TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ምንድነው ያስተላለፈው ውሳኔ ?

💡" ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል ! "

🌃 " ዋና እና መጋቢ መንገድ ላይ የሚገኙ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል ! "

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

የተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

ከነዚህም አንዱ ፥ በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚል ነው።

ሌላኛው የምሽት ትራንስፖርትን ይመለከታል።

በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በመወያየት በመንግስት እና  የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ ተብሏል።

በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ተወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል።

በተጨማሪ ካቢኔው ፦

- የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ ስለሆነ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

- በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #AddisAbaba

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መቼ ይካሄዳል ?

38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት መጀመሪያ ሳምንት ይካሄዳል።

አዲስ አበባ የፊታችን የካቲት ወር መጀመሪያ ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ታስተናግዳለች።

ለዚህም ጉባኤ ሁሉን አቀፍ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባዔውን የኢትዮጵያን ገጽታና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነት በሚያሳድግ መልኩ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጣጥና የሆቴል ፋሲሊቲዎች መሰረት በማድረግ 42 ሆቴሎች እንግዶቹን እንዲያስተናገዱ መመረጣቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር መረጃ ያሳያል።

ሆቴሎቹ በሕብረቱ ጉባዔ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል።

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሁም 46ኛው የህብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። #ENA

Photo Credit - Addis Ababa Mayor Office

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የስምና ንብረት ዝውውር ታገደባቸው ክ/ከተሞች የትኞቹ ናቸው ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በ6 ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል ፤ " ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራው ነው " ብሏል።

" ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ ተጀምሯል ፤ አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ተሰርቷል " ብሏል።

በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እንደሚሰራ ፤ የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ 6 ክ/ከተሞች በቀጣይ 5 ወራት ውስጥ እንደሚከናወን
ጠቅሷል።

ክፍለ ከተሞቹ ፦
- የካ፣
- ለሚ ኩራ፣
- አቃቂ ቃሊቲ፣
- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣
- ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ እንደሆኑ አሳውቋል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክፍለ ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ ድረስ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱን ገልጿል።

ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።

@tikvahethiopia
" የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት አለበት " - ፕ/ር መረራ ጉዲና

ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን በአዲስ አበባ አስመርቋል።

የቀድሞ ሜክሲኮ የሚገኘው ዋና ፅ/ቤቱ በኮሪደር ልማት ምክንያት በመፍረሱ አዲሱን ቢሮ ቀበና አደባባይ አከባቢ ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።

በዚህ ወቅት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ንግግር ያደረጉ ሲሆን " አሁንም ሀገራችን ትልቅ ችግር ውስጥ ናት " ብለዋል።

የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበትም ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ወደጦርነት የሚመሩትን የፖለቲካ ችግሮች በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

" የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ፍላጎት ዘላቂ ሰላም ፣ ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓት እና በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው " ያሉ ሲሆን፤ " ይሄን ከግብ ለማድረስ ኦፌኮ'ን ጨምሮ ሌሎች የተቃዋሚ ፖርቲ ህብረቶች ትግላቸውን ማጠናከር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

በወቅቱ ተገኝተው የነበሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች " ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያላውን ችግር ለመፍታት ህብረታችንን በደንብ በማጠናከር እና ህዝቡን ከጎን በማሰለፍ አንድላይ መቀጠል ይኖርብናል " ብለዋል።

ኦፌኮ አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን ስራ ባስጀመረበት ወቅት " በአገሪቱ ውስጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣዩ ትግል አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል " ያለ ሲሆን " በዚህ መሠረት በጦርነቱ ጉዳት፣ በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የማህበራዊ መቃወስና ወደ መፍረስ እየተኬደ ካለው መንገድ ኢትዮጵያን ለመታደግ ትኩረት ይሰጣል " ብሏል።

#OFC #AddisAbaba

@tikvahethiopia
#BankOfAbysinia

ዘመናዊ ፖስ ማሽኖቻችን ባሉባቸው የግብይት ቦታዎች ሰልፍ አይታሰብም!

#POSMachine #contactless #DigitalPayments #CashlessTransactions
#BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#AddisAbaba #እንድታውቁት

የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት መንገዶች ይዘጋሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

➡️ ከ6 ኪሎ አደባባይ - ምኒልክ ሆስፒታል
➡️ ከምኒልክ ሆስፒታል - መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ
➡️ ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ - 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ
➡️ ከዋልያ ቢራ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከአቃቂ ዋናው መንገድ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከ08 - አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።

በተጨማሪ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በ11ዱም ክ/ከተሞች ጥምቀተ ባህር ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በ500 ሜትር  ክልል ውስጥ ታቦታት ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም በሚሄዱባቸው መንገዶች ለአጭር ጊዜም ይሁን ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአቢሲንያ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች የATM ካርድ በቆማችሁበት በሰከንዶች ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#AddisAbaba

" አባታችንን አፋልጉን ! "

አባታችን ገብረማርያም መለሰ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በኃላ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።

እድሜያቸው 85 ዓመት ሲሆን መጥፋታቸውን ለፖሊስ አመልክተናል።

በሰዓቱ ለብሰውት የነበረው ጥቁር ጃኬት ነበር። ከዘራም በእጃቸው ይዘዋል።

መጨረሻ ጊዜ የነበሩበት ቦታ ወሰን 02 አካባቢ ነው።

ቤተሰብ ተጨንቋል አባታችንን አፋልጉን፤ መረጃ ለመስጠት 0911452386 ላይ ደውሉልን። " - ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው

@tikvahethiopia
ብልህ ለራሱ ያውቃል ... በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ህይወትን ቀለል አድርጎ ይመራል።#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ