TIKVAH-ETHIOPIA
#አፈሳ 🔵 “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” - የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች 🔴 “ ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” - ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች “ በመንግስት ፀጥታ አካላት ” እየታፈሱ መሆኑን፣ በዚህም እንዲህ አይነት ድርጊት በሚፈጸምባቸው ቦታዎች ወጣቶች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገደበ ነዋሪዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ…
#EHRC
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህጻናት እና የአእምሮ ህሙሟን ጨምሮ በርካቶች በግዳጅ ተይዘው እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል።
ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳውቋል።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት " የመከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎችን ምልመላ እናከናውናለን " በሚል የሰራዊቱን አሠራር እና መስፈርቶች በጣሰ ሁኔታ ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን በግዳጅ ስለመያዛቸው እና የተያዙትን ለመልቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ ስለማስገደዳቸው ኮሚሽኑ ከነዋሪዎች መረጃዎች ደርሰውት ነበር።
ይህ ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ክትትል እና ምርመራ አከናውኗል።
በዚህ ክትትል እና ምርመራ በኦሮሚያ ክልል ፦
- በአዳማ፣
- በቢሾፍቱ፣
- በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን በማነጋገር፤ እንዲሁም የሚሊሻ እና የፖሊስ ተቋማትን ጨምሮ ከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በማወያየት ስለጉዳዩ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን አሰባስቧል።
ምንም እንኳን ሀገር መከላከያ ስርዓቱን እና ህጉን ተከተለ መልኩ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሀገር መከላከያን እንዲቀላቀሉ ማስታወቂያ ቢያወጣም ፤ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የምልመላ ሂደቱን በመከላከያ ሚኒስቴር መስፈርቶች መሠረት እንዲያከናውን የተጠየቀ ቢሆንም የክልሉ የአስተዳደር አካላት እና የጸጥታ ኃይሎች አባላት በመከላከያ ሚኒስቴር ከተገለጸው የምልመላ መስፈርት ውጪ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን " የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ " በሚል በግዳጅ እንደያዙ ተረጋግጧል።
በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በዚህ አግባብ የተያዙ ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስገደዳቸውም በኢሰመኮ ምርመራ ተረጋግጧል።
ኢሰመኮ ክትትል እና ምርመራ ባደረገባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ከክልሉ አመራሮች ጋር በመተባበር " የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ " በሚል ተይዘው የነበሩ ሕፃናትን እና የአእምሮ ሕሙማንን ጨምሮ በግዳጅ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ለማስለቀቅ ተችሏል።
በወቅቱ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ችግሩ መኖሩን አምነዋል።
የማቆያ ስፍራዎችን በመፈተሽ የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን እና ድርጊቱን በፈጸሙ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሚሊሻ አባላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ለኢሰመኮ ገልጸዋል።
ኢሰመኮ ክትትል ባደረገባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችም ከመስፈርት ውጪ የተደረገ ምልመላ መሆኑን በመግለጽ በክልሉ የጸጥታ አካላት የተያዙ ሰዎች ከማቆያ ስፍራዎች እንዲለቀቁ ያደረጉ መሆኑን ተገንዝቧል።
ይህ የምርመራ ሪፖርት በመጠናቀር ላይ በነበረበት ወቅት በተለይም ኅዳር 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሲከናወን የቆየው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምልመላ ሥራ መጠናቀቁን እና ሰራዊቱ በፈቃደኛነት የተመዘገቡ እና የምልመላ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ምልምሎችን ለይቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲገቡ ማድረጉን ኢሰመኮ ተገንዝቧል።
(ኢሰመኮ የላከልን ሙሉ የምርመራ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#EHRC ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህጻናት እና የአእምሮ ህሙሟን ጨምሮ በርካቶች በግዳጅ ተይዘው እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል። ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳውቋል። በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ…
በሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በማቆያ አዳራሽ ከነበሩ እና ኢሰመኮ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን የገለጹ ሲሆን አንድ ሕፃን ደግሞ ዕድሜው 11 ዓመት መሆኑን ገልጿል።
ከት/ቤት ሲወጡ #ከነዩኒፎርማቸው ፤ ሀሌሉ ወረዳ ወደ ሚገኘው ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ሁለት የ15 ዓመት ሕፃናት ወደ አዳራሽ ከገቡ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው ገልጸው የገቡበትን ሁኔታም አስረድተዋል።
ሕፃናቱ ፤ “ ከትምህርት ቤት ስንመለስ መከላከያ ለሚገቡ 25,000 ብር ይሰጣል ብሎ አንድ ግለሰብ በባጃጅ አሳፈረን፤ ከዚያ 010 ቀበሌ (ሀሌሉ ወረዳ) ወደ ሚገኘው አዳራሽ ገባን፤ ነገር ግን ከገባን በኋላ መውጣት አልቻልንም ” ሲሉ ነው የገለጹት።
በጅማ ከተማ ኢሰመኮ ያነጋገረው የ14 ዓመት ሕፃን ስለተያዘበት ሁኔታ ሲያስረዳ፦
“ ኅዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት አካባቢ ወደ ቤት እየሄድኩ እያለሁ መንገድ ላይ ቆመው የነበሩ ሚሊሻዎች ባትሪ አብርተውብኝ አስቆሙኝ፤ መታወቂያ ሲጠይቁኝ ዕድሜዬ ገና 14 ዓመት ነው፤ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ መታወቂያ የለኝም ብዬ ስመልስ፣ ቀበሌ ሄደህ ጉዳይህ ይጣራል በማለት ወደ ቀበሌ ወስደው ብዛታቸው ከ20 በላይ ከሚሆኑ ወጣቶች መካከል ቀላቅለውኝ ሄዱ። ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት መያዜንም ወጣቶቹ ናቸው የነገሩኝ። በማግስቱ በድብቅ ለቤተሰቦቼ ደውዬ ካሳወቅኩ በኋላ ለመውጣት ችያለሁ ” ብሏል።
#EHRC #OROMIA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Myanmar (Burma) #ማይናማር " በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር " - ሽኩር (የአይን ምስክር) " ስሜ ሽኩር ይባላል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለምን ባመሰቃቃላ ግዜ እኔ ሥራ ካጡ ሰዎች አንዱ ነበርኩ። በአገራችን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጉዳዩን የበለጠ አባብሶት የነበረ ቢሆንም ለመኖር ሲባል ለ 7ወር የህል በመምህርነት አገልግያለሁ። ነገር ግን ገቢዬ ፍላጎቴን ለማሟላት በቂ አልነበረም።…
" አሁንም በርካታ ሰዎች ከኢትዮጲያ እየጎረፉ ይገኛሉ !! " - በስፍራው የሚገኝ የአይን ምስክር
በርካታ የሀገራችን ወጣቶች " ታይላንድ ስራ አለ " እየተባሉ ወደ ማይናማር ድንበር ቦታ ተወስደው ካምፕ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረጉና በዓለም አቀፍ የኦንላይ ማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ እየተደርጉ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዬጵያ ለረጅም ጊዜ ማሳወቁ ይታወሳል።
አሁንም በርካታ ወጣቶች እዛው ናቸው።
ከአደገኛው ስፍራ ለመውጣት እገዛ ይፈልጋሉ።
ለዛሬ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆነ እና በደላሎች ተታሎ ባልፈለገው ተግባር ላይ ተሰማርቶ እየተሰቃየ የሚገኝን አንድ ወጣት ምስክርነት እናቀርባለን።
ከማይናማርና ሜሱት ድንበር ፦
" ስሜ ይቆየኝ ፤ እኔ ኤዢያ ውስጥ በማይናማር እና በሜሱት ድንበር ላይ ነኝ።
ወደዚህ የደረስኩት በደላሎች ቅብብሎሽ ነው።
ስራ ያለው ታይላንድ ከተማ ላይ ነው ብለውኝ ነበር የመጣሁት ግን አንድ ቀን ታይላንድ አደረኩ በቀጣይ ቀን ወደ ሜሱት መጣሁ።
ስሄድ በVisit Visa 15 ቀን ነበር ለታይላንድ የከፈልኩት አሁን ግን እሱም ቀኑ አልቋል።
የጠበኩት ስራ ሌላ ነበር እያሰሩን ያሉት ሰዎችን በበየነ መረብ (ኦንላይን) ማጭበርበር ነው።
በርካቶች ማጭበርበር ስላልቻሉ ታግተዋል።
እኔ እዚህ ከመጣሁ 3 ወሬ ነው ነገ ምን እንደሚያደርጉኝ አላቅም በጣም አምባገነን እና ጨካኝ ናቸው።
ቻይኖች ናቸው የሚያሰሩን እኛንም በየቀኑ እያስጠነቀቁን ነው።
እዚህ ግቢ ፎቶ መውሰድ የተከለከለ ነው። በየቦታው በየመቀመጫው የCCTV ካሜራ እያንዳንዱን ሰው ይቆጣጠራል።
ፎቶ ሲያነሳ / ቪድዮ ሲቀርጽ የተገኘ ሰው 7 አመት የጫካ እስር እና 100 ሺህ የታይላንድ ባት ይቀጣል።
አሁንም በርካታ ሰዎች ከኢትዮጲያ እዚህ እየጎረፉ ይገኛሉ ፤ በየቀኑ ከ30 በላይ የሀገሬ ልጆች ወደዚህ ስፍራ ይመጣሉ። እባካችሁ በጭራሽ ወደዚህ እንዳትመጡ።
ለመምጣት እንዳያስቡት ጭምር ነው የማስጠነቅቀው።
እኛንም የኢትዮጵያ መንግስት እጁን ከቶ ያስወጣን ከዚህ ጉድ።
ይሄን መረጃ የምሰጠው እኔ የአይን ምስክር ስለሆንኩ ነው።
እኔን እግዚአብሔር ያውጣኝ ከዚህ።
ለሌሎች እኔ ያየሁትን ስቃይ እንዲያዩ አልመኝም።
በርካታ ኢትዮጵያን እና የምስራቅ አፍሪካ ሰዎች በቃ የአውሮፓ ሲቀር በርካቶች እዚህ ናቸው። እኔ ለሀገሬ ልጆች ይሄን መረጃ አድርሼ ለመታደግ ከቻልኩ ብዬ ነው።
ወጣት እያለቀ ነው እየተበዘበዘ በሰው ሀገር እኔን ጨምሮ የደላላ ስልክ እና የቴሌግራም ዩዘርኔም አለኝና ፎቶም አለኝ ለሚፈለገው አካል ማጋራት እችላለሁ። "
🚨 ከላይ ያለው ምስል ያሉበት ግቢው ነው። ግቢው ሶስት ሲሆን KK1 , KK3 , KK2 ይባላሉ። በጣም ሰፊ እና ማንም የማይደርስበት ነው።
ወጣቶችን ከተለያዩ ሀገራት በደላሎች አታለው ወስደው ምንድነው የሚያሰሯቸው ? በዝርዝር ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/90728

#ArbaMinch : ላለፉት በርካታ ዓመታት አርባ ምንጭ ላይ ሲገነባ የቆየው የጋሞ አደባባይ ተመርቋል።
" አደባባዩ በዞኑ የሚገኙ ህዝቦችን ባህል እና ትዉፊት በሚወክል መልኩ ነው የተሰራው " ሲል የዞኑ አስተዳደር ገልጿል።
ለዚህ አደባባይ ከ122,000,000 ብር (መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ብር) በላይ ወጪ እንደተደረገበት ነው የተነገረው።

@HibretBanket
Experience 25+ YEARS OF BANKING
At Hibret Bank, we are committed to exceeding your expectations.
Hibret Bank
United, We prosper!
📞 For more information call our free call center - 995.
🤳 To receive new information join our Telegram page. https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 Visit our other social media pages and wesite on linktr.ee/Hibret.Bank

#TecnoAI
በንግድ እና ቢዝነስ ስራዎት ሁነኛ አማካሪ፣ አጋዥ እና ባለሙያ ያስፈልጎታል? አዲሱ ቴክኖ ኤ አይ ሁሉንም ስራዎትን ጥንቅቅ ባለ ደረጃ ሊከውን እየመጣ ነው፡፡
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡
https://www.tiktok.com/@tecnoet
@tecno_et @tecno_et

“ የህክምና ገንዘብ ባለማግኘቱ ምክንያት ወጣቱ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ” - የታማሚው ወዳጆች
የልብ ቧንቧ መደፈን ህመም የገጠመው ሚካኤል ኑሩ የተባለ ወጣት በገንዘብ እጥረት ሲከታተለው የነበረውን ህክምና በማቋረጡ ረዳት በሌለበት የአልጋ ቁራኛ መሆኑን የቅርብ ሰዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የታማሚው የቅርብ ሰዎች በሰጡት ቃል፣ “ ታማሚው ወጣት ወንድም፣ እህት የለውም። ለእናቱ አንድ ልጅ ነው። እናቱም የአልጋ ቁራኛ ናቸው ” ብለዋል።
የ25 ዓመቱ ወጣት ሚካኤል ሹፌር እንደነበር በመታመሙ ሥራ እንዳቆመ፣ በመጀመሪያ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ቢወሰድም ወረፋ መጠበቅ ስላለበትና ህመሙ ደግሞ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ የግል ሆስፒታል መታከም እንዳለበት እንደተነገረው አስረድተዋል።
“ በመጀመሪያ ህክምና ሁላችንም አዋጥተን አሳከምነው በግል ሆስፒታል። ከዚያ በኋላ የተጠየቅነውን ብር ማግኘት አልተቻለም። በ400 ሺሕ ብር የመጀመሪያውን ህክምና ነበር ማግኘት የሚችለው የሚያስፈልገው ከ700 ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ነው የተባለው ” ነው ያሉት።
“ ሁለተኛውን ህክምና ለመከታተል ብር ስሌለ ሆስፒታሉ አስወጣው ‘ብሩን ስታገኝ ረጅም ጊዜ ሳትቆይ መጥተህ ታከም’ ተባለ። የህክምና ገንዘብ ባለማግኘቱ ምክንያት ወጣቱ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ከመታከሙ በፊት ይታዩበት የነበሩ የበሽታው ምልክቶች እንደተስተዋሉበት እንደሆነ፣ ህክምናውን ለማጠናቀቅ 500 ሺሕ ብር ስለሚያስፈልገው ልበ ቀና ኢትዮጵያዊ ሁሉ ርብርብ እንዲያደርጉለት ተጠይቋል።
መርዳት ለምትሹ የታሪኳ ተሰማ ለማ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000029724842 ነው። ደውሎ ለመጠየቅ 0913645873 የታሪኳ ስልክ ቁጥር ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#ወጣቶቻችን😭 " በሶስት ወራት ብቻ ከ6,600 በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰድዋል !! " - የትግራይ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ አውራ መንገዶች " ልጄ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት ሲሄድ በአጋቾች ተይዞ ይህንን ብር ክፈል ፣ ካልከፈልክ ትገደላለህ ብለውኛል እርዱኝ " የሚሉ በትልቅ ባነር በተቀመጠ የወጣቶች ፎቶ አስደግፈው እርዳታ የሚለሙኑ ወላጆች ተበራክተዋል። …
#ስደት🚨
" ባለፉት 15 ወራት ብቻ ከ38 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሰደዋል ፤ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል " - የትግራይ ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ
🚨 " ያሉት ችግሮች ወጣቱን ተስፋ በማሳጣት ህገወጥ ስደትን እንደ ብቸኛ አማራጭ እንዲመለከት እያደረጉት ነው ! "
በትግራይ በተካሄደው አስከፊና እውዳሚ ጦርነት ምክንያት የወጣቶች ህገ-ወጥ ስደት እንግልትና ሞት በእጅጉ ተባብሶ መቀጠሉ ተነግሯል።
የፕሪቶሪያ ውል ተሟልቶ አለመፈፀሙ ፣ የመልሶ ግንባታ ስራዎች አለመጀመራቸው ፣ ሰፊ የስራ እጦት መኖር ለህገ-ወጥ የወጣቶች ፍልሰት መባባስ ምክንያቶች ናቸው ተብለዋል።
ይህን የሰማነው የትግራይ የስፖርትና የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከለጋሽ ድርጅቶች በመተባበር " ህገ-ወጥ ስደት " በሚል ካዘጋጀው አንድ መድረክ ላይ ነው።
ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ የበርካታ ወጣቶች ህይወት እየነጠቀ ያለውን ህገ-ወጥ ስደት አስመልክቶ በ49 የክልሉ ወረዳዎች በተካሄደ ጥናት ባለፉት 15 ወራት ብቻ ከ38 ሺህ በላይ ወጣቶች መሰዳዳቸው ያሳያል።
ከ38 ሺህ ስደተኞች ከ6 ሺህ በላይ ባለፈው ዓመት በጉዞ እያሉ ለህልፈት ተዳርገዋል ፤ አካላቸው የጎደለ አሉ ፣ አድራሻቸው የጠፉም ብዙ ናቸው።
2017 ዓ.ም ከገባ ወዲህ ብቻ ከ6 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገወጥ መንገድ ተሰደዋል ከነዚሁ ደግሞ 300 ገደማ ለህልፈት ተዳርገዋል።
አደጋው የክልሉ ከፍተኛ ስጋት ወደ መሆን ተሸጋግረዋል ሲል ቢሮው አሳውቋል።
በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ፦
⚫ የኢኮኖሚ አውታሮች ወድመዋል ፣
⚫ የብድር አገልግሎት መስጠት እጅግ የደከመ ነው፣
⚫ ሰፊ የስራ እጦት አለ እነዚህን እና ሌሎች ችግሮች ወጣቱ ተስፋ በማሳጣት ህገወጥ ስደት እንደ ብቸኛ አማራጭ እንዲመለከት አድርገውታል።
ይህ ከፍተኛ ችግር እንዲቀረፍ የፌደራል መንግስትና ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፋቸው እንዲቸሩ የትግራይ ክልል ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ። ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል። በዚህ መሰረት፦ ➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር ➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር ➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር ➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር ➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር…
#ነዳጅ
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ " የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ " ሲል አሳስቧል።
የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?
➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር
➡️ የአውሮፕላን ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።

#Ethiotelecom
⏰ የአክሲዮን ሽያጩ ሊጠናቀቅ እየተቃረበ ነው!
❇️ የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ብስራትን ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጡ ይገኛሉ!
የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር፣ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 9,900 ብር (33 አክሲዮኖች)፣ ከፍተኛው 999,900 ብር (3,333 አክሲዮኖች) ነው፡፡
💁♂️ የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይከናወናል፤ እርሶም የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፡፡
🗓 ለገበያ የቀረቡት አክሲዮኖች ቀድሞው ተሸጠው ካልተጠናቀቁ እስከ ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም ይቆያል፡፡
ለተጨማሪ: https://bit.ly/3Y9JUae ይመልከቱ!
📖 የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን https://teleshares.ethiotelecom.et/ ያንብቡ፡፡
#telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia