አባባ ከተማ አስታዳደር አሳውቋል።

#AU #ADDISABABA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ተያያዥ ስብሰባዎች እስከሚጠናቀቁ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ክልክል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የመሪዎች ጉባኤ እስከሚጠናቅ ድረስ ባሉ ቀናቶች ውስጥ በየትኛውም የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍፁም ክልክል መሆኑን ነው ፖሊስ አሳስቧል።

ትእዛዝ በመተላለፍ ሲንቀሳቀሱ በሚገኙ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ ሆነ ባለ ንብረቶች ላይ እርምጃ እንዳሚወሰድ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia