TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቀድሞ / ነባር ነኝ አይደለሁም የሚለውን ከፓሊስ እንነጋገርበታለን ፤ ያኔ ግልፅ ይሆንላቸዋል !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ሳምንት ህዳር 17/2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ቡድን ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ አማኒኤል አሰፋ በሰጡት መግለጫ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " የቀድሞ ፕሬዜዳንት " ሲሉ ጠርተዋቸው ነበር። ህዳር 22/2017…
#ሹመት

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን 6 አዳዲስ ሹመቶች ሰጥተዋል።

ከስድስቱ ሽመቶች ሁለቱ በደብረፅዮን ገ / ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተሾሙትን በማንሳት የተሰጠ ነው።

በዚሁ መሰረት ፕሬዜዳንቱ ከህዳር 20/2017 ዓ.ም  ጀምሮ የሚፀና በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የመቐለ ከንቲባ በመሆኑ የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) በመሻር በብርሃነ ገ/ዮሱስ ተክተዋል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ምክትል የስራ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው ከህዳር 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የዓዲግራት ከንቲባ በመሆን የተሾሙት ረዳኢ ገ/ሄር ምትክ ኪ/ማርያም ወ/ሚካኤል ምክትል የቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ፕሬዜዳንቱ በጡሮታ በተገለሉት ሓዱሽ ካሱ ምትክ ዶ/ር ገብሩ ካሕሳይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አድርገዋቸዋል።

ኮማንደር ተስፋይ ገ/ማርያም በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል ማጣራት ሃላፊ ፤ ኮማንደር ጌታቸው ኪሮስን በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል መከላከል ሃላፊ እንዲሁም አቶ ሃይላይ ኣብራሃ በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የሰው ሃይል ልማት ዘርፍ ሃላፊ አደርገው ሹመዋል።

በቅርቡ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው በተናገሩት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ምትክ ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ደብዳቤ መሾማቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም !! "

" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም ! " ያለው የእግር ኳስ ተጫዋች ግብረሰዶማውያን ለመደገፍ ሲባል ክንድ ላይ የሚጠለቀውን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል።

በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፍልሚያ አፍቃሪያን እንዳሉ ይታወቃል።

ከየትኛውም ሀገራት በላይ ደግሞ የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የሚካሄዱት ፍልሚያዎች እጅግ ብዙ ተመልካች ያላቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከፉክክር ጋር ያጣመሩ ናቸው።

በተለይም የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ሳይቀር እጅግ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለውና ብዙ ተመልካች ያለው ነው።

ከህጻን እስከ አዋቂ፣ አዛውንቶች ሳይቀሩ ነው ፍልሚያውን የሚከታተሉት።

ነገር ግን በየዓመቱ ይህ የእግር ኳስ ፍልሚያ የሚደራበት ወር በተለይም ሃይማኖተኛ የሆኑ የእግር ኳስ ተመልካቾችን የሚያስቀይም ነው።

ምክንያት ? ሊጉ ውስጥ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ ሲባል ዘመቻ ስለሚካሄድበት ነው።

ሰዎቹ " እኩልነትን ለማምጣት " ይበሉት እንጂ በበርካታ ሃይማኖተኛ እግር ኳስ ተመልካቾች እና ተጫዋቾች ዘንድ የሚወገዝ ተግባር ነው የሚፈጽሙት።

የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ለግበረሰዶማውያን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት አምበሎቻቸው የግብረሰዶማውያኑን መለያ ምልክት ክንዳቸው ላይ እንዲያጠልቁ ያደርጋሉ።

ይህን ዘመቻ የሚያደርጉትም እኤአ ከኅዳር 29 እስከ ታኅሣሥ 5 ነው።

ከቀናት በፊት በነበረ አንድ ጨዋታ ላይ ግን የአንድ ክለብ አምበል " እኔ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ምልክቱን ሳያድረግ ቀርቷል።

የተጨዋቹ ስም ሳም ሞርሲ ይባላል ፤ ኢፕስዊች ታውን የተባለው ክለብ አምበል ነው።

በእምነቱም የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የግብፅ ዜጋ ነው።

ይኸው ተጫዋች ነው ቡድኑ ኖቲንግሃም ፎረስት ከተባለው ቡድን ጋር በተጫወተበት ወቅት ክንዱ ላይ ምልክቱን " አላጠልቅም " ብሎ ጨዋታውን ያካሄደው።

ክለቡ ባወጣው መግለጫ ምልክቱን ያላደረገው " በሃይማኖቱ ምክንያት ነው ፤ ውሳኔውን እናከብራለን " ብሏል።

ክለቡ አክሎም ፤ የግብረሰዶማውያኑን ምልክት የሚያሳየውን የአምበሎች መለያ በኩራት እንደሚደግፍ ፤ ከግብረሰዶማውያን ማኅበረሰብ ጋር አብሮ እንደሚቆም ፤ እኩልነት እና ተቀባይነት እንዲንሰራፋ እንደሚሰራ ገልጿል።

ከሳም ሞርሲ በስተቀር ሌሎች የፕሪሚዬር ሊጉ አምበሎች የግብረሰዶማውያንን ባንዲራ አጥልቀው ሲጫወቱ ነበር።

#SamMorsy #PremierLeague #Muslim

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም !! " " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም ! " ያለው የእግር ኳስ ተጫዋች ግብረሰዶማውያን ለመደገፍ ሲባል ክንድ ላይ የሚጠለቀውን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል። በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፍልሚያ አፍቃሪያን እንዳሉ ይታወቃል። ከየትኛውም ሀገራት በላይ ደግሞ የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የሚካሄዱት ፍልሚያዎች እጅግ ብዙ ተመልካች ያላቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከፉክክር ጋር…
" እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ !! "

በሀገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ በመላው ዓለም ላይ በቢሊዮኖች ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ በሚል በየአመቱ ዘመቻ ያደርጋል።

ይህንን ዘመቻ የሚያደርገውም በእያንዳንዱ ክለብ አምበል ክንዶች ላይ ግብረሰዶማውያንን የሚገልጸውን ባዲራ / እንዲያደርጉ በማድረግ ነው።

ይህን የሊጉን ተግባር እጅግ በርካታ ሃይማኖተኛ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ነው የሚያወግዙት።

በዘንድሮው ዓመት የሊጉ ፍልሚያ ኢፒስዊች ታውን የተባለው ክለብ አምበል እና የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲ " እኔ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል።

ከዚህ ባለፈ ግን አንድ የሌላ ክለብ ተጫዋችና አምበል የክርስትና እምነት ተከታይ ክንዱ ላይ ምልክቱን ቢያደርግም ከላይ " እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ !! " የሚል ፅሁፍ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳደሮች እንዳስቆጣ በዚህም ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተሰምቷል።

ተጫዋቹ ማርክ ጉሂ ይባላል ፤ እድሜው 24 ሲሆን የአይቮሪኮስት ዝርያ ያለበት የእንግሊዝ ዜጋ ነው።

የሚጫወትለት ክለብ ክርስታል ፓላስ የሚባል ነው።

ይኸው ተጫዋች ነው ባለፈው ቅዳሜ ኒውካስትል ከተባለው ሌላኛው የሊጉ ክለብ ጋር ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ግብረሰዶማውያንን የሚደግፈውን ምልክት ክንዱ ላይ ቢያጠልቅም ከላዩ " እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ ! " የሚል ፅሁፍ ፅፎበት በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

በዚህም የሊጉን አስታዳዳሪዎች አስቆጥቶ ቅጣት ሊጥሉበት እንደሆነ ተነግሯል።

የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ በየዓመቱ አምበሎች የግብረሰዶማውያን ምልክት የሆነውን የተለያየ ቀለም ያለው ምልክት በክንዳቸው አጥልቀው እንዲጫወቱ ያደርጋል።

#Guehi #Christian #PremierLeague

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ጊዜያዊ አስታዳደሩ የወሰደው እርምጃ ህዝቡን ወደአላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ ነው " - የመቐለ ከተማ ምክር ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ 

የመቐለ ከተማ ም/ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ከህዳር 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሰጠው የመቐለ ከንቲባ ሹመት ከመቃወም አልፎ " ህገ-መንግስት የጣሰ ተግባር " ብሎታል። 

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ህዳር 24/ 2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር በምክር ቤት አብላጫ ድምፅ የተሾሙ ከንቲባ በስራ ላይ እያሉ የምክር ቤት እና የህዝብ ሉአላውነት በመጣስ ፓሊስ ስራቸው እንዳይሰሩ አግዷል ብሏል።

" በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ህጋዊ ያልሆኑ ከንቲባ በአስተዳደሩ አንድ አዳራሽ መግለጫ እንዲሰጡ ተደርገዋል " ሲልም ገልጿል።

" በምክር ቤት በስርዓት የተሾሙ ከንቲባ ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ የመቐለ ፓሊስ ከህግ አገባብ ውጪ ፅህፈት ቤታቸው በማሸግ ህዝብ አገልግሎት እንዳይገኝ አስተጓጉለዋል " ሲል ከሷል።

" የፓሊስ ኢ-ህጋዊ ተግባር  አገልግሎት ያጣ ህዝብ ወዳልተፈለገ ሽብርና ቀውስ እንዲገባ አድርገዋል " ብሏል።

በተጨማሪ የቋም ኮሚቴው በመግለጫ ምን አለ ?

👉 " በህገ-መንግስት የተሰጠ ስልጣን በመቀማት አምባገነን ስርዓት ለመትከል የተፈፀመ ተግባር ነው ይህንን እንኮንናለን። የተፈፀመው አግባብነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲታረም ጥሪ እናቀርባለን። "

👉 " የመቐለ ፓሊስ አመራር በህገ-መንግስት የተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው የፈፀመው ህገ-ወጥ ተግባር በማስተካከል በምክር ቤት የተሾሙ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ሳይውል ሳያድር  ስራቸው እንዲሰሩ እና አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲያደርግ እንጠይቃለን "

👉 " የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የተፈፀመው የህግ ጥሰት በመገንዘብ ህግ እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን "

👉 " የመቐለ ከተማ ህዝብ ህገ-ወጥ ተግባሩ በመቃወም ከምክር ቤቱ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ እናቀርባለን "

👉 " የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር የምክር ቤቶች ሉአላዊ ስልጣን በመጣስ የወሰደው እርምጃ ህዝቡ ወደ አላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ መሆኑ በመገንዘብ በዚሁ በህገ-መንግስት ጥሰት የተሳተፉት አካላት በህግ እንዲጠይቃቸው ጥሪ እናቀርባለን "

... ብሏል።



በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሸሙት አዲሱ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ መደበኛ ህዝባዊ አገልግሎት መስጠት አንደሚጀምሩ ታማኝ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ሰጥተውታል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ልመና አልነበረም ማለት አይደለም ፤ አሁን ግን እየተባባሰ ሄዷል ! ... የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው " - አቶ አበረ አዳሙ

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ 8ኛ መደበኛ ሰብሰባው አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት ከም/ቤት አባላት ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ሚኒስትሩም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑ አቶ አበረ አዳሙ ምን ጠየቁ ?

" 1. በዓለም አቀፍ ተጨባጭ ሁኔታዎች ምክንያት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ የኑሮ ውድነቱን እያናረው ከመሆኑንም በላይ በተለይ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው ምክንያት የለሽ ጭማሪ የህዝቡን ኑሮ እንዲመሰቃቀል አድርጎታል።

ለምሳሌ ፦
- ጤፍ
- ስንዴ
- ምስር ... ሆነ ሌሎች የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ቢሆኑም በጥራት እና በብዛት ገበያ ላይ አይገኙም ፤ ቢገኙም ዋጋቸው እጅግ የተጋነነ በመሆኑ በቀላሉ የሚቀመስ አይደለም።

የችግሩ ምንጭ ደግሞ ሰው ሰራሽ መሆኑ አይካድም።

ህጋዊ ነጋዴው በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እና ለደላላ እየተጠለፈ መስራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

በዚህ የተነሳ ' ልጆቼን የማበላቸው አጣሁ ' የሚሉ አዛውንቶች፣ ' ጋሽዬ ቁራሽ የዳቦ መግዣ ስጠኝ ራበኝ ' የሚሉ አንጀት የሚበሉ በርካታ ህጻናትን ማየት በከተማችን እየተለመደ መጥቷል።

ልመና አልነበረም ማለት አይደለም አሁን ግን እጅግ እየተባባሰ ሄዷል።

ደላላው ዋጋ ይተምናል ፤ ደላላው ዋጋ ይሰቅላል ቢፈልግም ያወርዳል ለዚህም አንድ ወቅት የሱዙኪ መኪና ዋጋን ሰማይ አድርሶ መሬት አስልሶት የነበረበትን አጋጣሚ ማስታወስ ይቻላል።

በአጭር አነጋገር ደላላ የንግዱን ስርዓት /ሲስተም እንደ ተባይ ወሮታል። በዚህም የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው።

ጥቅሙን የሚያገኘው  በጋ ከክረምት ደም ታፍቶ ያመረተው አርሶ አደሩ ቢሆን መልካም ነበር።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶ ህገወጥ ነጋዴዎች እና ደላላዎችን ስርዓት ሊያሲዝ የሚችል ዘላቂነት ያለው ስራ ከመስራት ይልቅ አልፎ አልፎ ወይም የሆነ አጋጣሚ ሲፈጠር ' ይሄን ያህል የንግድ ድርጅቶችን አሽኩ / ልናሽግ ነው ' እያሉ በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያዎችን ከማስተጋባት የዘለለ ፦
° የንግድ ተቋማቱ በምን ምክንያት እንደታሸጉ
° ምን አይነት ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው
° የማሸጉ እርምጃ ምን ውጤት እንዳስገኘ
° የንግድ ድርጅቶቹ ከታሸጉ በኃላ የመጣንው ለውጥ ለህዝቡ ሲያሳውቅ አይታይም።

በኑሮ ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አይስተዋልም።

ታዲያ የሀገራችንን ገበያ እየመራ ያለው ንግድ ሚኒስቴር ነው ወይስ ደላላና ህገወጥ ነጋዴ ?

2. ለንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ከሚቆጣጠራቸው ተቋማት አንዱ መብራት ኃይል ነው። (በየጊዜው የመዋቅር መቀያየር ለውጥ ካለ ይቅርታ ጠይቃለሁ!)

ይሁን እንጂ የመብራት ተደራሽነት እና አግልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ የተበላሸ ነው።

👉 ተደራሽነቱ ፍትሃዊነት የጎደለውና ለማዳረስ የተሞከረው ለረጅም አመታት የተተከሉ ፖሎች ሳይቀር ያለ አገልግሎት የቆሙበት፤

👉 ተዳረሰ የተባለውም በኃይል መቆራረጥ ችግር ተጠቃሚውን የሚያሰቃይ፤

👉 አገልግሎቱን ለማግኘት ያለ እፍረት በእጅ መንሻ / ጉባ ካልሆነ በቀር የማይሰራ ሰራተኛ የበዛበት ነው።

የሚያሳዝነው ደግሞ ጉቦ ወንጀል መሆኑ ቀርቶ መብት እስኪመስል ድረስ ዋጋ ተምነው ' ይህን ያህል አምጣ ' የሚሉ ሰራተኞች መብዛታቸው ነው።

በዚህ ከቀጠለ ምናልባትም ፓርላማውን ' የምቀበለው ጉቦ አንሶኛል እና ህግ አውጡልኝ ' ማለት የቀራቸው ይመስላል።

ይህ የእርሶን ተቋም ብቻ የሚመለከት አይደለም በርካታ ተቋማትን የሚያካትት ነው።

ክቡር ሚኒስትር ለመሆኑ ለእርሶ ተጠሪ የሆነው ባለስልጣን መ/ቤት ህዝቡን እያስለቀሰ የሚቀጥለው እስከመቼ ነው ? ይህንን ተቋም መቆጣጠርና ስርዓቱን ማስያዝ ያልተቻለው ለምንድነው ?

3. የኑሮ ውድነቱን ከሚያባብሱ ምክንያቶች አንዱ ነዳጅ ነው።

የዋጋው ማሻቀብ ምክንያቱ የሚታወቅ ቢሆንም ከዋጋው በላይ ሰልፉ ህዝቡን እያማረረ ይገኛል።

ከእጥረቱም በላይ ነዳጅ ለመቅዳት በሚደረግ ረጃጅም ሰልፍ ምክንያት የስራ ሰዓት ያለ አግባብ እየባከነ፣ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ፣ እንዲያውም ሲል በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ከሀገር እንዲወጣ ሰፊ በር እየከፈተ መሆኑን እማኝ መጥቀስ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።

ክቡር ሚኒስትር ይህንን የተበላሸ አሰራር ስርዓት ማስያዝ የማን ኃላፊነት ይመስሎታል ? እባክዎ ለዚህ የተከበረ ም/ቤት እና ለብዙሃኑ የሀገራችን ህዝብ ተገቢውን መልስ ይስጡ። "

ሚኒስትሩ ምን ምላሽ ሰጡ ? ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-03

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#TecnoAI

የስራዎች መደራረብ ህይወቶን ፕሮግራም አልባ አድርጎታል? በላቁ ቴክኖሎጂዎች የተዋቀረው አዲሱ ቴክኖ ኤ አይ ፕሮፌሽናል አጋዥ በመሆን ህይወቶን ለማቅለል እየመጣ ነው፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ በሆነው የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et