TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#JawarMohammed " አልፀፀትም " / " HIN GAABBU " በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የገዘፈ ስም ካላቸው ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ መፅሀፍ ይዘው እየመጡ እንደሆነ ገለጹ። የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ መንገድ በመታገል ስርዓቱ ሳይወድ በግዱ እንዲቀየር በማድረጉ ረገድ ግንባር ቀደሙን ድርሻ እንደሚይዙ የሚነገርላቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ከዚህ ቀደም…
#JawarMohammed

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሩ አቶ ጃዋር መሐመድ ' አልጸጸትም / HIN GAABBU ' መጽሐፍ ዛሬ ሳይመረቅ ቀረ።

መጽሐፉ ዛሬ በኬንያ፣ ናይሮቢ ሊመረቅ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር።

አቶ ጃዋር መሐመድ ናይሮቢ ሊካሄድ የነበረው የመፅሐፍ ምርቃት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አረጋግጠዋል።

ጃዋር " በተሳታፊዎች ብዛት እና በደህንነት ስጋት ምክንያት የምረቃ አዳራሹ አስተዳደር ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን " ገልጸዋል።

" በቅርብ ቀን ተቀያሪ ቦታ እናሳውቃለን " ብለዋል።

ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ደግሞ ምንጮቼ  እንደገለጹልኝ የመጽሐፍ ምርቃቱ ሳይካሄድ የቀረው ከተለያዩ አካላት ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎች በመድረሳቸው ነው ብሏል።

መጽሐፉ የሚመረቅበት ናይሮቢ የሚገኘው የኬንያታ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል መሆኑ ከታወቀ በኋላ የተለያዩ ማስፈራሪያዎች ደርሰዋል ተብሏል።

ዛቻው እና ማስፈራሪያው የጸጥታ ስጋት እንዳለ በመጥቀስ ማዕከሉን ለሚያስተዳደሩት አካላት በመድረሱ ምርቃቱ መሰረዙን እኚሁ ምንጮች ገልጸዋል።

እኚህ አካላት እነማን እንደሆኑ ግን ዘገባው በግልጽ አላሰፈረም።

በቅርቡ አቶ ጃዋር መሐመድ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ መጽሃፋቸውን በኢትዮጵያ ለማስመረቅ እንደሚፈልጉ ነገር ግን "... በአገሪቱ መጽሐፍ ማስመረቅ ይቅርና ለመተንፈስ ከባድ ነው " የሚል ነገር ተናግረዋል።

" ኢትዮጵያ ለማስመረቅ ፍላጎት ነበረኝ " ያሉ ሲሆን " ሆኖም ግን ገዢዎቹ ደስተኛ አልነበሩም። አሁን አገራችን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ለመጽሐፍ ብዬ አምቧጓሮ ውስጥ ለመግባት አልፈለግኩም " በማለት በጎረቤት አገር መዲና መጽሐፉን ለማስመረቅ የወሰኑበትን ምክንያት አስረድተዋል።

አቶ ጃዋር መሐመድ የፖለቲካ ጉዞ እና የሕይወት ታሪካቸውን በሚመለከት ' አልጸጸትም / HIN GAABBU ' በሚል ርዕስ በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ መጽሐፍ ጽፈው አሳትመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🚨“ አቶ ክርስቲያን ታደለና ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ የሐኪም ቀጠሮ ነበራቸው ማረሚያ ቤቱ አልወሰዳቸውም ” - ቤተሰቦቻቸው

🔴 “ በሕይወት የመኖር መብታቸውን ነው ያሳጧቸው። የእስረኛ ዝውውር ወይስ በሕይወት የመኖር መብት ነው የሚቀድመው ? ” - ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ

አዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት ባደረባቸው የጤና እክል በወቅቱ ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት ህመም የተዳረጉት አቶ ክርስቲያን ታደለና አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ሰሞኑን የቀዶ ህክምና ተደርጎላቸው ወዲያው ወደ ማረሚያ ቤት በመመለሳቸው ደም እየፈሰሳቸው እንደሆነ፣ ዛሬም የሀኪም ቤት ቀጠሮ እንደነበራቸው ቤተሰቦቻቸው ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ለዛሬው ሀኪም ቤት ቀጠሯቸው ሄዱ ?

ሁሉቱም ዛሬ (ሐሙስ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ/ም) ለቸካፕ ቀጠሮ የነበራቸው ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ እንዳልወሰዳቸው ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። 

አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ተደጋጋሚ የደም መፍሰስ እያጋጠማቸው በመሆኑ ቁስላቸው ለኢንፌክሽን እንዳይጋለጥ ለቸካፕ ለዛሬ በመቅረዝ ሆስፒታል ቀጠሮ እንደነበራቸው አስረድተዋል።

ቀጠሮው ስለሰርጀሪው ፣ ለቅድመ ካንሰር ምርመራ ውጤቱ፣ ለቀጣይ ተከታታይ ህክምና የሚሰጣቸውን የቀጠሮ ቀን የሚውቁበት እንደነበር ገልጸው፣ “ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አልወሰዳቸውም ” ሲሉ ወቅሰዋል።

የእነ የአቶ ክርስቲያንና ዮሐንስ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ በበኩላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

በቀጠሮው አለመሄዳቸው ጉዳት ያመጣል። ለሁለት ነገር ነው በምርመራ ላይ ያሉት። አንደኛ በፊንጢጣ በኩል ኦፕራሲዮን ተደርገው ደም እየፈሰሳቸው ነው።

አዋሽ አርባ በነበሩበት ወቅት የአንጀት ድርቀት ገጥሟቸው ባለመታከማቸው በኋላ ላይም በሽብር ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ በብዙ ጭቅጭቅ ማረሚያ ቤቱ ወደ ሀኪም ቤት ቢሄዱም የሰርጀሪ ደሙ አልቆመም። 

ሆስፒታሉም ‘በዚህ ቀን ይዛችሁ ኑ’ ብሎ ፐርስክርፒሽን ሰጥቷል። ይሄ ህመም ነው የጤና ጉዳይ ነው። የዛሬ የሆስፒታል ቀጠሮ የሚፈሰውን ደምና የቁስሉን ምንነት ለማረጋጠጥ ነበር።

ሁለተኛ የአንጀታቸውን በተመለከተ ኦፕራሲዮን ለማድረግ የካንሰር ምርመራ አድርገዋል። ውጤት ለማወቅ ነበር ቀጠሮው። ግን ከቤተሰቦቻቸው የሰማሁት በቀጠሯቸው መመሠረት ሀኪም ቤት እንዳልወሰዷቸው ነው።

ማረሚያ ቤቱ ያቀረበው ምክንያት ‘እስረኞቹን ወደ ሌላ ቦታ እያዘዋወርን በመሆኑ አጃቢና መኪና ስሌለ ነው’ በሚል ነው። ይሄን በተመለከተ ፍርድ ቤት ምስክር በምናሰማቸው በነ ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ዐቃቢ ህግ ምስክር እያሰማ እዛው ውለናል ከትላንትና ትላንት ወዲያ።

‘እስረኛ እያዘዋወርን ስለሆነ አናመጣቸውም’ የሚል ወረቀት ቢያስገቡም ‘አይቻልም’ ብሎ ፍርድ ቤቱም ትዕዛዝ ስለሰጣቸው ትላንትናም አምጥተዋቸዋል። ትላንትም ምስክር ሰምተናል፣ ዛሬም ምስክር ሰምተናል።

ታዲያ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲሆን ብቻ ነው እንዴ እነርሱ የሚያከብሩት ? በእርግጥ እስረኛ እያዘዋወሩ እንደሆነ ይታወቃል። ግን ምስክር ለመስማት ‘አምጡ’ ሲባሉ ነው ተገደው ማምጣት ያለባቸው ወይስ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ሲሆን ነው አፋጣኝ እርምጃ ወስደው ማምጣት ያለባቸው ?

መቼም የማረሚያ ቤት አስተዳደር ብዙ ጠባቂዎች አሉ። እንደምንም ተፈልጎም መኪናም ተከራይተውም ቢሆን የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ በቀጠሯቸው መሠረት አምጥተው ማሳከም ነበረባቸው። 

ስለዚህ ድርጊቱ አግባብ አይደለም። ይሄ በሕይወት የመኖር መብትንም የሚጣረስ ነው። እነዚህ ሰዎች አሁን ደም እየፈሰሳቸው ነው በቀጣይነት ደሙ ቢፈስስ? የቅድመ ካንሰር ምርመራ ሕይወት ወደማሰጣት ቢደርስስ ? 

በመሆኑም በሕይወት የመኖር መብታቸውን ነው ያሳጧቸው። የእስረኛ ዝውውር ነው ወይስ በሕይወት የመኖር መብት የሚቀድመው? በሕይወት የመኖር መብት ነው መቅድም ያለበት ”
ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #AddisAbaba

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መቼ ይካሄዳል ?

38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት መጀመሪያ ሳምንት ይካሄዳል።

አዲስ አበባ የፊታችን የካቲት ወር መጀመሪያ ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ታስተናግዳለች።

ለዚህም ጉባኤ ሁሉን አቀፍ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባዔውን የኢትዮጵያን ገጽታና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነት በሚያሳድግ መልኩ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጣጥና የሆቴል ፋሲሊቲዎች መሰረት በማድረግ 42 ሆቴሎች እንግዶቹን እንዲያስተናገዱ መመረጣቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር መረጃ ያሳያል።

ሆቴሎቹ በሕብረቱ ጉባዔ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል።

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሁም 46ኛው የህብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። #ENA

Photo Credit - Addis Ababa Mayor Office

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ሚመራው የህወሓት ቡድን በቀጣይ " አዲስ እና ሰላማዊ የትግል ስልት እከተላለሁ " ብሏል።

ቡድኑ በቀጣይ አጠቃላይ አባላቶቹ በመጠቀም " የእምቢተኝነት ዘመቻ " ያለውን እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዳቀደ ተነግሯል።

ለዚህ ዘመቻ " እምቢ ለብሔራዊ ክህደት፣ ለአገዛዝ እና ብተና " የሚል መፈክር እንደሰጠው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ትላንት እና እና ዛሬ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ከፍተኛ ካድሬዎቹ ስብሰባ ተቀምጠው ነው የዋሉት።

@tikvahethiopia
" የሟችዋ ገዳይ አልተገኘም ፤ አሟሟትዋ  እጅግ ዘግናኝ እና ያልተለመደ ነው " - የእንዳባጉና ከተማ ነዋሪዎች

ሟች እንስት ኣልማዝ ፀሃየ የትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳባጉና ከተማ ነዋሪ ነበረች።

ማችዋ በአከባቢው የሚገኘው አንድ ዴቄት ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ስትሆን ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከስራ ገበታዋ እንደወጣች አልተመለሰችም።

መሰወሯ ያስጨነቃቸው ወዳጅ ዘመዶች በከተማ በገጠሩ ፣ በዱር ሸንተረሩ ለ4 ቀናት ፈልገው አላገኟትም።

በአምስተኛው ቀን ታድያ በአከባቢው ከአንድ ቤተ እምነት አጠገብ ከሚገኘው ወንዝ ዳር ህይወትዋ አልፎ ተጥላ ትገኛለች።

የአከባቢው ህዝብ ከሞትዋ በላይ አሟሟትዋ ከፍተኛ ድንጋጤና ቁጣ ፈጥሮቦታል።

የሟችዋ አንድ አግር በአራዊት ተበልቶ ይሁን ሌላ አልተገኘም።  

የሟችዋ አስክሬን ከተገኘበት ቦታ 400 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ተጉዞ መቐለ በሚገኘው ዓይደር ኮምፕሬሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል ምርመራ ከተካሄደበት በኋላ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ሀሙስ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም በእንዳባጉና ከተማ ተፈፅሟል።

እንስትዋ እንዴት ለህልፈት በቃች ? ማን ገደላት ? በምን ምክንያት ? እንዴት ? የሚሉ የህዝብ ጥያቄዎች  የማጣራት ጉዳይ ለአከባቢው ፓሊስ የተተው ሆኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" የኑሮ ውዶነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል " - ተቃዋሚ ፓርቲዎች

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ (ኮከስ) ምን አለ ?

- የመድረክ
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)
- የኅብር ኢትዮጵያ
- የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
- የኢሕአፓ ... ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ በወቅታዊ ሁኔታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫ ልኳል።

ኮከሱ ምን አለ ?

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከሱ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር በእጅጉ ኮንኗል።

በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ " የአገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ከዕለት-ወደ ዕለት ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዙ ነው " ብሏል።

ይህም ለሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ እየዳረገን ነው ሲል ወቅሷል።

" ፖለቲካችን የተለመደውን የአፈናና አግላይነት፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ጠቅላይነት አጠናክሮ ቀጥሏል " ያለው ኮከሱ " የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአጃቢነት፣ ህዝብ ከአገልጋይነት ያለፈ የፖለቲካ መብታቸውን የማንሳት ህገመንግስታዊ መብት ተነፍጓቸው በወንጀል ተቆጥሮባቸው ፀጥ-ለጥ ብለው እንዲገዙ ተፈርዶባቸው በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ናቸው " ብሏል።

ኢኮኖሚው ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ ተሸጋግሮ ለተለያዩ የልማት መሰረተ ልማት አውታሮች ሊውል የሚችል የዓመታዊ በጀት ከፍተኛውን ድርሻ ለጦርነትና ጸጥታ ማስከበር ግብዓቶች እንዲውል ተደርጓል ሲል ወቅሷል።

" ልማትና ዕድገት ከቀለም-ቅብ ያለፈ መሰረት እንዳይኖረው ተገደናል " ሲልም አክሏል።

" የኑሮ ውድነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል " ሲልም ገልጿል።

ኮከሱ " ማኅበራዊ ህይወታችን በሥራ አጥነት፣ መፈናቀል፣ የማኅበራዊ ተቋማት መዳከምና የአገልግሎት መቋረጥ ወይም መቀንጨር፣ የሠራተኞች ብሶት መገለጫቸው ከሆነ ውሎ አድሯል " ብሏል።

" በየአቅጣጫው የሚነሱት ጥያቄዎችም የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው " ሲል ገልጿል።

" ከትምህርትና ጤና አገልግሎት ተቋማትና ሠራተኞች የሚሰማው ጩሄት በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል " ሲልም አመልክቷል።

ኮከሱ፦

- " ግጭትና ጦርነትን እያስፋፉ - የይስሙላ አግላይ የምክክርና ውይይት ስብከት ሊቆም ይገባል " ብሏል። " መንግስት / ገዢው ፓርቲ / ከማስመሰል ተላቆ ራሱንና የአገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ለሁሉን አካታችና አሳታፊ ተዓማኒና በባለድርሻ አካላትና አስፈጻሚዎች ተቀባይነት ያለው ሃቀኛ የምክክር ፣ ድርድር ፣ ውይይት መድረክ እንዲያመቻች ሽግግሩ በመጨናገፉ የቀጠለውና የተስፋፋው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።

- የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ማጠናከር ዓላማና ተልዕኮ ይዞ ፤ የገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ያቋቋሙት የጋራ ምክር ቤት ከተቋቋመበት ዓላማና ተልዕኮ እየራቀ የገዢው ፓርቲ ታዛዥ ጉዳይ ፈጻሚና አስፈጻሚ እንዲሆነ ጫና እየተደረገበት ነው " ብሏል።

- " የፖለቲካ ድርጅቶች ሃሳብ መለዋወጫ እንዲሆን የመሠረቱትን የጋራ ምክር ቤትን ብልጽግና ቀስ በቀስ በስልታዊውና በሚታወቀው የኢህአዴግ አካሄድና ዘዴዎች አሽመድምዶታል " ሲል ገልጿል።

- " ህወሓት መር የነበረው ኢህአዴግ ይሠራቸው የነበሩት ዕመቃዎች፣ ጥሰቶች፣ ተንኮልና ደባዎች፣ አስርጎ የማስገባትና የመከፋፈል ሤራዎች፣አሁን በወራሹ ብልጽግና ደምቀውና ጎልተው ያለድብብቆሽና ይሉኝታ እየተደገሙ ነው " ሲል ወቅሷል።

- " ብልጽግና በአደባባይ ኃሳብን በነጻነትና ያለመሸማቀቅ የመግለጽ መብት መከበርን ቢሰብክም በተግባር ግን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በአዋጅ፣ በመመሪያና ደንብ እያፈነ ይገኛል " ሲል ከሷል።

-  " ሽግግር በሌለበት የሽግግር ፍትህ ውዳሴ " ከንቱ ነው በማለት ከመንግስት/ የገዢ ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ጠይቋል። በመንግሥት አደራጅነት የሚቋቋም የሽግግር ፍትህ ተቋም ከዚህ በፊት ከተቋቋሙትና ያለውጤትና ሪፖርት ከተበተኑት ኮሚሽኖች የተለየ ውጤት አይጠበቅም ብሏል። ለአካታች፣ አሳታፊና ተዓማኒ የሽግግር ሂደትና ተቀባይነት ያለው ህጋዊ የፍትህ ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ እንዲተገበርና ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ አቅርቧል።

- " የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና የዲሞክራሲ አጋሮች እየተበረታቱ ሳይሆን እየተሸማቀቁ ነው " ብሏል።

-  " ዕለት ከዕለት የገዥው ብልጽግና አምባገነዊነትና አማቂነት እየጎላና እየተበራከተ ነው የመጣው " ያለ ሲሆን " የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ መጥቶ ተኮማትሯል። " ሲል ገልጿል። " በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ነፃነትና ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና በመግለጫዎች እንዲወሰን ተደርጓል " ሲልም ወቅሷል። " ሠላማዊ ሠልፍ ለመጥራት መዘጋጀት፣ ህገመንግሥት የሚፈቅደው መብት ሆኖ ሳለ- ያሳስራል፣ ለከፋም ጉዳት ይዳርጋል " ብሏል።

- " በገዥው የብልጽግና ፓርቲ ሹመኞች፣ ሃላፊነት በጎደለው ፍላጎትና ውሳኔ፣ በዋና ከተማችን ‹የኮርደር ልማት› በሚል የተጀመረው የመኖሪያና ንግድ ቤቶችንና ህንጻዎችን በማፍረስ ህዝብን በማፈናቀል ለከፍተኛ ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቀውስና ለጎዳና ተዳዳሪነት አጋልጧል " ብሏል። " ይህ ኅብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ከፖለቲካ ገለልተኛ ሙያዊ ጥናት ውጪ የሚደረገው ዜጋ አሰቃይ  እርምጃ ወደ ክልል ከተሞች እየተዛመተና ሥቃዩን በመላ አገሪቱ እያዳረሰ ነው " ሲል ተቃውሟል። " ግቡ ለቀጣዩ ምርጫ የቅስቀሳ ግብዓት ነው " ብሏል።
" የኮርደር ልማት በገዥዎች የረጅም ጊዜ አብሮነታቸውና ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቁርኝታቸው የማይፈለገውን የማኅበረሰብ አባላት ማፈናቀልና መበተን ስለሆነ ሥራው ያለምንም ተጠያቂነት፣ በማናለብኝነት መንፈስ፣ በጥድፊያ እየተካሄደ ነው " ሲል ወቅሷል።

- " በርካታ የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ወደ ጎን ተብለዋል። ውዱን የአገርና ህዝብ ሃብት ከመንገድ ስፋትና፣ ህንጻ መቀባትና ሣር መትከል አልፎ ለቤተመንግሥት ግንባታ ጭምር እየዋለ መሆኑ ለዜጎች ህይወትና ኑሮ ደንታ ማጣት- ኢሰብዐዊነት ነው " ሲል ወቅሷል።

ኮከሱን መንግስትን " ጦርነትን እንደ መግዣ ሥልቱ እየተጠቀመ ነው " በሚል ወቅሶ እንዲህ አይነት መንግሥት " የሠላምና ልማት ጠንቅ ነው " ብሏል።

" አገሪቱ ከገባችበትና ካለችበት እጅግ አሳሳቢና ፖለቲካዊ ማህበረ-ኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንድትወጣ፣ በየአቅጣጫው ከሚሰማውና ህዝባዊ የህልውና ጥያቄ፣ ከሚታየው የትጥቅ ትግል መፍትሄ ለመስጠት ተኩስ ቆሞ ሃቀኛ፣ ሁሉን-አቀፍ፣ አሳታፊ፣ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ ለማውረድ ተዓማኒ ውይይት/ምክክርና ድርድር እንዲደረግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።


(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" መልሼ አጤነዋለሁ " - ሶማሊያ

የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ " መልሶ ለማጤን " ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

አንድ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ " የሶማሊያ መንግሥት ለልዑኩ ኅይል ከሚያዋጡት ሀገራት ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ወታደሮችን አግኝቶ ደልድሏል " ሲሉ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ አንዳቸው የሌላውን ሉዐላዊነት፣ እንዲሁም የግዛት አንድነት እንደሚያከብሩ አንካራ፣ ቱርክ ላይ ባለፈው ሳምንት ስምምነት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።

ስምምነቱ በመፈጸሙም ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአዲሱ ልዑክ ውስጥ የመካተታቸውን ጉዳይ " እንደገና እንደምታጤን "  ባለስልጣኑ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈጸመችውንና የባሕር በርን የተመለከተውን የመግባቢያ ስምምነት የማትሰርዝ ከሆነ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሶማሊያ ስትጠይቅ ቆይታ ነበር።

ሶማሊያ ይህን ብትልም ኢትዮጵያ ግን በሶማሊያ የሚገኙት ወታደሮቹ አል ሻባብን መዋጋት እንደሚቀጥሉ ሲያስታውቃ ነበር።

የኢትዮጵያ ትኩረት ' አል ሻባብ ' ላይ መሆኑን የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በቅርቡ አስታውቀው ነበር።

የኢትዮጵያ 🇪🇹 ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋት የደም ዋጋ ከፍለዋል ፤ ዛሬም ድረስ እየከፈሉ ነው። 

ኢትዮጵያ ለሱማሊያ ያልከፈለችው መስዕዋትነት የለም ፤ ይህ ውለታ ተረስቶ ነው የሶማሊያው መሪ ሀሰን ሼክ መሀሙድ አስተዳደር ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ብዙ የሚያስተዛዝብ ንግግር ሲናገር የከረመው።

በአንካራው ስምምነት ፕሬዜዳንቱ ፤ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሀገራቸው (ሶማሊያ) ለከፈሉት መስዋዕትነት በይፋ እውቅና ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia
ታታሪ የወጣቶች ዋዲያህ የቁጠባ ሒሳብ

የሸሪዓውን የዋዲያህ መርህ ተከትሎ በሕብር ሀቅ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ስር የሚገኘውን እና እድሜያቸው ከ 18-30 ዓመት ለሆኑ ወጣቶች የቀረበውን ታታሪ የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ እንድትጠቀሙ ተጋብዘዋል፡፡ 

ጁመዓ ሙባረክ!

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡


#islamicbanking #islamicfinance #interestfree #YouthfulIslamicBanking
🎉 ቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ተከፈተ!!

የአገራችን ትልቁ የበዓል ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከልና በመስቀል አደባባይ በድምቀት ተከፍቷል፤ ግብይቱ ቢሉ መዝናኛው ሁሉ ተሰናድቷል፡፡

💁‍♂️ የመግቢያ ትኬትዎን በቴሌብር ሲቆርጡና ያሻዎን ሲገበዩ እስከ ብር 2500 ላለው 10% ተመላሽ ያገኛሉ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ወይም *127# ይጠቀሙ!

🏑 በገና ሸመታ አይቆጡም ጌታ!!


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#ግብር

🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች

🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

" በ2015 ዓ/ም ነበር ጥናቱ የተጠናው ፤ ከዛ 'ተግባራዊ አይሁን፣ ትክክል አይደለም' ተብሎ የተቀመጠ ጥናት ነው አሁን መመሪያ ተደርጎ በትዕዛዝ የወረደው " ሲሉ ነው የተናገሩት።

አስመጪዎቹ ስለዝርዝር ቅሬታቸው ምን አሉ ?

" አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን አላስፈላጊ ግብር እየጠየቀን ነው። ይሄን የሚያደገው 'ሲስተም አዘጋጅቻለሁ' በሚል ነው።

አዲሱ ሲስተም የስሪት፣ የተመረተበትና የመጣበት አገር ይጠይቃል፣ በጥናት መልክ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን ብሎ በአዲስ አበባ በሁሉም ቅርንጫፎች ኤክስኤል ሰርቶ አውርዶ ሥሩ ብሏል።

'ከጉምሩክ ዴክላራሲዮን ላይ ሒሳቡ ሲሰላ ከ45 በመቶ በላይ የሆነ ትርፍ እያተረፋችሁ ነው’ በሚል ነው አዲስ አሰራር ያመጣው።

ይህ መመሪያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተለዬ፣ ፌደራልና ክልል ላይ የሌለ፣ በአዲስ አበባ ብቻ፣ የመኪና አስመጪዎችን ብቻ በተመለከተ የተዘጋጀ መመሪያ ነው።

በዚህ መመሪያ መሠረት የተጠየቅነው ግብር አላስፈላጊ፣ ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ነው። ምክንያቱም ግብር በህግ ነው እንጂ በጥናት አይደለም የሚከፈለው። 

ግብር ሲከፈል ህግ ተረቆ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ነው። ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የግብር መመሪያ የሚያወጣው  ደግሞ ገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

ይሄን አዲስ መመሪያ ግን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በራሱ በደብዳቤ መልኩ ነው ወደታች ያወረደው ከአሰራር ውጪ በሆነ መልኩ


እስከዛሬ ጉምሩክ ባስቀመጠው መሠረት ከፍተኛው ጣራ 9% ተደርጎ እኛም 4ም፣ 5ም% አተረፍን ብለን አቅርበን ነበር የምንፈፍለው።

አሁን ግን ቢሮው ሌላ የራሱን ሰንጠረዥ አዘጋጅቶ ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ይህንን መመሪያ አወረደ በትዕዛዝ መልክ። መመሪያው የወረደው ‘ከ45 በመቶ በላይ እያተረፋችሁ ነው የዚህን ግብር ክፈሉ’ በሚል ነው።

ከዚህ ቀደሙ ግብር ጋር ሲነጻጸር 5% አትርፌአለሁ ብለሸ አሳውቆ ግብር ሲከፍል የነበረን ሰው ‘45% ታተርፋለህ’ ማለት በጣም ብዙ እጥፍ ነው። የህግ አግባብ የለውም አሰራሩ። 

በፌደራል ደረጃ ንግድ ፈቃድ አስመጪዎች ያላቸው መኪና መሸጫ አላቸው። የእነርሱ በኖርማሉ ነው፣ እነርሱን አይመለከትም መመሪያው። ክልል ያሉትንም በተመሳሳይ አይመለከትም። 

አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው ክፍለ ሀገርም ሆነው የክፍለ ሀገር ፈቃድ አውጥተው (ለምሳሌ የክልል፣ የፌደራል ፈቃድ ያላቸው) ከኛ ጋር ተመሳሳይ መኪና የሚሸጡ አሉ።

እነርሱን ግን ይሄ አዲሱ የግብር መመሪያ አይመለከትም። አንድ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ አይነት መኪና እየሸጡ እያሉ
ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው።

የፌደራል ገቢዎች የማያውቀውን ተመን እንዴት አንድ የከተማ አስተዳደር በራሱ ያወጣል? ይሄ አሰራር የህግ ግራውንድ የለውም። ቅሬታችን ይሰማልንና ትግበራው ይስተካከልልን”
ብለዋል።

አዲስ አበባ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጭዎች ከዚህ ቀደም ያልነበረ አሰራር ወርዶ ከመጠን ያለፈ ግብር ተጠየቅን ለሚለው ቅሬታቸው ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል ለአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጥያቄ አቅርበናል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ምን ምላሽ ሰጡ?

" በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው።

የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለውም። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። ዋናው ዓላማ ግን ከፍተኛ የሆነ የታክስ ስወራ ስላለ ያን ለማስቀረት ነው።

ከተማው ማንኛውም መኪና የሚገዛ ሰው ስንት ብር ነው የገዛው? በትክክል በገዛውና በከፈለው ገንዘብ ልክ ደረሰኝ ተሰጥቶታል ወይ? በስት አካውንት ነው ገንዘብ እንዲያስገባ የሚጠየቀው? የሚለው የአደባባይ ምስጢር ነው። 

ስለዚህ የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

እዚህ ላይ ልዩነት አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው መጥቶ ልንወያይ እንችላለን በራችን ክፍት ነው "
ብለዋል።

(ኃላፊው፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ላቀረብንላቸው ጥያቄዎች የሰጡን ሙሉ ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia