TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

በነገው ዕለት ፓርላማው በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግና ፍትህና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ፥ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሏል። 

ከንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦

" #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል። "

የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ለመደንገግ ከተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦

" የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 50 ሺህ እስከ ብር 100 ሺህ የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል።

መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል እስከ 3 ዓመት እስርና እስከ 300 ሺህ ብር ቅጣት ያስጥላል። "


🔴 ስለ ንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ቀደም ያጋራናችሁን ዝርዝር መረጃና ሰነድ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88315

🔵 ስለ ነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓት ስለሚደነግገው ረቂቅ አዋጅ ያጋራናችሁ ዝርዝር መረጃ ደግሞ በዚህ ይገኛል ፦
https://t.iss.one/tikvahethiopia/92370?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በትግራይ ክልል ፤ አክሱም ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ መከልከል ጋር ተያይዞ የተከሰተው ውዝግብ አሁንም መቋጫ አላገኘም።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጉዳዩ በማስመልከት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ በሰጠው መግለጫ " የመብት ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃ እንወሰዳለን " ብሎ ነበር። 

በመግለጫው  " የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን " ማለቱም ይታወሳል ።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዛሬ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አክሱም ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጠው ፤ ከምክር ቤቱ መግለጫ በኋላ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወደ አክሱም በማምራት ከትምህርት ቤቱ አመራሮች ፣ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ተወያይተዋል።

የመረጃ ምንጫችን " ውይይቱ መሬት ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አላመጣም "  ብሏል። 

" የቢሮ ሃላፊው የትምህርት ሚንስቴር ህግ ፣ መመሪያ እና ደንብ መሰረት ያደረገ ትእዛዝ መስጠት ሲገባቸው ፤ ጉዳዩን ለማሸማገል ያደረጉት ጥረት ተጎጂ ተማሪዎቹ መታደግ አልቻለም " ሲል አክሏል።

ስለሆነም ችግሩ በቀጣዩ ቀናት መፈታት ካልተቻለ 160 የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች እጣ ፈንታ አደጋ ላይ ይወድቃል ሲል የመረጃ ምንጩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተናግሯል።

የመቐለ ቲክቫህ አባል ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ቅርበት ካላቸው ወገኖች ባገኘው መረጃ ደግሞ ከውዝግቡ ጋር በተያያዘ ይሁን ለሌላ ስራ ጉዳይ ነገ የፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ የሃይማኖት አመራሮች መቐለ ትግራይ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባዔ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት ተቃውሞ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በተጨማሪ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅንም አጽድቋል፡፡ አዋጁ በሶስት ተቃውሞ ፣በአራት ድምፅ ተአቅቦ ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የጉምቱው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሃብት (የኢኮኖሚ) ሊቅ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል።

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ የአስክሬን ሽኝት ይደረጋል።

ከሽኝቱ በኋላ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ዊንጌት አካባቢ በሚገኘው በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ስርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል።

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መስራቾች አንዱ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ፓርቲው መላው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ከቤታቸው ለገጣፎ አንስቶ በሚደረገው ሽኝት እና በስርዓተ ቀብራቸው ላይ እንዲገኝ ጥሪ አቅርቧል።

ኦፌኮ አቶ ብልቻ ደመቅሳን " የሀገር ዋርካ " ሲል ገልጿቸው በህልፈታቸው ሀዘን ላይ መሆኑን ገልጿል።


@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA 🔥 በአሜሪካ ፤ በሎስ አንጀለስ ታሪክ አውዳሚ ነው በተባለ የሰደድ እሳት እስካሁን በውል ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ ፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል። እሳቱ በሎስ አንጀለስ ከተማ በብዙ ስፍራ እየተዛመተ ነው ተብሏል። የሰደድ እሳቱ የሆሊውድ ምልክት በሚገኝበት የሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ እየተያያዘ መሆኑ ተነግሯል። በሎስ አንጀለስ እና በአጎራባች ግዛቶች ቢያንስ 5 ሰደድ እሳቶች የተያያዙ ሲሆን ሶስቱን…
#Update

እስካሁን ድረስ መቆጣጠር ባልተቻለው የአሜሪካ፣ ሎስ አንጀለስ  ሰደድ እሳት ምክንያት ቢያንስ 16 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

የበርካታ ሰዎች ቤት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

ሰደድ እሳቱ ያደረሰው ውድመት 135 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ከዚህም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።

እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢቀጥልም ዝነኛ ወደሆነውና የአሜሪካ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወደሚሰሩበት " ሆሊዉድ " እየተቃረበ ነው ተብሏል።

በቀጣይ ቀናት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኛነት መተንበይ ባይቻልም ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ወይም ለመውጣት እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ ጥር 5/2017 ዓ.ም ተፈናቃዮች " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ የሚደግፍ መግለጫ አውጥተዋል። 

" ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን በሚል መሪ ቃል በተፈናቃዮች የተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቀናና የሚደገፍ " ብሎታል ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው። 

" የተፈናቃዮች መከራ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም " ያለው መግለጫው " የፌደራል መንግስት የገባው ውል እና ቃል በመተግበር ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለበት " ሲል በአፅንኦት ገልጿል።

" አሁንም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከአገር መከላከያ ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ይውጡ " ሲልም አክሏል።

" በህገ-መንግስቱ ማእቀፍ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለባቸው "ም ብሏል።

" የአፍሪካ ህብረት ፣ የአሜሪካ መንግስት ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የህዝቡ ድምፅ በማዳመጥ የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ጫናቸው እንዲያሳድሩ " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

" ፅላል ስቪክ ማሕበር ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ " የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር ያስተባበረውና " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ መንገድ በመዝጋት የተጀመረው የተፈናቀዮች ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ጥር 7/2017 ዓ.ም እንደሚቀጥል ታውቋል።

ዛሬ በርካታ የመቐለ ጎዳናዎች ተዘግተው በርካታ የፖሊስ አባላትም ተሰማርተው ነው የዋሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #Axum

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

" ያልተመዘገበ አይፈተንም " ማለቱ ይታወሳል።

ከሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ውዝግብ ባለመግባባት ተቋጭቷል።

159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።

ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተለው የቆየው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጥር 6 ቀን 2017 ከሰዓት በኋላ ወደ አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር  ስዩም ካሕሳይ ደውሎ አግኝቷቸዋል።

ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" - በትምህርት ቤታችን ከተለመደው የአለባበስ ስርዓት የተለየ የተሰጠ የአለባበስ ትእዛዝ የለም።

- ሴት ሙስሊም ተማሪዎቻችን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከትምህርት ቤቱ አመራር በአካል በመምጣት እንዲወያዩ ማስታወቅያ በመለጠፍና ስልክ በመደወል ጥረት ተደርጓል ለመምጣት ፍቃደኛ ኣይደሉም።

- የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ጉዳዩ እንዲረግብ ከትምህርት ቤታችን ፣ ከከተማዋ ከንቲባ ከአገር ሽማግሌ እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ሰላማዊ ልመና ቢቅርብላቸውም ጉዳዩ ለማርገብ ፍቃደኛ አልሆኑም።

- በአጠቃላይ የፈተና ፎርም ያለ መሙላትና ያለ መፈተን ፍላጎቱ ከተማሪዎቻች ፍላጎት ውጪ የውጭ ተፅእኖ እና ግፊት አለበት።

- ልጆቻችን በቀላሉ በመግባባት ሊፈታ በሚችል ጉዳይ ከፈተና ውጪ መሆናቸው እንደ ርእሰ መምህርና ወላጅ እጅግ እሞኛል አበሳጭቶኛል " ... ብለዋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ታህሳስ 22 ቀን 2017 ከህገ-መግስት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ክልከላ ውጪ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ " እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ  ፥ " ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎችን ለህዝባችን እናሳውቃለን " ማለቱ ይታወሳል። 

ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ጥያቄዎቹ በሚመለከተው አካል ጀሮ ዳባ ልበስ መባላቸውን በማረጋገጡ በታህሳስ 30 ቀን 2017 ባወጣው አጭር መግለጫ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ክስ መመስረቱ ግልጽ አድርጓል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አመራሮች ስለ ጉዳዩ አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጡ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

ከ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጭ የሆኑት 159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ወዴት ያመራ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " - ባለስልጣናት በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 24 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ደግሞ የገቡበት አይታወቅም። በሎስ አንጀለስ ዙሪያ 3 አካባቢዎች መቃጠላቸውን ቀጥለዋል። በአሁኑ ላይ ትልቁ እሣት ሚገኘው በፓሊሳድስ ሲሆን 9307 ሔክታር መሬትን ሲያቃጥል 11 በመቶውን መቆጣጠር…
#Update

በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ከፍተኛ ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን እሳቱ አሁንም ሎስ አንጀለስን ማንደዱን ቀጥሏል።

እሳቱ እስካሁን ካደረሰው ውድመት በላይ ሊያደርስ ይችላል ተብሏል።

በአካባቢው ያለው የንፋስ ሁኔታ እሳቱን እያባባሰው ነው ተብሏል።

ከተነሱት ሰደድ እሳቶች አንዱን ብቻ ነው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለው።

ባለስልጣናት
#ቀጣዮቹ ንፋሶች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የንፋስ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ በማለት መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

እስከ ትላንት ባለው 24 ሰዎች ሲሞቱ 16 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።

የግል ትንበያ ተቋም የሆነው " አኩዌዘር " እስከ ትላንት ባለው በእሳት ቃጠሎ የተነሳ የደረሰው ኪሳራ ግምት ከ250 እስከ 275 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ ጥር 5/2017 ዓ.ም ተፈናቃዮች " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ የሚደግፍ መግለጫ አውጥተዋል።  " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን በሚል መሪ ቃል በተፈናቃዮች የተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቀናና የሚደገፍ " ብሎታል ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው።  " የተፈናቃዮች መከራ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም " ያለው መግለጫው…
#Update

" ያለፈው ይብቃ አሁን የተጣለባችሁን ሃላፊነት በአስቸኳይ ፈፅሙ " - ተፈናቃዮች

" ይበቃል ! ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል መቐለ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ አበቃ።

ሰልፉ 3 ተከታታይ ቀናት የተካሄደ ሲሆን የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።

በዚህም ተፈናቃዮች " የፌደራል መንግስት ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ታማኝ እና ተገዢ በመሆን ስምምነቱን በሙሉነት እንዲያስፈፅም " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የፕሪቶሪያ የሰላም ውል እንዲፈረም ያሳየው ቁርጠኝነት ተግባራዊ እንዲሆንም ሚናውን ማጉላት አለበት ብለዋል።

ሰልፈኞቹ የትግራይ ክልል የቀድሞ ይዞት በህገመንግስቱ መሰረት ወደነበረበት እስከሚመለስ ሰላማዊ ተቃውሞ ማሰማታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በተለይ ደግሞ ለሁለት የተሰነጠቁት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ለስልጣን እና ወንበራቸው ሲሯሯጡ የተፈናቃዮች ስቃይ መዘንጋታቸው በምሬት የነቀፉት ሰልፈኞቹ " ያለፈው ይብቃ አሁን የተጣለባችሁ ሃላፊነት በአስቸኳይ ፈፅሙ " በማለት ጥሪ አቅርበዋል ።

" ይበቃል ! ወደ ቄያችን መልሱን ! " ሰላማዊ የተቃውሞ ስልፍ ተሳታፊዎች ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፣ ለህወሓት እንዲሁም በክልሉ ለሚገኙ የተለያዩ የተባበሩት መንግስት የእርዳታ ድርጅቶች የአቋም መግለጫቸው አድርሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMeKelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሂጃብሂጃብ #አክሱም " ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ #እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ ታዟል " - ፍርድ ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎችን ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ክልከላ አድርገዋል በተባሉት አካላት ላይ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህጋዊ ክስ…
#Update

🧕" የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ በመጣስ አሁንም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች / ልጆቻችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይገቡ ከልክሏል "  - የተማሪዎች ቤተሰቦች

👉 " የተጣሰ የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የለም ፤ የትምህርት ህግ እና ደንብ ያከበሩ ተማሪዎች ወደ ክፍል ገብተው መማር ጀምረዋል ፤ ቀሪዎቹ እንዲመለሱ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ነን " -  የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር

የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ጥር 6/2017 ዓ.ም በፃፈው የእግድ ትእዛዝ ሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ ሂጃባቸው ለብሰው እንዲማሩ ፤ በክልከላ የተሳተፉ አካላት ለጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ ቢያዝም ተግባራዊ አልሆነም ብለዋል የተማሪዎች ቤተሰቦች።

የተማሪ ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ (መቐለ) በሰጡት አስተያየት ፤ " የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተማሪዎች የሂጃብ መልበስ ክልከላ ጋር በተያያዘ በአክሱም ከተማ ፍርድ  ቤት በኩል በ5 አካላት ላይ የእግድ ደብዳቤ ቢያፅፍም ተግባራዊ አልሆነም ተጥሷል " ብለዋል። 

የእግድ ትእዛዙን ከጣሱት አንዱ የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሆኑን የጠቀሱት የተማሪ ቤተሰቦች ፤ " ትምህርት ቤቱ የእግድ ትእዛዙን በመጣስ ጥር 7 እና 8/2017 ዓ.ም ተማሪዎቹ ክፍል ገብተው እንዳይማሩ በማድረግ ተደራራቢ ጥፋቶች እየፈፀመ ነው " ሲሉ ከሰዋል። 

አስተያየት ሰጪዎቹ  " ከህግ በላይ መሆን ልክ አይደለም የፍርድ ቤት ትእዛዝ እና የሃይማኖት መብት ይከበር " ሲሉ ምሬታቸው ገልፀዋል። 

በተማሪዎች ቤተሰቦች በኩል ለቀረበው አስተያየት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ምላሽ የሰጡት የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ፥ " ትምህርት ቤታችን ' የፍርድ ቤት እግድ እና ትእዛዝ በመጣስ ተማሪዎቹ እንዳይማሩ ከልክሏል ' የሚባለው ስህተት ነው " ብለዋል።   

" ለተማሪ ሴት ልጆቻችን በቅርብ እና በሩቅ ሆኖው ' እንቆረቆራለን ' ከሚሉት በላይ እናስብላቸዋለን " ያሉት ርእሰ መምህሩ " አሁንም ጉዳዩ ከሚገባው በላይ ማጋነን እና ማቀጣጠል እንዲሁም ለፓለቲካዊ ፍጆታ ማዋል ለአገር እና ህዝብ አይጠቅምም " ሲሉ አብራርተዋል።  

" የትምህርት ቤታችን አስተዳደር የፍርድ ቤት ትእዛዝ እና እግድ ሳይጠብቅ የተፈጠረው አለመግባባት እንዲፈታ ሌት ተቀን በመስራት ላይ እንገኛለን " ሲሉ ገልጸው " የፍርድ ቤቱ ቃል አክብረን የትምህርት ቤቱ መምሪያ እና ደንብ በመጠበቅ ጥቂት የማይባሉ ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መልሰናል የተቀሩት ለመመለስ ደግሞ በማያቋርጥ ጥረት ላይ እንገኛለን " ብለዋል።

" ከ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ የቀሩት እንዲካተቱ ከሚመለከታቸው አካላት ተከታታይ ስራዎች እየሰራን " ሲሉ አክለዋል።   

ከሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ ከ2017 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲቀሩ  የሆኑት 159 የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ጉዳይ ክልላዊ እና አገራዊ አጀንዳ ከመሆን በዘለለ በህግ እንዲታይ ወደ ፍርድ አምርቷል።

ከሂጃብ አጠቃቀም ክልከላ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው በተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ 5 አካላት ለጥር 16/2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ ፤ ጎን ለጎን ደግሞ ሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ ሂጃባቸው ለብሰው ትምህርታቸው እንዲቀጥሉ የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ጥር 6/2017 ዓ.ም አዟል።  

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ጥር 8/2017 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በፃፈው ደብዳቤ ፤ የሂጃብ መልበስ ክልከላው እንዲያነሳ አሳውቋል።

በተያያዘ መረጃ ከሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ጋር ተያይዞ ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይገቡ መከልከሉ ለመቃወም የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለዓርብ ጥር 9/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ እንዲካሄድ የጠራው እና የተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ የጥምቀት በዓል ዋዜማ በመሆኑ ምክንያት ወደ ጥር 13/2017 ዓ.ም ማዘዋወሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ  ከምክር ቤቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TikTok📱 ' ቲክቶክ ' አሜሪካ ውስጥ ከእሁድ ጀምሮ እስከ ወዲያኛው እንዲዘጋ ወይም እንዲሸጥ የሚለውን ውሳኔ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደገፈ። ዛሬ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ' ቲክቶክ ' በአሜሪካ እንዲዘጋ ካልሆነም እዲሸጥ ለሚጠይቀው የፌደራል ህግ ድጋፍ ሰጥቷል። ' ቲክቶክ ' ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ ሆናል። ከዚህ ቀደም መተግበሪያው " የአሜሪካውያንን የግል መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ይሰጣል…
#Update : ቲክቶክ በመጪው እሁድ በአሜሪካ አገልግሎቱን እንደሚያቆም አስታውቋል።

ቲክቶክ የተጣለበት እገዳ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር ከመጪው እሁድ ጀምሮ መተግበሪያውን በአሜሪካ ለማቆም እንደሚገደድ ገልጿል።

ኩባንያው በሰጠው መግለጫ ዋይት ሃውስ እና የፍትህ ዲፓርትመንት " ቲክቶክ በቀጣይነት እንዲቀጥል ለማህበራዊ ሚዲያው መሰረታዊ የሚባሉ ግልጽነት እና ማረጋገጫ መስጠት ተስኗቸዋል " ብሏል።

መንግሥት የተጣለበትን እገዳ በመጣሱ እንደማይቀጣ ጣልቃ ገብቶ ማረጋገጫ ካልሰጠው በስተቀር ቲክቶክ " ነገ እሁድ  መተግበሪያውን ለማጨለም እገደዳለሁ " ሲል ይፋ አድርጓል።

170 ሚሊዮን ተጠቃሚ ያለው ቲክቶክ እስከ ነገ ድረስ ካልተሸጠ በስተቀር በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዳይውል የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትላንት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

እገዳው አስቀድሞ በስልካቸው ላይ ቲክቶክን የጫኑ ተጠቃሚዎችን አይጎዳም የሚል እሳቤ ነበር ፤ ነገር ግን እገዳው ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ የመተግበሪያው ማሻሻያዎች አያገኙም በዚህም የማህበራዊ ሚዲያው በጊዜ ሂደት ከጥቅም ውጭ ይሆናል ተብሎ ነበር።

ሆኖም ቲክቶክ ባወጣው መግለጫ ለነባር ተጠቃሚዎችም ሆነ መተግበሪያውን አውርደው መጫን ለሚፈልጉ አዳዲስ ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ አገልግሎቱን እንደሚያቆም ጠቁሟል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው " -  የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የታገቱት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከምን ደረሰ ? የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ፦ " በህገወጥ ዓለምአቀፍ ደላሎች ተታለው ወደ ማይናማር ፣ ታይላንድ፣ ቻይና ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ወደሚገኙ ህገወጥ ካምፓች ተወስደው የሚገኙ ዜጎችን ለማስመለስ በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶች ቀጥለዋል። ጉዳዩ…
#Update

🚨“ በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ

ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰጠው መግለጫ በመነሳት፣ “ አንዳንድ ሚዲያዎች መንግስት በማይናማር የታገቱ ዜጎችን አስለቀቀ ” በማለት መዘገባቸው ስህተት መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የታጋቾቹ ቤተሰቦች በዝርዝር ምን አሉ ?

“ አጋቾች  ያገቷቸውን ልጆቻችንን ‘መንግስት አስለቀቀ’ መባሉ ትክክል አይደለም።

አጋቾቹ ሲቀጧቸው የተጎዱ፣ በህመም ሳቢያ መስራት የማይችሉ ልጆችን ከካምፕ አውጥተው ታይላንድ ድንበር ሲጥሏቸው ሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩ ኤን.ጂ.ኦ አንስተው ታይላንድ በመውሰድ አሳክመው ህንድ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ነው ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያደረጓቸው።

አንዳንድ ሚዲያዎች የዘገቡትና መንግስትም ድፍን ባለ መልኩ የሰጠውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ማይናማር ያሉ ልጆች የተለቀቁ የመሰላቸው
አድማጮች እንኳን ደስ አላችሁ ’ የሚለን በዝቷል። እውነታው ይሄ አይደለም።

ይህን ጉዳይ ህዝብ ይረዳው። ማይናማር ከታገቱት ልጆች መካከል እንዲለቀቁ በተደረገ ጥረት ማንም አልተለቀቀም።

ታይላንድ ያሉት ናቸው እንጂ ማይናማር ያሉት አይደሉም የወጡት። ዋሽተው ነው። ዜናውን አካብደውታል። እኛን ምንም ተስፋ አልሰጡንም። ‘አትምጡ’ ነው ያሉን ” ሲሉ አስረድተዋል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?

በዚህ መልኩ (ታጋቾች ተለቀዋል በሚል) የዘገቡት ሚዲያዎች ሁለት፣ ሦስት ጊዜ ድምፅ እንዲሆኑን ጠይቀናቸው ሳለ ‘ እንከሰሳለን ’ ብለው ነው የፈሩት። አሁን ግን ያልተወራውን ማስተላለፍ ከኢቲክስ ውጪ ነው። በጣም ቅር ብሎናል። እውነታውን አሳውቁልን።

በታይላንድና በማይናማር ድንበር ያሉት ልጆች እንጂ ወጡ የተባሉት ከማይናማር ግዛት ካሉት ጋር እንደማይገናኝ በህንድ የሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ነግሮናል።

የኤምባሲው ሰዎች ‘እኛ የሚመለከተን ታይላንድ አካባቢ ያለውን ብቻ እንጂ የማይናማሩ የሚመለከተው ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነውና ማይናማር ያሉትን አንድም ነገር አልሰራንም’ ብለው ቃል በቃል ነው የነገሩን።

ከኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በመግቢያ ንግግራቸው ያስተላለፉት ትክክለኛውን ‘ታይላንድ አካባቢ ያሉትን’ ብለው ነው።

ነገር ግን አንዳንድ ሚዲያዎች በስቃይ ላይ ያሉ ልጆችን መንግስት እያስወጣ እንዳለ አድርገው ነው መግለጫውን የዘገቡት። ይህ ቅር አሰኝቶናል።


ሌሎች አገራት እኮ ዜጎቻቸውን ያስወጡት ከትራደሽናል ሊደሮች፣ ከኤምባሲዎች ጋር ሆነው በመስራት ነው። የኛዎቹ ግን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም።

አንዱን ኢትዮጵያዊ የመራቢያ አካሉን የዘር ፍሬ ነቅለውታል። በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ።

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ በችግር ላይ ያሉ ልጆችንን  ካሉበት ስቃይ እንዲታደጋቸው በአጽንኦት እንጠይቃለን ” ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ ቲክቶክን ዘጋች። ' ቲክቶክ ' የተባለው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ እስከ ዛሬ እሁድ ድረስ እንዲሸጥ ካልሆነ ግን እንዲታገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል። በዚህም ቲክቶክ በመላ አሜሪካ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ እንዳይሰራ ተደርጓል። መተግበሪያው ገና እግዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሰዓት ሳይደርስ ቀደም ብሎ (ከሰዓታት በፊት) ነው የዘጋው። በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ስክሪን ላይ ፥ " ቲክቶክን ለማገድ የወጣው…
#Update

" ያለ አሜሪካ ፍቃድ/ይሁንታ ቲክቶክ የለም " - ትራምፕ

👉 " 50% የቲክቶክን ድርሻ አሜሪካ መያዝ አለባት ! "

ትራምፕ ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል ሊያደርጉ ነው።

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ገጻቸው ላይ ዛሬ ባወጡት ፅሁፍ ፤ ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራቱን እንዲቀጥል እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

ለዚህም በስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያ ቀን (ነገ ማለት ነው) ቲክቶክ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል የሚያስችል እርምጃ ይወስዳሉ / ልዩ የሆነ ትዕዛዝ ይሰጣሉ።

ትራምፕ በዚሁ ፅሁፋቸው አሜሪካ የማህበራዊ ድረ-ገፁን ግማሽ (50%) በባለቤትነት መያዝ እንዳለበት ጠቁመዋል።

ነገ ወደ ቢሮ ገብቼ ስራ ከጀምርኩ በኃላ " ቲክቶክ እንዲጨልም አልፈልግም " ሲሉ ገልጸዋል።

ትራምፕ እንደ ጋራ ሽርክና አሜሪካ በቲክቶክ ውስጥ የ50% የባለቤትነት ድርሻ እንድትወስድ ሀሳብ አቅርበዋል።

ይህ ማለት ከወላጅ ኩባንያው ባይትዳንስ ወይም ከአዳዲስ ባለቤቶች ጋር " በአሜሪካ እና በመረጠችው ግዢ መካከል ትብብር ሊፈጥር ይችላል።

ትራምፕ " ይህንን በማድረግ ቲክቶክን እንታደገዋለን ፣ በጥሩ እጆች ውስጥ እናቆየዋለን " ብለዋል።

" ያለ አሜሪካ ፍቃድ ቲክቶክ የለም " ያሉት ትራምፕ " ከኛ ይሁንታ ጋር በመቶ ቢሊዮን ዶላር ምናልባትም ትሪሊዮን የሚቆጠር ዋጋ አለው " ሲሉ ጽፈዋል።

ቲክቶክ ከዚህ ቀደም " ከምሸጠው ሙሉ በሙሉ ዘግቼ አሜሪካን ብለቅ ይሻለኛል " ማለቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች ! " - ሰልፈኞች

በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።

ሰልፉ የተዘጋጀው በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አማካኝነት ነው።

ምክር ቤቱ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።

ሰልፈኞቹ ፦

- ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይመለሱ !
- ህገ-መንግስት ይከበር !
- ፍትህ ለእህቶቻችን ነፃነት ለሁሉ !
- ሂጃብ መልበስ ሃይማኖታዊ መብትና ግዴታ ነው !
- ሂጃቤ መልኬ ነው !
- የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይከበር !
- ሰላም እና ፍትህ ለትግራይ !
- መብታችን ይጠበቅልን !
- ከተበዳዮች ጎን እንቁም !
- ፍትህን እንጠይቃለን !
- ከሂጃባችን ጋር ታግለናል፤ ሂጃባችን ለብሰን እንማራለን !
- ሂጃባችን ምርጫችን እና መብታችን ነው !

... የሚሉና እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።

በመቐለ ሮማናት አደባባይ ለተሰባሰቡት ሰልፈኞች መልእክት ያስተላለፉት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዜዳንት ሸኽ አደም ዓብደልቃድር  ፥ " ትግራይ የሃይማኖቶች የመቻቻል የነፃነት ተምሳሌት ነች፤ ይሁን እንጂ ይህንኑ ስልጡንነት ወደ ኋላ በሚመልስ መልኩ ልጆቻችን ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ ከዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እንዲቀሩ ተደርገዋል "  ብለዋል።

ችግሩ ሳይባባስ እንዲፈታ ለሁለት ወራት በላይ የተለያየ ጥረቱ መደረጉ ያወሱት ፕሬዜዳንቱ  " ትምህርት ቤቶቹ የክልሉ እና የአገሪቱን ህግ በማክበር የሂጃብ ክልከላውን በአጭር ጊዜ ማንሳት አለባቸው ፤ ጥያቄያችን በአጭር ጊዜ ካልተመለሰ ግን ጥያቄያችን እስከ መጨረሻው ድረስ በሰላማዊ መንገድ እንቀጥላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ክርስትያን ወንድሞቻችን ችግሩ ክጅምሩ እንዲፈታ ብዙ ጥረት  አድርጋችሃል " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ችግሩ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስም የጀመራችሁት ትግል ተጠናክሮ ይቀጥል " በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም የሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ጉዳዩ ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት እንዳያመራ የሚያስገነዝብ ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከትምህርት ገበታቸው የተስተጓጎሉ ሴት ተማሪዎች መካካሻ ትምህርት እንዲያገኙ ያለሙ የሚያወሱ 12  ጥሪዎች እና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ መልእክቶች ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር በማቅረብ እና  በማስተላለፍ ከረፋዱ 4:30 ሰልፉ ተጠናቋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የከተማዋ የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥበቃ ያደረጉ ሲሆን በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፥ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ ክልከላ አድርገዋል የተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የጋራ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥተዋል።

ት/ቤቶቹ ምን አሉ ?

" 1. የሴት ሙስሊም ተማሪዎች የሂጃብ አጠቃቀም አስመልክቶ በትግራይ ያለው ህግ እና አተገባበሩ ምን ይመስላል ?

ትምህር ቤቶቻችን የትግራይ ትምህርት ቢሮ በ1995 ዓ.ም ያወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ነው እየተጠቀሙ ያሉት ። አዲስ ፖሊሲ ወይም መመሪያ እና ደንብ በትምህርት ሚንስቴር ከወጣ ደግሞ ከትምህርት ቢሮ ጋር ተነጋግሮ ይህንን መመሪያ እና ደንብ ተጠቀሙ ብሎ ይልክልናል ። እኛም ተግባራዊ እናደርጋለን። ይህን ባለልሆነበት ' እህያውን ፈርቶ ዳውላውን ' የሆነ ጥያቄ እና ጫና ግን ግራ የሚያጋባ ነው።

በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደግሞ ተማሪዎች መምህራን ወላጆች ተወያይተው ያፀዱቁት ላለፉት 22 ዓመታት እየተጠቀሙት ያለ መመሪያ ደንብ ነው።

በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደንብ ደግሞ እንዲታይ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ከወላጅ ተማሪዎች ጥያቄ ተነስቶ ነበር ። የተነሳው ጥያቄ መሰረት በማድረግ በመመሪያ እና ደንቡ ውይይት ተካሂዶ ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም በአንድ ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ፀድቀዋል።

በውይይት እና ድምፅ አሰጣጡ የሙስሊም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ተሳትፈውበት በሙሉ መግባባት መተማመን የተደረሰበት ነው። ታድያ ከአሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ የሂጃብ ክልከላ ጥያቄ ከየት ? እንዴት መጣ ? ትምህርት ቤቶታቻችን ግራ ገብቶዋቸዋል።

2. የትምህርት ቤት ዩኒፎርም አለባበስ ደንብ እና ስነ-ሰርዓት ምን ይመስላል ?

በ1995 ዓ.ም በፀደቀው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መምሪያ እና ደንብ መሰረት ትምህርት ቤቶቻችን የሚከተለውን የአለባበስ ስርዓት እንዲተገብሩ ያስገድዳል።

የቤተክርስትያን ካህናት እና ዲያቆናት ተማሪዎች ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ነጠላ ማድረግ አይፈቀድም። ወንድ ተማሪዎች ባንከር ፣ ፍሪዝ የፀጉር አቆራረጥ አይፈቀድም።

ሴት ተማሪዎችም ነጠላ ፣ መሃረብ ፣ ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ጥቁር የሃዘን ሻርፕ ፣ ሂል ጫማ ፣ ሱሪ ፣ የማንኛውም ሃይማኖት አለባበስ የሚያንፀባርቅ ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድም። ይህ የሆነበት ደግሞ በመካከላቸው የሃብት የሃይማኖት ልዩነት ፈጥሮ የመማር የማስተማር ሂደቱ እንዳይታወክ ለማድረግ ያለመ ነው።

ይህ ህግ ደግሞ ክርስትያን ፣ ሙስሊም መምህር የተማሪ ወላጅ ተወያይተው ያፀደቁት እና የሚተዳሩበት ነው። አሁን ታድያ ምን አዲስ ነገር ተፈጥሮ ነው በትምህርት ቤቶቻችን ላይ የሚዘመተው ? 

 3. ስለ ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች መሬት ላይ ያለው መረጃ ምንድነው ?

በአክሱም አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ።  በአራቱ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ ለ12ኛ ክፍል አገር  አቀፍ ፈተና የሚቀርቡት  ተማሪዎች 1044 ናቸው።

ከነዚህ 1044 ተማሪዎች 17 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ 17 ሴት ተማሪዎች ለ22 ዓመታት በቆየው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ እና ደንብ በመቀበል 7 ሴት ተማሪዎች ፈተናው ለመውሰድ ፎርም ሞልተዋል።

10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ከአክሱም ከተማ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በተዘረጋ የውጭ ተፅእኖ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸው ፎርም አልሞሉም። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ' 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲስተጓጎሉ ተደረገ ' እየተባለ ነው የሚወራው። 142 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻችን የሌሉ የፈጠራ ድርሰቶች ናቸው።

የተቀሩት 10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ቢሆኑ ፎርም መልተው ለመፈተን ፍላጎት አላቸው ፤ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፣ ከመቐለ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በየቀኑ እየተደወለ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ የቆየውን አብሮነት እና መቻቻል የሚጎዳ ለህዝብ እና አገር የማይጠቅም መወገዝ ያለበት ተግባር ነው። "

... ሲሉ ትምህርት ቤቶቹ በጥምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በላኩት የፅሁፍ ምላሽ ገልጸዋል።

#UPDATE ትምህርት ቤቶቹ ዘግይተው በላኩት መልዕክት ደግሞ " ሁሉም ተፈታኞች ፎርም ሞልተዋል ለፈተናም ብቁ ናቸው " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle
#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የስራ ማቆም አድማ የመቱት ሰራተኞች ምን አሉ ? 🚨“ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም” - የሥራ ማቆም አድማ የመቱ ከ350 በላይ ሠራተኞች ➡️ “ በዚሁ ዙሪያ ስብሰባ ላይ ነኝ ” - ድርጅቱ በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ የሰራተኞች ማኀበር ሥር እንደሚተዳደሩ የገለጹ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ከ350 በላይ…
#Update

🔴 “ በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል ” - ማኀበሩ

🔵 “ 20% የደመወዝ ጭማሪ አድርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል ” - ሠራተኞቹ

“ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰናል ” - ፌደሬሽኑ

በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ መሠራተኞች ማኀበር ሥር የሚተዳደሩት የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ሠራተኞች በማኀበሩ ላይ ቅሬታ ማቅረባቸውን ከሰዓታት በፊት መረጃ አድርሰናችሁ ነበር። 

ቅሬታ የቀረበበት ማኀበሩ በወቅቱ ማብራሪያ ሳይሰጥ የቆዬ ሲሆን፣ በኋላ ለቀረበበት ቅሬታ በሰጠን ምላሽ፣ “ስምምነት ላይ ደርሰናል” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማኀበሩ የሰው ኃብት አቶ በፍቃዱ አበራ፣ “ስብሰባ ላይ ነበርኩ። ውይይት ላይ የነበረ ጉዳይ ነው። ውይይቱም በሰላም ተጠናቋል” ብለዋል።

ሠራተኞቹ ብዙ ቅሬታ አላቸውና በምን ተስማማችሁ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “አጠቃላይ እንደቀረፍን ነው ልነግርህ የምችለው። በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል” ነው ያሉት።

ስምምነት ላይ ደርሳችኋል ስንል የጠየቅናቸው ሠራተኞቹ በበኩላቸው አሁንስ ምን አሉ ?

“ ተነጋግረናል ሥር ጀምረን ከዛ ለማስተካከል፡፡ 20% የደመወዝ ጭማሪ አደርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል፡፡

'የትራንስፖርት ጉዳይም ይስተካከላል፣ አሁን ባለው የሥራ ማቆም ምክንያት ማንም ሰው እንዳይባረር፣ ሌሎችንም ጥያቄዎች ደግሞ በኅብረት ስምምነት ገብተን እንፈታልን’ ብለው ሁሉም ሠራተኞች እንዲመለሱ ነው የስማማነው፡፡

ችግሩ ተፈትቷል፡፡ የሚዲያ ትኩረት አጣንና በመጨረሻ በማይሆን ነገርም መስማማት ግዴታ ሆነብን፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በላይ ሥራ ካቆምንም የሥራ ዋስትና አይኖርም ብለን እጅ ሰጥተናል፡፡ 

አንገብጋቢው ጉዳይ የደመወዝ ጉዳይ ስለነበረ እሱ ላይ 20% ጭማሪ በቀጣይ ወር ኢፌክቲቭ እንደሚሆን፣ ከዚያ ውጪ ሌሎች የሚሻሻሉ ነገሮችን በውይይት ተቀራርበን መስራት አለብን በሚለው ተነጋግረናል ” ብለዋል።


የ20% ደመወዝ ጭማሪ እዳደረገላቸው ነው የገጹት ሠራተኞቹ፣ ይሄ እውነት ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ የማኀበሩ የሰው ኃብት፣ “ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ከመስጠት እቆጠባለሁ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ ተደርጓል የተባለው የደመወዝ ጭማሪ ትክክል ነው? ሲል በውይይቱ ሲሳተፍ ለነበረው ለትራንስፓርትና መገናኛ ሠራተኛ ማኀበራት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ጥያቄ አቅርቧል።

የፌደሬሽኑ ፕሬዜዳንት አቶ አባትሁን ታከለ ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ ደመወዝ ጭማሪ በኀብረት ስምምነቱ የሚቀመጥ ነው። ኀብረት ሰምምነት አልነበረም። ወደፊት በኅብረት ስምምነት እንደምናስቀምጥ፣ ዘላቂ መፍትሄ እንደምናመጣ ተግባብተናል ከአሰሪው ጋ።

ነገር ግን ለጊዜው አሁን ያለውን ሁኔታ አገናዝበን አሰሪው ከታች ከ5% ተነስቶ ወደላይ ከፍ ብሎ፣ ሠራተኞም ከላይ ወደታች መጥተው፣ በኛም መሠረት ከየተካቲት 1/2017 ዓ/ም 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምነት ላይ ደርሰናል።

አሁን ሠራተኞቹ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ከነገ ጀምሮ ሥራ ይገባሉ ”
ብለዋል።

ሠራተኞቹ ቅር የተሰኙባቸው ከደመወዝ ውጪ ያሉ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በምን ተስማማችሁ! ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፕሬዜዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ሌሎች የተነሱ ወደ ዘጠኝ ጥያቄዎች ነበሩ፣ ለጊዜው በኅብረት ስምምነት ወደፊት የሚፈተለ አሉ። የትራንስፓርት ጉዳይም በኀብረት ስምምነት የሚፈታ ነው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 “ በጥሩ ሁኔታ በመግባባት ጥያቄያቸው ተመልሷል ” - ማኀበሩ 🔵 “ 20% የደመወዝ ጭማሪ አድርገው በኋላ ደግሞ ሥራ ጀምረን ሌላውን ለማስተካከል ተስማምተናል ” - ሠራተኞቹ “ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ 20% የደመወዝ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰናል ” - ፌደሬሽኑ በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ መሠራተኞች ማኀበር ሥር የሚተዳደሩት የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና…
#Update

“ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” - ሠራተኞቹ

በርካታ ቅሬታዎች ያደሩባቸው ከ350 በላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሱቫል ሠራተኞች ለቅሬታቸው አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም።

“ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና ሲምካርድ አፕሩቫል ሰርቪሶች ተቋርጠዋል ” ብለው የነበረ ሲሆን፣ ሠራተኞቹን የሚያስተዳድረው አይሰን የተሰኘው ድርጅት ቅሬታውን በውይይት እንደፈታ ትላንት ምላሽ ሰጥቶን ነበር።

የትራንስፖርት መገናኛ ሠራተኛ ማኀበራት ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን፣ ሠራተኞቹ ደመወዝ ሊጨመርላቸው ስምምነት ላይ እንደተደረሰ፣ ሌሎች ጥያቄዎቻቸው በሂደት እንዲፈቱ፣ ለዛሬ ሠራተኞቹ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ነግሮን ነበር።

ሠራተኞቹ አቋርጠውት ወደነበረው ሥራ ተመለሱ ?

ለቅሬታዎቻችሁ " መፍትሄ አላገኘንም " በማለት መብታችሁን ለማስከበር ካደረጋችሁት የሥራ ማቆም አድማ በኋላ ዛሬስ ወደ ሥራ ተመለሳችሁ ? ስንል ጠይቀናቸዋል። 

ሠራተኞቹም፣ “ ቃል በገባነው መሠረት ሁላችንም ሠራተኞች ወደ ሥራ ተመልሰናል። ግን ገና የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ ” የሚል ምላሽ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

ሠራተኞቹ ፦

“ ሥራ ጀምረናል። ግን ገና ብዙ የሚስተካከሉ ነገሮች አሉ። ሁሉም ቀስ እያሉ ይስተካከላሉ። የደመወዙ ጭማሪ ከየካቲት 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።

ሌሎቹን ጉዳዮች በተመለከተም ከቀጣይ ሳምንት ጀምረን ወደ ድርድር እንገባለን። 

ሁሉም ሠራተኞች ወደ ስራ ተመልሰዋል። ምክንያቱም ማንም ሰው ባደረገው የሥራ አድማ ምክንያት አሉታዊ ነገር እንዳይደርስበት ተፈራርመን ነው የተመለስነው ” ብለዋል።


በጉዳዩ ዙሪያ የሚፈጠር አዲስ ነገር ካለም የምንከታተልና መረጃም የምናደርሳችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውጤቱ ህዝብን እና አገር የሚያጠፋ አካሄድ በመሆኑ መቆም አለበት " - የተለየ አቋም ያላቸው ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች 

በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ የትግራይ ኃይል አመራር መኮንኖች ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ያወጡት መግለጫ ተቃውሞ እየገጠመው ነው።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደርን በመቃወም በብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ያልተሰጠው ጉባኤ ያካሄደው በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት እውቅና እንደሚሰጡ ያስታወቁት የትግራይ ኃይል አመራሮችን ጊዚያዊ አስተዳደሩ በፅኑ ተቃውሟቸዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩን መግለጫ ተከትሎ በአመራሮቹ ሰብሰባ ላይ የተሳተፉ የተለየ አቋም እንዳላቸው የገለጹ ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች ፥ " የሰራዊት አመራር በመሆን የፓለቲካ ፓርቲ የሚመስል ሰራዊት ለመገንባት የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤቱ ህዝብን እና አገር የሚያጠፋ አካሄድ እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

የተለየ አቋም እንዳላቸው በመግለጫቸው ያሳወቁት ከፍተኛ አመራሮቹ ፤ " አንድ የፓለቲካ ፓርቲ እና በዚህም በዚያም ያሉት ቡድኖችን የሚመለከት አጀንዳ ላይ መወያየት እና አቋም መያዝ ከሰራዊቱ ተልእኮ ውጪና ወታደራዊ ወንጀል በመሆኑ በጥብቅ እንቃወማለን " ሲሉ አብራርተዋል።

" ስለሆነም ከሰራዊቱ ተልእኮ እና የስራ ስምሪት ውጪ ' ጠላት ነው ' በሚል ፍረጃ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ፕሬዜዳንት ለመቀየር የሚደረግ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ተቋማዊ አሰራር የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም በጥብቅ እንጠይቃለን " ሲሉ አክለዋል።

የክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡብ ምስራቃዊ ፣ የደቡባዊ ዞን ኦፍላ ወረዳ እንዲሁም በራስ ተነሳሽነት መሰባሰባቸውን የገለፁ የመቐለ ከተማ ወጣቶች ባወጡት መግለጫ ፤ " ወታደራዊ  መኮንኖች ከተልእኮ እና ከተሰጣቸው ህዝባዊ እና መንግስታዊ  ስምሪት ባፈነገጠ መልኩ ወደ አንዱ ቡድን በማዳላት ያወጡት መግለጫ በአስቸኳይ እንዲያርሙት " ሲሉ ጠይቀዋል።

የትላንቱ የመግለጫ ተቃዋሚዎች  ፤ " አመራሮቹ ያወጡት ህገ-ወጥ መግለጫ ጅምር ሰላሙ የሚያጨልምና የሚያመክን በመሆኑ ፤ ለህግ እና ስርዓት ተገዢ ከሆኑ አመራር እና አባላት ጋር በመሆን እስከ መጨረሻ ብፅናት እንደምንታገላችሁ ልናሳውቃችሁ እንፈልጋለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የትላንቱን መግለጫ በመቃወም ለቪኦኤ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " የትግራይ ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ እንዲሆን የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ስህተት ነው ፤ ወታደራዊ መኮንኖቹ ፓለቲከኛ መሆን ካሰኛቸው ወታደራዊ ሃላፊነታቸው በመተው የፈለጉት ፓርቲ አባል መሆን ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ያደረጉት ስህተት ግን በአስቸኳይ እንደሚያሩሙት ተስፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” - ሙስሊም ተማሪዎች

🔵 “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” - ዲላ ዩኒቨርሲቲ 

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው እየተስተጓጎሉ በመሆኑ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠንከር ያለ ስሞታ አቅርበዋል።

የተማሪዎቹ ዝርዝር ስሞታ ምንድን ነው ?

“ ኒቃብና ጥቁር ማስክ እንዳንለብስ ነው የተከለከልነው። ክልከላው የጀመረው ከአንድ ወር በፊት ነበር። በዚህም ማመልከቻ አስገብተን ነበር መልበስ እንዲፈቀድልን። ሆኖም ግን ምላሽ ሳይሰጠን ቆዬ።

ትምህርታችን በስርዓት እንዳንከታተል አስተጓጎሉን። ቅዳሜ፣ አንዲት እህት ማስክ አድርጋ፣ ሂጃብ ለብሳ በምትገባበት ወቅት ኦዲያ ካምፓስ በሁለቱም በሮች እንዳትገባ ከልክለዋታል።

እንዲያውም ወንዶቹ የግቢው ጥበቆች አስፈራርተው ፊቷን አስከፍተዋታል። እንደዛም ሆኖ ማስክ ለብሳ ወደ ግቢ መግባት እንደማትችል ነግረው መልሰዋታል። 

ቅዳሜ ከሰዓት ሁለት ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎች ግቢ ሊገቡ ሲሉ ተከልክለዋል። ለምን እንደተከለከሉ ሲጠይቁ ‘ ለደህንነት ሲባል ፊታችሁ መሸፈን የለበትም ’ አሏቸው።

ለደኅንነት ሲባል ከሆነ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በሴት ጥበቃ ተፈትሸው፣ አይዲያቸውን አሳይተው እንዲገቡ ሲጠይቋቸው ‘ ያንችን ፊት ማየት ምንም አይሰራልኝም። ፊትሽን ለምታሳይው አሳይ ’ የሚል መልስ ተሰጠን።

ከዚያ በኋላም ሰኞ እለት ደግሞ ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ መልበስ እንደማይቻል በፕሬዜዳንቱ ጭምር ተወሰነ። የተማሪ ተወካዮች ጠርተው ይህን አሳወቋቸው።

ጥበቃዎቹም ውሳኔውን በመጥቀስ ‘አናስገባም’ አሉን። ማክሰኞ እለት ማታ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን።

ረቡዕ ጠዋትም ከለር ማስክ አድርገው የገቡትን በፌደራል ጭምር አስፈራርተው ፊታቸውን እንዲገልጡ አድርገው፣ ሂጃብም ማውለቅ እንዳለባቸው አሳሰቧቸው።

ከሰኞ ጀምሮ ክላስም እየተከታተልን አይደለም፣ ኤግዛም አልፎናል፣ አሳይመንትም እያለፈን ነው። ማውለቅ ስለማንችል ከግቢ ውጪ ነን። በቃ ከተማሪነት ውጪ ባለ ህይወት ነን። እንደ ሴትነታችን ትልቅ የመብት ጥሰት ነው የተፈጸመብን። 

ከምሽቱ 3 ሰዓት እንዳንገባ ሲከለክሉን የት እንድናድር፣ ምን እንድንለብስ፣ ምን እንደምንምገብ ያሰቡትን አናውቅም። ስለዚህ እንደንገባ ቢፈቅዱም እንዲህ ያደርጉበት ምክንያትን ሊጠየቁ ይገባል ”
ሲሉ ተናግረዋል።

ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅናቸው ስማቸው እንዲነገር ያልፈቀዱ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ ስለጉዳዩ በዩኒቨርሲቲው ፌስ ቡክ ገጽ የወጣውን መረጃ እንድንጠቀም ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎቹ ነቃብ፣ ማስክና ሂጃብ ለብሰው እንዳይገቡ ተከልክለው ከግቢ ውጪ በመሆናቸው ትምህርት እያለፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፤ መከልከሉ ልክ ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

በምላሻቸው፣ “ እንዲህ አይነት ነገር የለም። የተሳሳተ መረጃ ነው። ማንም ተማሪ እዚህ ግቢ በተፈቀደለት ሰዓት ይገባል፤ ይወጣል ” ሲሉ መልሰዋል።

“ የተቋሙንም ሆነ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት አስተዳደር መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” ብለዋል።

ተማሪዎቹ በተጨባጭ ከግቢ ውጪ እንደሆኑ፣ ክላስ እያለፋቸው እንደሆነ በድጋሚ የገለጽንላቸው እኝሁ አካል፣ በድጋሚም “ የለም ” የሚል ማስተባበያ ነው የሰጡት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የጌዴኦ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን ተማሪዎች ደረሰብን የሚሉት ክልከላ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲው “ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” ብሏልና እናንተ ጉዳዩን አይታችሁት ነበር ? ሲል ማረጋገጫ ጠይቋል።

ምክር ቤቱ ምን መለሰ ?

“ ጉዳዩ ከወር በፊት ደርሶን ነበር። እየቆየ ከፍ እያለ መጥቶ ተማሪዎች ግቢ ለመግባት ሲከለከሉ እኛም ደብዳቤ ፅፈን ነበር ችግሩ እንዲፈታ።

ዩኒቨርሲቲው እርከን ያልጠበቀ ጉዳይ ተደርጎ ታይቶ ነው፤ ተማሪዎቹን እናገኛቸዋለን የሚል ጥሩ ስሜት ነበረው። 

የእስልምና አለባበስ ከጥንት ጀምሮ ራሱን የቻለ ሊቃውንቶች ያስቀመጡት ነው። ይሄ የተሻለውና ተመራጭ የሆነው አለባበስ ነው ” ብሏል።


(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” - ሙስሊም ተማሪዎች 🔵 “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” - ዲላ ዩኒቨርሲቲ  የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው…
#Update

🔴 " ዩኒቨርሲቲያችን እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

➡️ " ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " - ሙስሊም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ


የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት የእስልምና እምነት ተከታይ / ሙስሊም ተማሪዎች " በሃይማኖታዊ አለባበሳችን ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን አድርሰዋል።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ተማሪዎቹ መካከል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ እና ሰመራ ካምፓስ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " አትግቡ መባል ከጀመርን አንድ ወር ገደማ ሆኗል " ያሉን ሲሆን " በሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኮሚቴ አማካኝነት በፅሑፍ ቅሬታ አቅርበን ስንጠባበቅ ከሰኞ ጥር 12/2017 ዓ/ም  ጀምሮ ' ንቃብ ማድረግ አትችሉም ' ተብለን ግቢ እንዳንገባ በመከልከላችን በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለን እንገኛለን " ብለዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኑሬዲን አብደላህ ፤ " ችግሩ ከተማሪዎች ባሻገር አንዲት የዩኒቨርስቲው መምህርትም ጭምር ያካተተ ስለነበር ለዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮች ቅሬታ በፅሑፍ አቅርበን በቂ ምላሽ ስላልተሰጠን ተማሪዎች በዚህ የፈተና ወቅት በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለዉ ይገኛሉ " ብሏል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ከማል ሀሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ በደቡብ ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኩል 150 ተማሪዎች ከእስላማዊ አለባበሱ ጋር በተያያዘ ክልከላ እንደተደረገባቸውና አብዛኞቹ  የፈተና ወቅት በመሆኑ ኒቃብ አዉልቀዉ ማስክ እየተጠቀሙ ወደ ግቢ እንደገቡ ገልጸዋል።

ስራ አስኪያጁ ፥ 22 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች አሁንም በመስጊዶች ተጠልለው እንደሚገኙ መረጃዉ በጽሑፍ እንደደረሳቸው ገልፀዉ ጉዳዩን ለትምህርት ሚንስትር በፅሑፍ ማቅረባቸውንና " ባለድርሻ አካላት የቆዩ መመሪያዎችን ዳግም ማየት ይጠበቅባቸዋል " ብለዋል።

" ከሁለት ዓመታት በፊት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ችግር ተነስቶ እንዲረግብ ተደርጎ የነበረ ሲሆን አሁንም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ችግሩ ላለመነሳቱ ዋስተና የሌለ በመሆኑ እነዚህን አጋጣሚዎች ለሌሎች ፍላጎቶች በሚጠቀሙ አካላት ጉዳዩ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ዘላቂ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል " ብለዋል።

ቲክቫህ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)ን ስለ ጉዳዩ አነጋግሯቸዋል።

ዶክተር ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፥ " የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " ብለዋል።

" በዩኒቨርሲቲው ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ አልተከለከለም ኒቃብ ደግሞ አስቀድሞም በዩኒቨርሲቲ አይደረግም ነበር " ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለዉም " በተለያዩ ማህበራዊ  ሚዲያዎች ዩኒቨርሲቲዉ ' ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ሂጃብ መልበስ ከልክሏል ' በሚል የሚሰራጨዉ መረጃ ትክክል ያልሆነ ሀሰተኛ መረጃ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህ ምክንያት ወጪ አሉ ስለተባሉ ተማሪዎች እና ስላመለጣቸዉ ፈተናዎች እንዲሁም ስለዩኒቨርስቲው ቀጣይ አቋም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበዉ ጥያቄ የተለየ ዉሳኔ አለመኖሩን ዩኒቨርስቲው አስታዉቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላችኋል " - በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት

በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ፤ ትናንት ጥር 15/2017 ዓ.ም  " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠውን መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም መግለጫው ፥ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት" የነሃሴው " ብሎ ሲጠራው ራሱን ደግሞ " ነባር " በማለት ገልጿል።

" የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን "  በሚል ያወጡት መግለጫ የ " ነሃሴው ህወሓት ህዝቡን እና ሰራዊቱ ለመበታተነ የሰራው ክፋት ውጤት ነው " በማለት ገልፆታል።

" የነሃሴው ህወሓት ህዝብን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያልተቀበለው ጉባኤ  በማካሄድ ነባሩን ህወሓት እንዲዳከም ሰርቷል " ሲል በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት ፤ " ወታደራዊ አምባገንነት ታግሎ ዴሞክራሲያዊ እና ህዝባዊ መንግስት የጨበጠ ህዝብ ወደ ኋላ አይመለስም " ብሏል።

" የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን "  በሚል ስም የወጣውን መግለጫ " የጦርነት አዋጅ ነው ፤ በህዝብ ላይ አፋኝ አስተዳደር የሚጭን ተቀባይነት የሌለውና የውድቀት ጥሪ " ሲል ገልጾታል።

" ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላቹሃል " ያለው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " የጦርነት አዋጃችሁ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፍርሶ ፤ ትግራይ ለአህጉራዊ ዓለምአቀፋዊ ተነጥሎ እና ውግዘት የሚዳርግ ህዝቡን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው " ሲል አክሏል።

የአነ አቶ ጌታቸው ቡድን መግለጫውን መላ የትግራይ ኃይል አባላት እንዲያወግዙት ጠይቆ " ህዝብን እና መንግስታችሁ በሚስጡዋችሁ አቅጣጫ ብቻ እንድትንቀሳቀሱ ጥሪያችን እናቀርባለን " ሲል አሳስቧል።

ህዝቡ እና ወጣቱ በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ገልጾ ይህንኑ በመገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትግሉ በማጠናከር ለመብቱ ለአንድነቱ እና ለህልውናው በመታገል የተደቀነበት አደጋ እንዲመከት ጥሪ አቅርቧል።

ለህዝቡ ፣ ለዳያስፓራ ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ስም የወጣው መግለጫ እንዲያወግዙት ጠይቀዋል።

መግለጫውን ያወጡት አመራሮች ያለፈ ታሪካቸው ከሚያጎድፍ ተግባር በመውጣት አሁን የፈፀሙት ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርሙ እና ታሪካቸው እንዲያድሱ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia