TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

“ አንዳች ነገር ኮሽ ባላለበት ከተማ ‘ቦምብ ፈነዳ፣ ሰዎች ሞቱ ፣ የፓሊስ አባላት ሞቱ ’ እየተባለ ስለሚወራው ወሬ ራሱ ነዋሪው ነው የሚታዘባቸው ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ ሰሚትና አያት አካባቢዎች የቦንብ ፍንዳታ ተከስቷል ” የሚሉ ወሬዎች ከትላንት ጀምሮ በX (ትዊተር) ላይ በስፋት ሲራወጡ ተስተውሏል።

ይህ መረጃ ዋና መነሻው የኢትዮጵያን ጉዳይ እየተከታተሉ ከሚፅፉ ገጾች ነው።

ጉዳዩን ግን በብዛት ሲያሰራጩት የተስተዋሉት ግብፃዊያን እና ሱማሊያዊያን ሲሆኑ፣ በቦምብ ፍንዳታው ሰዎች እደሞቱ ፣ የፓሊስ አባላት እንደተገደሉ ነው መረጃ ሲያሰራጩ የተስተዋሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በX (ቲዊተር) እየተራወጠ ያለውን መረጃ በተመለከተ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽንን መልዕክት እንዲያስተላልፍ ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ “ በከተማዋ ያለው ሰላም አስተማማኝ ነው ” ብዋል።

እንዲህ ያለ የሐሰተኛ መረጃ በሚነዙ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ በአንክሮ ገልጸዋል።

ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን አሉ ?

“ ማንም በዬጫት ቤቱ ቁጭ ብሎ የሚያወራውን የመንግስት ተቋም ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው።

ማኀበራዊ ድረ ገጹ እንደሚታውቀው ነው።

በጣም ጥቂት ድረገጾች ናቸው ትክክለኛና ታማኝ መረጃ የሚዘግቡት እንጂ በአብዛኛው የከተማው ሰላም መሆን የሚያስጨንቃቸውም ስለሆኑ ዓይናቸው ደም ይለብሳል።

እንደዚህ ተወለደ ፣ እንደዚህ ተፈጠረ እያሉ ያልተፈጠረ ነገር እያወሩ ሰው በሰላም ገብቶ እንዳይወጣ ሽብር የመንዛት ሀሳብ ነው ያላቸው።

የከተማው ሰላም አስማማኝ መሆኑን 24 ሰዓት የነዋሪውን እንቅስቃሴ በማዬት ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል። ምንም አይነት ጥናትም የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም። 

ከተማው 24 ሰዓት ክፍት ነው። አንዳች ነገር ኮሽ ባላለበት ከተማ ‘ቦምብ ፈነዳ፣ ሰዎች ሞቱ፣ የፓሊስ አባላት ሞቱ’ እየተባለ ስለሚወራው ወሬ ራሱ ነዋሪው ነው የሚታዘባቸው።

የተለመደ የበሬ ወለደ አይነት ወሬያቸው ነው። ዞሮ ዞሮ የከተማው ነዋሪ አሁን በጣም ገብቶታል። ለእነርሱ የሐሰት መረጃም ምንም ምላሽም አይሰጥም ትዝም አይለውም። መደበኛ ሥራውን ነው የሚምራው።

ከተማው አንዳችም የጸጥታ ችግር ያለበት ሁኔታ ላይ አይደለም። ሰላማዊ የሆነ እንቅስቃሴ ነው ያለው።

ምንም ነገር በሌለበት ሁኔታ እንደዚህ የሚሉ ግለሰቦችም ይሁኑ ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ነው መልዕክት ማስተላለፍ የምንፈልገው።

እንደ አዲስ አበባ ፓሊስ የከተማው የጸጥታ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው ነው። ኃላፊነትም ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰበት ያለ ጉዳይ ነው። እንደዚህ አይነት ሥራ በሚሰሩ ሰዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል።
”  ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በተለያዩ ቀናት ከሦስት ድርጅቶች ስልክና ላፕቶፕ ሲሰርቅ በካሜራ ዕይታ የገባው ግለሰብ በፖሊስ እየተፈለገ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ በቀናት ልዩነት በ 3 ድርጅቶች የላፕቶፕ እና የሞባይል ስልኮች ስርቆት በተመሳሳይ ግለሰብ መፈጸሙን ዝርፊያው የተፈጸመባቸው የንብረቱ ባለቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል ።

ግለሰቡ የስርቆት ድርጊቱን ፈጸመ የተባለው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት እና ሦስት እንዲሁም በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ መድኃኒአለም አቢሲኒያ ህንጻ አካባቢ ነው።

ለቲክቫህ ቃላቸውን የሰጡ ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ግለሰብ "ህዳር ዘጠኝ ስምንት ሰዓት ላይ ወሎ ሰፈር አካባቢ የሚገኝ ህንጻ ስድስተኛ ፎቅ ወደሚገኝ ቢሮአችን ነጭ ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ አድርጎ የገባ ግለሰብ ሪሰፕሽን ላይ ሰው አለመኖሩን በማረጋገጥ ላፕቶፕ ይዞ ተሰውሯል" ብለዋል።

ግለሰቡ የስርቆት ድርጊቱን ሲፈጽም በድርጅቱ በተገጠመ የደህንነት ካሜራ የተቀረጸ ሲሆን ላፕቶፑን በቲሸርቱ ውስጥ በመደበቅ ይዞ ሲወጣ ይታያል።

ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ግለሰብ ግለሰቡን የሚያውቀው ሰው ካለ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በደህንነት ካሜራ የተቀረጸውን ቪዲዮ ማጋራታቸውን ተናግረዋል።

መረጃውን በማህበራዊ ሚዲያ ካጋሩት በኋላ በቀናት ልዩነት እኛም በተመሳሳይ ሰው ተዘርፈናል የሚሉ ግለሰቦች እንዳነጋገሯቸው ገልጸውልናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ሌላኛውን ተበዳይ በማነጋገር ዝርፊያው መፈጸሙን አረጋግጧል።

ግለሰቡ ቦሌ መድኃኒአለም አካባቢ ወደሚገኝ ህንጻ በመግባት ስርቆቱን የፈጸመው ህዳር 9 ሰኞ የስርቆት ድርጊቱን ከፈጸመ ከአምስት ቀናት በኋላ ማለትም ህዳር 14 ቅዳሜ ቀን ሲሆን በዕለቱ ጥቁር ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ በመልበስ ስልኮቹን ሲያነሳ በተመሳሳይ በደህንነት ካሜራ እይታ ውስጥ ገብቷል።

በቀናት ልዩነት አንድ ላፕቶፕ እና ሁለት ስልኮችን ከሁለት የተለያዩ ድርጅቶች ሰርቆ የተሰወረው ይህ ግለሰብ ጻጉሜ 4/2016 ዓም ቂርቆስ ክፍለ ወረዳ ሁለት ፍላሚንጎ አካባቢ በተመሳሳይ ሰው የስርቆት ድርጊት ተፈጽሞብኛል ያሉ ግለሰብም ቃላቸው ለቲክቫህ ሰጥተዋል።

"ፍላሚንጎ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አካባቢ ወደሚገኝ ቢሮአችን በመግባት ላፕቶፕ በመስረቅ ተሰውሯል ለፖሊስ ብናመለክትም ስሙንም ሆነ አድራሻውን ማወቅ አልተቻለም" ሲሉ ነግረውናል።

ሶስቱም ግለሰቦች በተመሳሳይ ሰው መሰረቃቸውን ያወቁት ወሎ ሰፈር ከሚገኝ ቢሮአቸው ላፕቶፕ የተሰረቁት ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ምስሉን በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን ተከትሎ ነው።

የስርቆቱ ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች ውስጥ ሁለቱ የደህንነት ካሜራውን ምስሎች እና አስፈላጊውን መረጃዎች በመያዝ ለፖሊስ ቢያመለክቱም ግለሰቡ እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም።

ፖሊስ ምን አለ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን በመያዝ ጉዳዩን እየተከታተለ የሚገኘውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የመስቀል ፍላወር አከባቢ ፖሊስ ጣቢያ አነጋግሯል።

ፖሊስ "በእኛ በኩል ሰውዬውን ለመያዝ በክትትል ላይ ነው የምንገኘው እስካሁን ገና አልተያዘም ቦሌ እና ቂርቆስ ላይ ወንጀሉን ፈጽሟል በክትትል ላይ ነው ያለነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ግለሰቡን ያያቹ ወይም ያለበትን የምታውቁ ከታች በተቀመጡት ስልኮች በመጠቆም ትብብር እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ለጥቆማ፡ 0114621442, 0911115656

@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ምንድነው ያስተላለፈው ውሳኔ ?

💡" ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል ! "

🌃 " ዋና እና መጋቢ መንገድ ላይ የሚገኙ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል ! "

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

የተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

ከነዚህም አንዱ ፥ በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚል ነው።

ሌላኛው የምሽት ትራንስፖርትን ይመለከታል።

በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በመወያየት በመንግስት እና  የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ ተብሏል።

በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ተወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል።

በተጨማሪ ካቢኔው ፦

- የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ ስለሆነ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

- በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #AddisAbaba

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መቼ ይካሄዳል ?

38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት መጀመሪያ ሳምንት ይካሄዳል።

አዲስ አበባ የፊታችን የካቲት ወር መጀመሪያ ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ታስተናግዳለች።

ለዚህም ጉባኤ ሁሉን አቀፍ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባዔውን የኢትዮጵያን ገጽታና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነት በሚያሳድግ መልኩ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጣጥና የሆቴል ፋሲሊቲዎች መሰረት በማድረግ 42 ሆቴሎች እንግዶቹን እንዲያስተናገዱ መመረጣቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር መረጃ ያሳያል።

ሆቴሎቹ በሕብረቱ ጉባዔ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል።

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሁም 46ኛው የህብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። #ENA

Photo Credit - Addis Ababa Mayor Office

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የስምና ንብረት ዝውውር ታገደባቸው ክ/ከተሞች የትኞቹ ናቸው ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በ6 ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል ፤ " ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራው ነው " ብሏል።

" ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ ተጀምሯል ፤ አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ተሰርቷል " ብሏል።

በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እንደሚሰራ ፤ የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ 6 ክ/ከተሞች በቀጣይ 5 ወራት ውስጥ እንደሚከናወን
ጠቅሷል።

ክፍለ ከተሞቹ ፦
- የካ፣
- ለሚ ኩራ፣
- አቃቂ ቃሊቲ፣
- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣
- ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ እንደሆኑ አሳውቋል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክፍለ ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ ድረስ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱን ገልጿል።

ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።

@tikvahethiopia
" የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት አለበት " - ፕ/ር መረራ ጉዲና

ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን በአዲስ አበባ አስመርቋል።

የቀድሞ ሜክሲኮ የሚገኘው ዋና ፅ/ቤቱ በኮሪደር ልማት ምክንያት በመፍረሱ አዲሱን ቢሮ ቀበና አደባባይ አከባቢ ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።

በዚህ ወቅት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ንግግር ያደረጉ ሲሆን " አሁንም ሀገራችን ትልቅ ችግር ውስጥ ናት " ብለዋል።

የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበትም ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ወደጦርነት የሚመሩትን የፖለቲካ ችግሮች በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

" የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ፍላጎት ዘላቂ ሰላም ፣ ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓት እና በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው " ያሉ ሲሆን፤ " ይሄን ከግብ ለማድረስ ኦፌኮ'ን ጨምሮ ሌሎች የተቃዋሚ ፖርቲ ህብረቶች ትግላቸውን ማጠናከር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

በወቅቱ ተገኝተው የነበሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች " ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያላውን ችግር ለመፍታት ህብረታችንን በደንብ በማጠናከር እና ህዝቡን ከጎን በማሰለፍ አንድላይ መቀጠል ይኖርብናል " ብለዋል።

ኦፌኮ አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን ስራ ባስጀመረበት ወቅት " በአገሪቱ ውስጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣዩ ትግል አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል " ያለ ሲሆን " በዚህ መሠረት በጦርነቱ ጉዳት፣ በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የማህበራዊ መቃወስና ወደ መፍረስ እየተኬደ ካለው መንገድ ኢትዮጵያን ለመታደግ ትኩረት ይሰጣል " ብሏል።

#OFC #AddisAbaba

@tikvahethiopia
#BankOfAbysinia

ዘመናዊ ፖስ ማሽኖቻችን ባሉባቸው የግብይት ቦታዎች ሰልፍ አይታሰብም!

#POSMachine #contactless #DigitalPayments #CashlessTransactions
#BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#AddisAbaba #እንድታውቁት

የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት መንገዶች ይዘጋሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

➡️ ከ6 ኪሎ አደባባይ - ምኒልክ ሆስፒታል
➡️ ከምኒልክ ሆስፒታል - መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ
➡️ ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ - 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ
➡️ ከዋልያ ቢራ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከአቃቂ ዋናው መንገድ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
➡️ ከ08 - አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናሉ።

በተጨማሪ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በ11ዱም ክ/ከተሞች ጥምቀተ ባህር ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በ500 ሜትር  ክልል ውስጥ ታቦታት ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም በሚሄዱባቸው መንገዶች ለአጭር ጊዜም ይሁን ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአቢሲንያ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች የATM ካርድ በቆማችሁበት በሰከንዶች ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#AddisAbaba

" አባታችንን አፋልጉን ! "

አባታችን ገብረማርያም መለሰ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በኃላ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።

እድሜያቸው 85 ዓመት ሲሆን መጥፋታቸውን ለፖሊስ አመልክተናል።

በሰዓቱ ለብሰውት የነበረው ጥቁር ጃኬት ነበር። ከዘራም በእጃቸው ይዘዋል።

መጨረሻ ጊዜ የነበሩበት ቦታ ወሰን 02 አካባቢ ነው።

ቤተሰብ ተጨንቋል አባታችንን አፋልጉን፤ መረጃ ለመስጠት 0911452386 ላይ ደውሉልን። " - ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው

@tikvahethiopia
ብልህ ለራሱ ያውቃል ... በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ህይወትን ቀለል አድርጎ ይመራል።#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ በሚከናወነው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎች ምክንያት ከነገ ማለትም ረቡዕ የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ ማለትም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ድረስ :-

1. አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ ፤

2. ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል፤

3. በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር መዘዋወራቸውን እና ስብሰባዎቹ እንደተጠናቀቁ ወደ ቀድሞ ቦታዎቻቸው እንደሚመለሰ የአዲስ አባባ ከተማ አስታዳደር አሳውቋል።

#AU #ADDISABABA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የኢትዮጵያ እና አፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ እንግዶቿን እየተቀበለች ትገኛለች።

በርካታ እንግዶች ለ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።

ዛሬ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንዲሁም የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ አበባ ገብተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #ADDISABABA

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታውቋል።

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር-ኃይሉ "  የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት የበለጠ በማጠናከር የኅብረተሰቡ እንቅስቃሴ ሳይገታ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ በማድረግ በቅንጅት በመሥራቱ ጉባኤው በስኬት ተጠናቋል " ሲል ገልጿል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " የህብረቱ ጉባኤ ለከተማችን ድምቀትና የኢኮኖሚ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የቱሪዝም መስህቦችን እና የከተማችንን መልካም ገጽታዎችን እንዲሁም የህዝባችንን ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል " ብለዋል።

" ጉባኤው እጅግ ደማቅ እና ከወትሮው የተለየ ሁኔታ የተካሄደ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

እንግዶች ወደየሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ እግዱ እንዲሰጥ መደረጉ ተገቢነት ስለሌለው እግዱ ሊነሳ ይገባል ”- እናት ፓርቲ ይግባኝ ባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ያሰራጨው የቤት ግብር ግምት ማሻሻያ የጥናት ሰነድን በተመለከተ ያቀረበው የእግድ ማመልከቻ እንዲነሳለት እናት ፓርቲ ጠየቀ። ቢሮው፣ “ከሕግ ውጪ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ለከተማው የግብር ሰብሳቢ አካላት የበተነው” ሰነድ ከፍተኛ ግብር የሚጥል፣ የቤት ግብር…
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ ስልጣን ያለው መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ያለው ሲሆን፣ ይህን ግብር ከመሰብሰብ የሚከለክል ምንም አይነት ህጋዊ አካል እንደሌለ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እየተካሄደ ባለበት ወቅት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው።

ከንቲባዋ የጣራና የግድግዳ ግብርን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ የጣራና የግድግዳ ግብር አዋጅ በ1968 ዓ.ም የወጣ አዋጅ መሆኑን አስታውሰዋል።

በወቅቱ የነበረው አሰራር አሁንም እንደቀጠለ ነው ያሉት ከንቲባዋ፣ ነገር ግን የተለወጠው ወቅቱን ያገናዘበ የዋጋ ተመን ብቻ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም አዋጁ ሲወጣ የነበረው የኪራይ ዋጋ እና አሁን ያለው የኪራይ ዋጋ እኩል ባለመሆኑ አሁን የጨመረው ኪራዩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የሚያስከፍለው ግብር ግን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን ለመኖሪያ ቤት የዋጋውን ግማሽ እንዲሁም ለንግድ ቤቶች 75 በመቶ ብቻ እንደሆነ ከንቲባዋ አብራርተዋል።

በከተማዋ በግብር ስርዓት ውስጥ ያልነበሩ በርካታ ነዋሪዎች እንደነበሩ ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች፣ በከተማዋ ካሉ 800 ሺህ ህንጻዎችና ቤቶች ግብር ይከፍሉ የነበሩት 120 ሺህ ብቻ እንደነበሩ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia