TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ዛሬ ምሽትም 4:17 ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል። በተለይም ደግሞ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። ጠንከር ያለ እንደነበረም ጠቁመዋል። ከጋርመንት፣ ጀሞ፣ አራብሳ፣ አያት ፣ ጎተራ፣ አያት 49 ጣፎ ... ሌሎችም አካባቢዎች…
#Update

ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ አፋር፣ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

" ዛሬ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። መጠናቸው ግን ዝቅ ያለ ነው። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ግን በጣም ያስፈራ ነበር። ሁኔታ አለመቆሙ እጅግ አስደንግጦናል ፤ የከፋ ነገር እንዳይፈጠር እያልን በሰቀቀን ውስጥ ነን " ብለዋል።

ከደቂቃዎች በፊት የነበረው መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ከተማ ብዙ ቦታዎች በደንብ ተሰምቷል።

እቃ አንቀሳቅሷል፣ አልጋ ላይ ያሉ ሰዎች ሲንቀሳቁም እንደነበር ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ስሜቱን ያልሰሙ ቦታዎችም ንዝረቱ ተሰምቷል።

" ተሰምቶን አያቅም እኮ " የሚሉ ሰዎችም ዛሬ ምሽት ስሜቱን እያተውታል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የላኩ ቤተሰቦች " ከወትሮ የተለየ ነበር  ድንጋጤን ፈጥሮብናል " ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የሚኖር ነዋሪ " የዛሬው ይለይ ነበር። በተኛሁበት ሲነቃነቅ ተሰምቶኛል ደንግጬ ወደ መሬት ወረድኩ " ብሏል።

ሌላ መልዕክቱን የላከ የቤተሰባችን አባል ፥ ነዋሪነቱ ጃክሮስ እንደሆነ ቪላ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ስለ ንዝረቱን ከዚህ ቀደም በሚዲያ ከሚሰሙት ውጭ በተግሻር ተሰምቷቸው እንደማያውቅ ዛሬ ግን እንደተሰማቸው ገልጿል።

" በጣም ነው ፍራቻ የለቀቀብን " ሲል ሁኔታውን ገልጿል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፥ " ንዝረቱን በደንብ እንደሰሙ ቋቋ የሚል ድምጽም እንደተሰማቸው " ጠቁመዋል።

ሌላኛዋ የመልዕክት ላኪ ቤተሰባችን " የእቃ እንቅስቃሴ እንደነበር ፤ እሷም በተቀመጠችበት መንቀሳቀሷን ፤ በፊት ከነበረው ይለይ እንደነበር " ገልጻለች።

ቱሉዲምቱ ፣ አራብሳ ፣ ጃክሮስ ፣ ጋርመንት ፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ አያት ፣ አያት 49 ፣ ጎሮ፣ አባዶ፣ ካራ፣ ጣፎ፣ ... ከሌሎችም ብዙ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላቱን መልዕክት ተቀብሏል።

ውድ የአፋር እና የሌሎችም የክልል ከተሞች ቤተሰቦቻችን " ሁኔታው የተለመደ ነው " ብላችሁ እንዳትዘናጉ አደራ እያልን በዚህ ሊንክ👇 https://t.iss.one/tikvahethiopia/93268 ያለውን የጥንቃቄ መንገዶች በማስተወሻችሁ ላይ አኑሩት።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ አፋር፣ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል። " ዛሬ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። መጠናቸው ግን ዝቅ ያለ ነው። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ግን በጣም ያስፈራ ነበር። ሁኔታ አለመቆሙ እጅግ አስደንግጦናል ፤ የከፋ ነገር እንዳይፈጠር እያልን በሰቀቀን ውስጥ ነን " ብለዋል። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው መንቀጥቀጥ…
#Update

4:18 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ተመዝግቧል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ልክ 4:18 ላይ ከአዋሽ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አመላክቷል።

ይህ 4.8 ሆኖ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ከተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ ነው።

ትላንትና ሰኞ ከጥዋት አንስቶ የተለያየ መጠን ያላቸው በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበው የነበረ ሲሆን ከፍተኛው 4.8 ነበር።

ዛሬም አዋሽ እና አካባቢው ላይ 4.3 እና ከዚያ በላይ የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ነበሩ።

#TikvahEthiopiaFamilyAfar

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ወቅታዊ ጥያቄያችሁን ሰምተናል ፤ ከሚመለከተው አካል ምላሽ ይሰጥበታል " - የትግራይ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ አመራሮች

ከመቐለ እና አከባቢዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተሰባሰቡ በሺህ የሚሆኑ ወጣቶች የሚበዙባቸው ሰልፈኞች ዛሬ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ወደ ከተማዋ የከንቲባ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ተሰባስበው ነበር።

የአስተዳደሩ ዋና በሮችና ዙሪያው የሚጠብቁ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፓሊሶች በአከባቢው የነበሩ ሲሆን በባነር የተፃፉ መፈክሮች በመያዝና ድምፅ በማሰማት ወደ አስተዳደሩ ህንፃ በተለያዩ አቅጣጫ የተመሙ ሰልፈኞች አንድ ላይ አንዳይሰባሰቡ አድርገዋቸዋል።

በአንዱ አቅጣጫ የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ከከንቲባው ህንፃ ዋና በር በቅርብ ርቀት በመሆን ፦
- ጊዚያዊ አስተዳደሩ አይፈርስም !
- በመንግስት ላይ እምቢታ ያወጁ ሃይሎች ላይ እርምጃ ይወሰድ !
- መንደርተኝነት እና ኋላቀርነት ይወገድ !
- ከፓርቲ መንግስት ይቀድማል !
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የህዝቦች አንድነት ለማፍረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ በጥብቅ እንቃወማለን !
- እምባገነንነት ፣ጭቆናና አፈና አንቀበልም !
- መቐለ የልማት እንጂ የአመፅ መነሃሪያ አይደለችም !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች በድማፃችን ይከበራሉ !
- የአመፅ መሪዎች ወደ ህግ ይቅረቡ !
- እውነተኛ የህዝብ ትግል አይቀለበስም !
- ህዝብ እና እውነት የያዘ ያሸንፋል !
- እናሸንፋለን ! ... የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ከፍ ባለ ድምፅ አሰምተዋል።

የሰልፈኞቹ ጥያቄ ያዳመጡ በቦታው የተገኙ የክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች " ወቅታዊ የሰልፈኞቹ ጥያቄ ከሚመለከተው አካል ምላሽ እንደሚሰጠው " በመንገር ሰልፈኞቹ ወደ መጠቡበት አከባቢ በሰላም እንዲመለሱ አድርገዋል።

በሰልፈኞቹ መካከል ይሁን ከፀጥታ አካላት  ጋር የተፈጠረ ግርግር እና ግጭት እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ቦታው ደረስ በአካል በመገኘት አረጋግጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፃቸው " የትግራይ ትንሳኤ እውን እንዲሆን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሳ " የሚል ይዘት ያለው ፅሁፍ አጋርተዋል።

በተመሳሳይ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እየመከረ ሲሆን ፤ በምክክሩ የዞን እና የክልሉ የፀጥታ አመራሮች ተሳታፊ እንደሆኑ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ይህ መረጃ ተዘጋጅቶ የተላከው በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አክሱም 🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች ➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት 👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም "…
#Update

የፌዴራል መጅሊስ ከቀናት በኃላ ዝምታውን ሰብሮ መግለጫ አወጣ።

ምን አለ ?

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ " አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ከፍተኛ ርብርብና በሃይማኖት አባቶች ዱአ በምናደርግበት በአሁኑ ወቅት በተፃራሪው አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚከሰቱ ሃይማኖታዊ ተንኮሳዎች የመንግስት አካላትን ጨምሮ የስጋት ምንጭ እየሆኑ ይገኛሉ " ብሏል።

ምክር ቤቱ ፥ " በትግራይ ክልላዊ መስተዳደር የአክሱም ከተማ ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን የእምነት አለባበስ (ሂጃብ) አስመልክቶ ትምህርታቸውን በሚጐዳ መልኩ ከአንድ ወር ባላነሰ ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጐሉ አድርጓል " ብሏል።

ከዚህ ባሻገር አንዳንድ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በእስር ያቆዩ በመሆኑ ጉዳዩን ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጋር ሲነጋገርበት መቆየቱን ከአሁን አሁን ሁነኛ መፍትሄ እስኪገኝ በትዕግስት እየጠበቀ እንደሆነ ገልጿል።

ነገር ግን ምንም አይነት እልባት አለመኖሩን በተግባር መረዳት እንደቻለ አመልክቷል።

" የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ለዘመናት የነበረባቸውን የእምነት ነፃነት፣ የመስገጃ ቦታ ችግርና የቀብር ቦታ ችግር እልባት ያልተሰጠበትና ወደ ባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው " ያለው ምክር ቤቱ " የክልሉና የፌዴራል መንግስት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤቶች በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግጋትና በህገ መንግስቱ አንቀጽ 27 መሠረት በዚህ ዘመን በጋራ እምነቶች ተከባብረው በሚኖሩበት አገር እሴቱን የሚሸረሽር ተግባር መፈፀሙን በጥብቅ እናወግዛለን " ብሏል።

በመሆኑም የሙስሊም ማህበረሰብ መብቶች ሳይሸራርፉ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረጉና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ይህንኑ እንዲያስፈጽሙ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

ይህንን ድርጊት በፈፀሙ ግለሰቦች ላይም ህጋዊ እርምጃ እዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል።

የጠቅላይ ም/ቤቱ የህግ ክፍል አስፈላጊውን ክትትል የሚያደርግ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን መላው የሙስሊም ማህበረሰብና ሌሎች የእምነት ተቋማትና ተከታዮች ጉዳዩን እንዲያወግዙና ከአክሱም ሙስሊም ማህበረሰብ ጐን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

ከሰሞኑን የአክሱም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ አድርጋችሁ አትገቡም " በመባላቸው ከትምህርት ገበታቸውን እንዲወጡ መደረጉን መግለጻቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወሰወዳለን "  - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች #ሒጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ዛሬ ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ " የፌደራል…
#Update

" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃዎችን እንስወዳለን "   - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ የተከለከሉ 160 የያዝነው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ካለፈው ጥቅምት 2017 ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች እንዳደረገ ምክር ቤቱ ጠቅሷል።

ትምህርት ቤቱ በያዝነው ሳምንት የትግራይ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህግ እና ደንብ ባልወጣበት ሁኔታ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸው እንዳይማሩ መደረጉ ልክ እንዳልሆነ አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ባለመቀበል ተማሪዎቹ በማስፈራራት እና በማሰር ከእውቀት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉ ምክር ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።

ምክር ቤት ባወጣው የ11 ነጥብ የአቋም መግለጫ፦

1. የሂጃብ ክልከላው በህገ-መንግስት የተቀመጡ የጋራ እና የግል መብቶች የሚፃረር ፣ በትምህርት ሚንስቴር እና በክልሉ መከበር ያለባቸው ደንቦች የጣሰ ነው።

2. የትምህርት ቤቶች ህግ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች የሚፃረር መሆን የለበትም። በትምህርት ሚንስቴር ደንብ ቁጥር -6 ንኡስ ቁጥር -3 ሂጃብ መልበስ እንደሚፈቅድ በግልፅ ተደንግጓል ስለሆነም ጥያቄያችን በዚሁ ደንብ በአስቸኳይ እንዲመለስ እንጠይቃለን።

3. ትግራይ አሁን ባለችበት ፓለቲካዊ ቀውስ በሃይማኖት ምክንያት ሌላ ቀውስ መጨመር ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስልን።

4. በጦርነቱ ምክንያት ከእውቀት መአድ ርቀው የነበሩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲበረታቱ የሚገባቸው ሙስሊም ሴቶች ማበረታታት ሲገባ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከትምህርት ገበታ መከልከል ፍፁም ኢ-ህጋዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን።

5. ጉዳዩ በማንኛውም መልኩ ለፓለቲካ ፍጆታ መጠቀምያ ማዋል ስለማይገባ ጉዳዩ እንዳይፈታ የሚያወሳስቡት ግለሰቦች ወይም አካላት መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው ጥሪ እናቀርባለን።

6. ኢ-ህገመንግስታዊ  ተግባሩን የሌሎች እምነት ተከታዮች እና የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች እንዲያወግዙት ጥሪ እናቀርባለን።

7. ከትምህርት ገበታ የተስተጓጎሉት ተማሪዎች የትምህርት ሚንስቴር ያወጣው ሁሉም ትምህርት ቤቶች መፈፀም የሚገባቸው የአለባበስ ሁኔታ የሚመለከት ህግና ደንብ ያልጣሱ ስለሆነ ትምህርታቸው እንዲቀጥሉ እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን።

8. ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ እየተደረገ ያለው ተግባር ሰብአዊ መብቶች ፣ ክልላዊ ፣ አገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ህጎች የሚፃረር በመሆኑ በጥብቅ እንኮንነዋለን።

9. ከትምህርት ሚንስቴር መመሪያ እና ደንብ ባፈነገጠ መልኩ በግል ፍላጎት ብቻ በመመራት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ህገ-ወጥ ተግባር የፈፀሙት ግለሰቦች እና አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጥሪ እናቀርባለን።

10. የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ የተደረገው ህገ-ወጥ ተግባር እንዲወገዝ ድጋፍ የቸራችሁ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ምክር ቤቱ ምስጋና ያቀርባል።

11. ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች ለህዝባችን እናሳውቃለን።

... ብሏል።

መረጃውን የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። ቤት ውስጥ ፣ አልጋ ላይ፣ ከቤት ውጭ የነበሩ ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል። ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም በመቀጠሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘናጉ። @tikvahethiopia
#Update

ከጥቂት ከደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ነው።


ዛሬ በተለያየ ሰዓት አምስት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የአሁኑ ለስድስተኛ ጊዜ የተከሰተው (በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካው ) በመጠን ከፍተኛው ነው።

ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ላይ በደንብ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🚨 “ ግብረሰዶም ወደ ሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል” -  በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ ➡️ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ኑሮን ለማሻል በሚል ወደ ታይላንድ የሄዱና በኃላም ወደ ማይናማር የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን በጋንግስተሮች እጅ ወድቀው ከውላቸው ውጪ  ህገወጥ የዶላር ማጭበርበር…
#Update

“ ከ29 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ኮሚቴ

በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲያስወጣቸው በተደጋጋሚ እየተማጸኑ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ፣ “ ግብረሰዶም ወደማፈጸምበትና ኩካሊት እያወጡ የሚሸጡ ሰዎች ወዳሉበት ካምቦዲያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ስጋቱን ገልጾልን ነበር።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅነው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ልጆቹ ያሉበት ቦታ አዳጋች እንደሆነ፣ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት አለመኖሩ ሁኔታውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ መቆየቱ አይዘነጋም።

ከቶኪዮ ኤምባሲ ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም ገልጾ የነበረው ሚኒስቴሩ ከዚያ በኋላ ላቀረብለት ጥያቄ፣ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” ቢልም እስካሁን ያለው ነገር የለም።

አሁንስ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የወላጆች ከሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ከ29 በላይ የማሆኑ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ አገር ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” ብሏል።

በመሆኑም ልጆቹ ካሉበት ስቃይ እንዲወጡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ ቢሯዎቻቸውን እያንኳኳ በደብዳቤ ጭምር እየተማጸነ መሆኑን ገልጾ፣ መንግስት አሁንም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።

ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?

“ ምንም መፍትሄ የለም። እንዲያውም የተወሰኑ ልጆችን ወደሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋልና ያን የሰሙ ልጆች በጣም ተረብሸዋል።

ወደ ካምቦዲያ እየሸጧቸው ነው ስለተባለ ተጨናንቀዋል። በየቀኑ ‘ምን አዲስ ነገር አለ?’ ነው የሚሉን። እኛም ውጪ ጉዳይን አሳስበን መፍትሄ በመጥፋቱ አሁን የሃይማኖት ተቋማትን እየተማጸንን እንገኛለን።

ልጆቹን በማይናማር ከነበሩበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ እየሸጧቸው ነው። ይሄ ነው ችግር የሆነው። በየጊዜው አዲስ ነገር ነው የሚሰማው በጣም ይጨንቃል።

ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምንም አዲስ ነገር የለም። አሁንም ተሰባስበን ልንሄድ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እየተማጸንን ነው።

ዱኣ አድርጉ፤ ጾም ጸሎት ይታወጅ ብለን እየጠየቅን ነው።

ሀገራቱንም፣ ህዝብንም፣ ቤተሰብንም መጥቀም የሚችሉ የተማሩ ልጆቻችን ስቃዬ ላይ እያሉ ውጪ ጉዳይ ሰምቶ ዝም ከማለት ያስቸገረው ነገር ካለም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትም ሄደን ነበር ለቅሬታ ሰሚ ክፍል ጥያቄያችንን በኢሜይል እንድናስገባ ነው የነገሩን። ግን በኢሜይል ብቻ አስገብተን አንቀመጥም ደብዳቤም እንወስዳለን ”
ብሏል።

(ጉዳዩን እስከ መጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Update

በነገው ዕለት ፓርላማው በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግና ፍትህና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ፥ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሏል። 

ከንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦

" #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል። "

የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ለመደንገግ ከተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦

" የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 50 ሺህ እስከ ብር 100 ሺህ የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል።

መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል እስከ 3 ዓመት እስርና እስከ 300 ሺህ ብር ቅጣት ያስጥላል። "


🔴 ስለ ንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ቀደም ያጋራናችሁን ዝርዝር መረጃና ሰነድ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88315

🔵 ስለ ነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓት ስለሚደነግገው ረቂቅ አዋጅ ያጋራናችሁ ዝርዝር መረጃ ደግሞ በዚህ ይገኛል ፦
https://t.iss.one/tikvahethiopia/92370?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በትግራይ ክልል ፤ አክሱም ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ መከልከል ጋር ተያይዞ የተከሰተው ውዝግብ አሁንም መቋጫ አላገኘም።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጉዳዩ በማስመልከት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ በሰጠው መግለጫ " የመብት ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃ እንወሰዳለን " ብሎ ነበር። 

በመግለጫው  " የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን " ማለቱም ይታወሳል ።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዛሬ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አክሱም ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጠው ፤ ከምክር ቤቱ መግለጫ በኋላ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወደ አክሱም በማምራት ከትምህርት ቤቱ አመራሮች ፣ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ተወያይተዋል።

የመረጃ ምንጫችን " ውይይቱ መሬት ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አላመጣም "  ብሏል። 

" የቢሮ ሃላፊው የትምህርት ሚንስቴር ህግ ፣ መመሪያ እና ደንብ መሰረት ያደረገ ትእዛዝ መስጠት ሲገባቸው ፤ ጉዳዩን ለማሸማገል ያደረጉት ጥረት ተጎጂ ተማሪዎቹ መታደግ አልቻለም " ሲል አክሏል።

ስለሆነም ችግሩ በቀጣዩ ቀናት መፈታት ካልተቻለ 160 የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች እጣ ፈንታ አደጋ ላይ ይወድቃል ሲል የመረጃ ምንጩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተናግሯል።

የመቐለ ቲክቫህ አባል ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ቅርበት ካላቸው ወገኖች ባገኘው መረጃ ደግሞ ከውዝግቡ ጋር በተያያዘ ይሁን ለሌላ ስራ ጉዳይ ነገ የፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ የሃይማኖት አመራሮች መቐለ ትግራይ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባዔ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት ተቃውሞ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በተጨማሪ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅንም አጽድቋል፡፡ አዋጁ በሶስት ተቃውሞ ፣በአራት ድምፅ ተአቅቦ ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የጉምቱው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሃብት (የኢኮኖሚ) ሊቅ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል።

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ የአስክሬን ሽኝት ይደረጋል።

ከሽኝቱ በኋላ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ዊንጌት አካባቢ በሚገኘው በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ስርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል።

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መስራቾች አንዱ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ፓርቲው መላው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ከቤታቸው ለገጣፎ አንስቶ በሚደረገው ሽኝት እና በስርዓተ ቀብራቸው ላይ እንዲገኝ ጥሪ አቅርቧል።

ኦፌኮ አቶ ብልቻ ደመቅሳን " የሀገር ዋርካ " ሲል ገልጿቸው በህልፈታቸው ሀዘን ላይ መሆኑን ገልጿል።


@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA 🔥 በአሜሪካ ፤ በሎስ አንጀለስ ታሪክ አውዳሚ ነው በተባለ የሰደድ እሳት እስካሁን በውል ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ ፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል። እሳቱ በሎስ አንጀለስ ከተማ በብዙ ስፍራ እየተዛመተ ነው ተብሏል። የሰደድ እሳቱ የሆሊውድ ምልክት በሚገኝበት የሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ እየተያያዘ መሆኑ ተነግሯል። በሎስ አንጀለስ እና በአጎራባች ግዛቶች ቢያንስ 5 ሰደድ እሳቶች የተያያዙ ሲሆን ሶስቱን…
#Update

እስካሁን ድረስ መቆጣጠር ባልተቻለው የአሜሪካ፣ ሎስ አንጀለስ  ሰደድ እሳት ምክንያት ቢያንስ 16 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

የበርካታ ሰዎች ቤት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

ሰደድ እሳቱ ያደረሰው ውድመት 135 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ከዚህም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።

እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢቀጥልም ዝነኛ ወደሆነውና የአሜሪካ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወደሚሰሩበት " ሆሊዉድ " እየተቃረበ ነው ተብሏል።

በቀጣይ ቀናት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኛነት መተንበይ ባይቻልም ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ወይም ለመውጣት እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ ጥር 5/2017 ዓ.ም ተፈናቃዮች " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ የሚደግፍ መግለጫ አውጥተዋል። 

" ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን በሚል መሪ ቃል በተፈናቃዮች የተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቀናና የሚደገፍ " ብሎታል ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው። 

" የተፈናቃዮች መከራ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም " ያለው መግለጫው " የፌደራል መንግስት የገባው ውል እና ቃል በመተግበር ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለበት " ሲል በአፅንኦት ገልጿል።

" አሁንም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከአገር መከላከያ ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ይውጡ " ሲልም አክሏል።

" በህገ-መንግስቱ ማእቀፍ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለባቸው "ም ብሏል።

" የአፍሪካ ህብረት ፣ የአሜሪካ መንግስት ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የህዝቡ ድምፅ በማዳመጥ የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ጫናቸው እንዲያሳድሩ " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

" ፅላል ስቪክ ማሕበር ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ " የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር ያስተባበረውና " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ መንገድ በመዝጋት የተጀመረው የተፈናቀዮች ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ጥር 7/2017 ዓ.ም እንደሚቀጥል ታውቋል።

ዛሬ በርካታ የመቐለ ጎዳናዎች ተዘግተው በርካታ የፖሊስ አባላትም ተሰማርተው ነው የዋሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia