TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ጉዳይ ወዴት ? በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች እንደሆኑ የገለጹ መኮንኖች ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ' የተዳከመ ' ያሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተነስቶ በሌላ እንዲዋቀር መወሰናቸውን ገልጸዋል። " የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ አሳልፈናል " ብለዋል። " በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ…
🚨#Alert

" የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ! " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን ደግፎ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማፍረስ ፤ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን እና ሰራዊቱን ለመበተን መንቀሳቀስ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ " የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር አስታወቀ።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ጥር 15/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ስም የወጣው መግለጫ አላማውን የሳተ እና ሰራዊቱ ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ ነው ብሏል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " በሰራዊት ከፍተኛ አዣዦች ስም የወጣው መግለጫ እንደማያውቀው በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ያልተለመደ ተግባር ነው " ብሎታል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ " ያልተለመደ ተግባር " ሲል የገለፀውን ውሳኔ አስመልክቶ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን እና ሁኔታውን መርምሮ ዝርዝር ማብራርያ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

" በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።

" ሃላፊነት የጎደለውን ውሳኔው ወደ ታች ለማውረድ ጥድፍያ የተሞላበት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑ ደርሼቤታለሁ " ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ " የሚያስከትለው አደጋው እጅግ ከፍተኛ  መሆኑ በመረዳት ተግባሩ በአስቸኳይ መቆም አለበት " ሲል አስጠንቅቋል።

" መላው የፀጥታ አካላት ህገ-ወጥ ውሳኔው የህዝቡን ችግር የሚያባብስ የጦርነት አዋጅ እና ስርዓት አልበኝነት የሚያስከትል መሆኑ በመገንዘብ በፅናት እንድትቃወሙት ትእዛዙን ተግባራዊ እንዳታደርጉ አስታውቃለሁ " ሲልም አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🚨#Alert

ከደቂቃዎች በፊት ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል።

ንዝሩት በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ተሰምቷል።

ቃላቸውን የላኩልን የቤተሰባች አባላት " ዛሬ በጣም የሚያስፈራ ነበር። ሰሞኑን ድግግሞሹ ቀንሶ ነበር። ዛሬ በድንገት በሚያስፈራ ሁኔታ ነው የተሰማን " ብለዋል።

@tikvahethiopia