TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" በምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ነው ከፅህፈት ቤቱ ያወጣው " - በድብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት መግለጫ አውጥቷል። ደርጅቱ በመግለጫው ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረው የፕሬዜዳንት ውክልና አንስቶ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንዲሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተወያየበት እንደሚገኝ…
#Tigray

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል።

በውይይቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዛዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር።

ከነሱ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ነበሩ።

ምንም እንኳን የውይይቱ ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

በውይይቱ በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራትና የክልሉ ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

በተለይ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታና ታጣቂዎችን ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ሂደት በትኩረት የሚሰራበት እና የሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

በተጨማሪ በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ህጋዊ  በሆነ አግባብ የህዝብንና የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግስት አገልግሎቶች የሚሻሻሉበትና የህዝብን ፍላጎት የሚመጥኑ እንዲሆኑ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በዚሁ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ላይ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ክልላዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ያለበትን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ወደየት እያመራ ነው ? በሚል ብዙዎችን ማስጋቱ ይታወቃል።

በተለይ ሰሞኑን በአቶ ጌታቸው እና በደብረጾን (ዶ/ር) ቡድኖች መካከል ጠንከር ያሉ የመግለጫና የሚዲያ ምልልሶች ሲደረጉ ሰንብተዋል።

ከመግለጫና የሚዲያ ምልልስ ባለፈ በደብረፅዮ ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በምክር ቤት አማካኝነት የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሹመኞች በማንሳት የራሱን ሲሾም በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ በደብረጽዮን በሚመራው ቡድን የሚሾሙ ሹመኞችን በማንሳት የራሱን አመራሮች ሲመድብ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል። በውይይቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዛዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር። ከነሱ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ነበሩ። ምንም እንኳን የውይይቱ ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት…
#Tigray

በመቐለ ማንኛውም ሰላማዊ ስልፍ እንዳይካሄደ ተከለከለ ፤ ክልከካው አስከ መቼ እንደሚቀጥል የተገለፀ ነገር የለም።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በመቐለ ከተማ ተደረግብኝ ላለው የከንቲባ መፈንቅለ ስልጣን " ሰላማዊ ስልፍ እንዳካሂድ ይፈቀድልኝ " ሲል በመቐለ የህወሓት ፅህፈት ቤት በኩል ህዳር 25/2017 ዓ.ም ለመቐለ ከተማ አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።

ሰልፉን እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6:30 ለማድረግ ነበር የጠየቀው።

ድርጅቱ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሂድ በጠየቀበት ደብዳቤው ፤ " ህዳር 23/2017 ዓ.ም የተፈፀመው በመሳሪያ የተደገፈ የመቐለ ከተማ መደበኛ አስተዳደር  መፈንቅለ ስልጣን ለማውገዝ " ነው ብሏል።

በተጨማሪም ፥ " ለዘመናት በከፈልነው መስዋእት ያፀናነው መብታችን እና የመሰረትነው ምክር ቤት በአዲስ ገዢ ግለሰቦች አምባገነንነት ሲፈርስ አንታገስም " ሲል ገልጿል።

ደንረጽዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ቡድን "  ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናካሂድ በተደጋጋሚ ከአባሎቻችን በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ፤ እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 አስከ ቀኑ 6:30 ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናካሂድ ቅድመ ዝግጅት ስላጠናቀቅን ፍቃድ እንዲሰጠን እና የፀጥታ ጥበቃ እንዲደረግልን እንጠይቃለን " ሲል ነው በደብዳቤው የገለጸው።

ለመቐለ ህወሓት ፅህፈት ቤት ደብዳቤ ዛሬ አርብ ህዳር 27 /2017 ዓ.ም ምላሽ የሰጠው የመቐለ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የከተማው ጥምር ኮሚቴ በሰጠው መምሪያ መሰረት በመቐለ ከተማ ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ #ተከልክለዋል ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል። በውይይቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዛዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር። ከነሱ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ነበሩ። ምንም እንኳን የውይይቱ ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት…
#Tigray

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " በትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክህደት የፈፀመ ቡድን " ሲል ፈረጀ።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " ብሄራዊ ክህደት ፈፅሟል " ሲል የፈረጀው ማእከላዊ ኮሚቴ " ቡድኑ ከአፍራሽ ተግባሩ እንዲቆጠብ " መላው የትግራይ ህዝብ እና አባላት እንዲታገሉት ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " የትግራይ ህዝብ መብት እና ራስን በራስ የማስተዳደር መገለጫ የሆኑት ምክር ቤቶች እንዲፈርሱ ለፌደራል መንግስት ጠይቀዋል " ሲል ገልፀዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ካካሄደው ውይይት መልስ ባወጣው መግለጫው ነው ይህን ጠንከር ያለ ፍረጃ ያቀረበው።

በተጨማሪ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ሳይረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የትግራይ ሰራዊት በዲሞብላይዜሽን (DDR) ምክንያት በችኮላ እንዲሰናበቱ እያደረገ ነው ብሏል።

በትግራይ በኩል የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚን ጥያቄ ውስጥ በሚከት መልኩ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ባለቤት ማን እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲወስን " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ጠይቀዋል ሲልም አክሏል።

በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እየተካሄደ ነው ከሚባለው ህገ ወጥ የወርቅ ማእድን ማውጣት እና ማዘዋወር ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያን በትግራይ ክልል ከኤርትራ በሚያዋስኑዋት አከባቢዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሰፍር በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ለፌደራል መንግስት ጥያቄ እንዳቀረበም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ገልጿል።

እስካሁን በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " በትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክህደት የፈፀመ ቡድን " ሲል ፈረጀ። በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " ብሄራዊ ክህደት ፈፅሟል " ሲል የፈረጀው ማእከላዊ ኮሚቴ " ቡድኑ ከአፍራሽ ተግባሩ እንዲቆጠብ " መላው የትግራይ ህዝብ እና አባላት እንዲታገሉት…
#Tigray

" ከፌደራል መንግስት ስልጣን እንዲቸረው የሚለምን አማፂ እና ቂመኛ ቡድን ሌሎችን በባንዳነትና እና በክህደት ለመፈረጅ መድፈሩ አስደማሚ ነው " - በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት

ለሁለት በተከፈሉት የህወሓት አመራሮች መካከል ያለው የመግለጫ ምልልስ አሁንም ቀጥሏል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ፤ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም ላወጣው መግለጫ መልስ ሰጥቷል።

በዚህም በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት " አማፂ እና ቂመኛ " ሲል ፈርጆታል። 

" በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ጊዚያዊ አስተዳደር ቃሉን አጥፈዋል በአጭር ጊዜ ልኩ ለማስገባት በማካሂደው ትግል ህዝቡ ከጎኔ ይቁም የሚል የሚያስደምም መግለጫ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም በመገናኛ ብዙሃን አሰራጭቷል " ሲል የአቶ ጌታቸው ቡድን ከሷል።

" አማፂ እና ቂመኛ ቡድን " በመባል የተገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " የፌደራል መንግስት የጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት በሁለት ሳምንት እንዲነሳ ቀጠሮ ተሰጥቶኛል " ሲል እንዳልቆየ " ጊዚያዊ አስተዳደሩን በአጭር ጊዜ መልክ ለማስያዝ ወሰኜ ቃል ገብቻለሁ ተከተሉኝ " የሚል የክተት ጥሪ አቅርቧል ሲል በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት ገልጿል።

" የዚህ አማፂ እና ቂመኛ ቡድኑ አካሄድ ለህዝብ አዲስ አይፈለም " ያለው መግለጫው  " ቡድኑ ከፌደራል መንግስት የሚነጋገረው እና የሚስማማው ሌላ ለትግራይ ህዝብ የሚለው ደግሞ ሌላ " ሲል ገልፆታል።

" ከፌደራል መንግስት ስልጣን  እንዲቸረው የሚለምን አማፂ እና ቂመኛ ቡድን ሌሎችን በባንዳነትና እና በክህደት ለመፈረጅ መድፈሩ አስደማሚ ነው " ሲል  በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ገልጿል።

" አማፂ እና ቂመኛ ቡድኑ የትግራይን ህዝብ ከፌደራል መንግስት የሚያጋጭ አቅጣጫ እየተከተለ መሆኑ ያወጣው መግለጫ አመላካች ነው " ሲል አክሏል።

የደብረጽዮን (ዶ/ር) ቡድን ህዝቡ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ እንዲያምፅ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው በሚል ተከሷል።

ከፌደራል መንግስት በድብቅ " የውጭ ሽምጋይ ሳያስፈልገን ጉዳያችን ብቻችን መጨረስ እንችላለን " በማለት ስልጣን ይለምናልም ተብሏል።

" ቡድኑ ከስልጣን ውጪ የትግራይ ህዝብ ጉዳይ እንደ ጉዳዩ የማይቆጥር ራስ ወዳድ " ሲል አቶ ጌታቸው የሚመሩት ህወሓት አብጠልጥሎታል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ " ለስልጣን ሲል ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዳይመለሱ የመከልከል እና የማደናቀፍ ስራውን ቀጥሎበታል ፣ ዴሞብላይዜሽን (DDR) እንዲደናቀፍ ሴራዎች እየሸረበ ነው " ሲል ከሷል።

" አማፂ እና ቂመኛ ቡድኑ ቃሉ እና ተግባሩ ለየቅል ናቸው ፤ የህዝብ ችግር እና መከራ እንዳይፈታ በማወሳሰብ እንደ ምክንያት ተጠቅሞ ህዝብን እና መንግስት በማቃቃር በአመፅ ስልጣን ላይ ለመቆየት  ሙጥኝ ያለ ፀረ ህዝብ ነው " ሲል  ፈርጆታል።

የትግራይ ህዝብ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጡት አስተዳደራዊ ፣ ፓለቲካዊ ተልእኮዎች በተሰጠው ጊዜ አጠናቅቆ በህዝብ የተመረጠ መደበኛ መንግስት እንዲኖር የሚደረገው ትግል በመደገፍ  " አማፂ እና ቂመኛ " ሲል የጠራውን የነ ደብረጽዮን (ዶ/ር) ቢድን " የሚያካሂደውን አፍራሽ ተግባር በፅኑ እንዲቃወመውና እንዲያመክነው ጥሪውን አቅርቧል።

ከትላትና በስቲያ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " በትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክህደት የፈፀመ ቡድን " ሲል መፈረጁ ይታወሳል።

አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በተገኙበት ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የመሩት ውይይት ቢደረግም ወደ መቐለ ከተመለሱ በኃላ ጠንከር ባሉ መግለጫዎች አንድ ሁለት እየተባባሉ ነው።

የመግለጫዎቹ ይዘት ጠንካራ ከመሆናቸው አልፎ እየተወረወሩ ያሉት ቃላት ነገሩ ከመርገብ ይልቅ እየተካረረ እየሄደ እንዳለ ማሳያ ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray : በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የራሱን ምክር ቤት አቋቁሟል።

" የሃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን " ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን የህወሓት ቡድን በፅኑ ለመታገል ቆርጦ እንደተነሳ ገልጿል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት እስከ ቀጣዩ 14ኛው የደርጅቱ መደበኛ ጉባኤ የሚቆዩ ሊቀመንበር እና ምክትል ያቀፈ 7 አባላት ባሉት አስተባባሪ ኮሚቴ የሚመራ ም/ቤት አቋቁሟል።

የደርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር ማን አድርጎ እንደሰየመ ያልገለፀው መግለጫው  ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው የቀጣይ 3 ወራት እቅድ ማዘጋጀቱ አስታውቋል።

ደርጅቱ 14 ኛ ጉባኤውን መቼ እንደሚያካሂድ ያልገለፀ ሲሆን የተመሰረተው ምክር ቤት አባላት ሁሉም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው ህወሓት " አንሰለፍም " ብለው የተቆራረጡ ናቸው።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት በከተማና ገጠር ከክልል ፣ ዞን ፣ ወረዳ እና እስከ ቀበሌ ድረስ አደራጃጀቶች በመዘርጋት " የኃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን " ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት በፅኑ ለመታገል ቆርጦ መነሳቱ ገልጿል።

መላው የትግራይ ህዝብ ፣ የህወሓት አባላት ፣ የፀጥታ ሃይሎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ በተለይ ወጣቶች ፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የዳያስፓራ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲሰለፉ ጥሪ ያቀረበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " በሰላማዊ ትግል የትግራይን ህዝብ ጥቅም ለማስክበር እታገላለሁ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከድምጺ ወያነ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፤ የትግራይ አመራሮች በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐበይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳይ በነበራቸው ቆይታ በክልሉ ጉዳይ የሃሳብ ልዩነት አልነበራቸውም ብለዋል፡፡

ነገር ግን " የትግራይ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆነው የህዝቡ ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡

በአዲስ አበባው ውይይት በደብረፅዮን (ዶ/ር) ይሁን በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ልኡካን እንዲሁም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተወካዮች መካከል በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮች ዙሪካ ያለልዩነት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በወቅቱ " የፌደራል መንግሰት የትግራይ ችግሮች እንዲፈቱ አላገዝክም " በማለት ወቀሳ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።

" የፌደራል መንግስት ' ጉባኤ እንድናካሂድ ፤ የትግራይ ፓለቲካ እንድናስተካክል ጊዜ ስጠን በማለት ዕድል እና ጊዚያችሁን አባክናቹሃል ' በማለት መልሶልናል " ሲሉ አብራርተዋል።

ሌተናል ጄነራሉ ፥ " በመሃከላችን እየታየ ያለው ክፉኛ መሳሳብ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዳይረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዳይመለሱ አደገኛ መሰናክል ሆኗል " ብለዋል።

የፕሪቶሪያ ውል በይፋ የተቃወመ የለም ፤ በተግባር ግን ውሉን የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተግባር የሚፈፀሙ አካላት አሉ ብለዋል።

" የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመተግበር ብቻ ነው አቃፊ መንግስት ማቋቋም የሚቻለው " በማለትም አስረግጠዋል።

" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት ዓለምአቀፋዊ ወሰኖች የመጠበቅ እና የማስከበር ስልጣን አለው፤ ይህንኑ ስልጣኑ ተጠቅሞ በቦታው የሚገኙ የውጭ ሃይሎች አውጥቶ የግዛት አንድነት እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት ጠይቀናል " ብለዋል።

በዚህ ምክንያት " ' ከሃዲዎች ' በሚል ስማችንን ማጠልሸት ተገቢ አይደለም " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በፌደራል መ/ቤቶች የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ ምክንያት የህዝቡ ድምፅ በተገቢው መንገድ ሊሰማ ባለመቻሉ ምክንያት ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ውክልና እንዲመለስ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ መቅረቡን  ሌተናል ጀነራሉ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል አንቀፅ 8 ዓለምቀፍ ወሰኖች በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ስለሚያዝ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ እና ከሱዳን የሚያገናኙ ወሰኖች ጠባቂ ስለሌላቸው የውጭ ሃይሎች እየገቡ ግፎች እየፈፀሙ ፣ ወርቅ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ወንጀሎች እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ወሰኖቹ በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ " ሲሉ መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።

#Tigray #TPLF

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ሚመራው የህወሓት ቡድን በቀጣይ " አዲስ እና ሰላማዊ የትግል ስልት እከተላለሁ " ብሏል።

ቡድኑ በቀጣይ አጠቃላይ አባላቶቹ በመጠቀም " የእምቢተኝነት ዘመቻ " ያለውን እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዳቀደ ተነግሯል።

ለዚህ ዘመቻ " እምቢ ለብሔራዊ ክህደት፣ ለአገዛዝ እና ብተና " የሚል መፈክር እንደሰጠው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ትላንት እና እና ዛሬ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ከፍተኛ ካድሬዎቹ ስብሰባ ተቀምጠው ነው የዋሉት።

@tikvahethiopia
#Tigray

በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ እና ዝውውር ዙሪያ መረጃዎች በማሰባሰብ ላይ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በታጣቂዎች መታገታቸውን ተቋሙ አስታወቀ።

የታገቱት ጋዜጠኞች ብዛት 3 እንደሆነ የገለፀው የሚድያ ተቋሙ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል። 

ትግራይ ቴሌቪዥን " በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት የተሰማሩ ጋዜጠኞች ናቸው በታጣቂዎች የታገቱት " ሲል አሳውቋል።

ሦስት አባላት የያዘ የጋዜጠኞች ቡድን ዛሬ ታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 ጀምሮ በአስገዳ ወረዳ ' ሜይሊ ' ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ በምትገኘው መንደር ነው የታገቱት ተብሏል።

ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ስላለው ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር በማስመልከት በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ የአከባቢውን ነዋሪዎች ፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሲያነጋግሩ እንደሰነበቱ የገለፀው የትግራይ ቴሌቪዥን " የጋዜጠኞች ቡድኑ በስራ እያለ በታጣቂዎች ሊታገት እና ሊታሰር ችሏል " ሲል አመልክቷል።

የታገቱት የጋዜጠኞች ቡድን ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ በመደረጉ ምክንያት ያሉበት ሁኔታ እና ድህንነታቸው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አመልክቷል።

ጋዜጠኞቹን የሚመለከት መረጃ ለመጠይቅ በአከባቢው ለሚገኙ የመንግስት አመራሮች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም እንዳልተሳከለት የትግራይ ቴሌቪዥን አሳውቋል።

እገታውን ስለፈጸሙ ታጣቂዎች ማንነት በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትግራይ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቃዎች ታግተዋል " የተባሉት  3 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ከደቂቃዎች በፊት ማረጋገጡ ይታወሳል። አሁን ከስፍራው በተገኘው መረጃ ሦስቱ ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀዋል። የጋዜጠኞቹ መፈታት በማስመልከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ጋዜጠኞቹ መረጃ…
#Tigray

የትግራይ የፀጥታና የሰላም ቢሮ " ትግራይ ቴሌቪዥን " ይቅርታ ይጠይቅ አለ።

ቢሮው ይህን ያለድ ለአንድ ቀን ያህል በእገታና አስር ቆይተው ተለቀቁ በተባሉት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ባለሙያዎች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ነው።

የቢሮው መግለጫ የሚድያ ባለሙያዎቹ እገታ እና እስር አስመልክቶ የተሰራጨውን መረጃ የሚቃወም እንድምታ አለው። 

ተስፋዝጊ ዓስበይ ፣ ኢሳያስ በየነ እና ኣታኽልቲ የተባሉ የትግራይ ቴሌቪዥን የሚድያ ባለሙያዎች  ታግተውበታል ወደ ተባለው ቦታ መሄዳቸው የወረዳ ፣ የቀበሌ እና የመንደር አመራሮች መረጃ አልነበራቸውም ብሏል።

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ' ታግተናል ታስረናል ' ማለታቸው ልክ እንዳልሆነ አመላክቷል።  

" ጋዜጠኞቹ ወደ ቦታው እንዲንቀሳቀሱ የቀበሌ እና የመንደር አመራሮች መረጃ እንዲኖራቸው የግድ ነው ወይ ? " የሚል ጥያቄን ግን የቢሮው መግለጫ አለመለሰም።

" ሊበሉዋት የፈለጓትን አሞራ  ቆቅ ናት ይሉዋታል " ብሎ የተረተው የሰላምና የፀጥታ ቢሮ መግለጫ ፤ ተገቢ ማጣራት ሳይደረግ የሚድያ ባለሙያዎቹ ' ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ታግተዋል ፤ ታፍነዋል ' ተብሎ  የተሰራጨው መረጃ መስተካከል እና የትግራይ ቴሌቪዥን ይቅርታ ሊጠየቅበት እንደሚገባ አስገንዝቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጠኞች እና የሚድያ ባለሙያዎች የሙያ ነፃነታቸው ተከብሮ በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ ተዘዋውረው መረጃ በማሰባሰብ ለህዝብ የማድረስ መብት እንዳላቸው የገለጸው የትግራይ ጋዜጠኞች ማህበር ፤ በትግራይ ቴሌቪዥን የሚድያ ባለሙያዎች ላይ የተደረገው ወከባ አፈና ፣ እስር እና እንግልት በፅኑ ኮንነዋል።

ጋዜጠኞቹ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ለህዝብ እና ለአገር መረጃ ለማቅረብ ሲንቀሳቀሱ ተገቢ የፀጥታ ጥብቃ ሊድረግላቸው እንደሚገባ ያሳሰበው የማህበሩ መግለጫ ፤ ህግ እና ስርዓት አክብረው ተገቢ የሙያ ተግባራቸው በሚከውኑ የሚድያ ባለሙያዎች ላይ የሚድረግ ማንኛውም ዓይነት አፈና ፣ በደል ፣ ክልከላ እና ወከባ በጥብቅ እንቃወማለን ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል። ምርጫ ቦርድ ፤ ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን አስታውሷል። ፖርቲው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ…
#TPLF #Tigray

ለሁለት ቡድን የተከፈሉት የህወሓት አመራሮች አሸናፊ እና ተሸናፊ በሌለበት የፓለቲካ ችግሮቻቸውን ለመፍታት የተደረገው ተደጋጋሚ ድርድር አልተሳካም አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር።

ሁለቱ ቡድኖች ፓለቲካዊ ልዩነታቸው እንዲፈታ ከመጣር ይልቅ ፤ አንዱ ሌላውን ጠርጎ ለማጥፋት በሚል እሳቤ መጠመዳቸው ለድርድሩ አለማሳካት አንዱ እና ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሏል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

- የፓለቲካ ልዩነቱ ዋና መነሻ ከፍተኛ አመራሩ በመሆኑ ችግሩ በድርድር እንዲፈታ ጥረት የተደረገው በከፍተኛ አመራሩ ነው ብለዋል።

- የክልሉ የፀጥታ ሃይል ጨምሮ ሌሎች አካላት " ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ችግሮቻቸው ፓለቲካዊ ነው መፈታት ያለበትም በፓለቲካዊ መግባባት ነው " በሚል ለማደራደር በርካታ ጥረት ተደርጓል።

- በሁለቱ ቡድኖች መካከል የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት አሁን የተፈጠረ ሳይሆን በወቅቱ ሳይፈታ ለዓመታት እየተከማቸ የመጣ መሆኑ ቡድኖቹ ለማቀራረብ አዳጋች አድርጎታል።

- በሁለቱን ቡድኖች ያለው ፓለቲካዊ መሳሳብ  አሁንም ፓለቲካዊ መፍትሄ ያሻዋል። የፀጥታ ሃይሉ  " የኛ ደጋፊ ነው " የሚል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚናገረው ተቀባይነት የለውም።

- የፀጥታ ሃይሉ የክልሉ እና የህዝቡ ፀጥታ እና ሰላም ከማስከበር ባለፈ አንዱን ቡድን በመደገፍ ሊቆም አይችልም። ህዝቡ ሁለቱ ቡድኖቹ ችግራቸው በጠረጴዛ ውይይት እንዲፈቱ ጫናውን ማሳደር ይጠበቅበታል።

- የፀጥታ ሃይሉ የአንዱ ደጋፊ ለማሰመሰል የሚደረግ ጥላሸት የመቀባት ተግባር ልክ አይደለም። ይህን መሰል በሬ ወለደ ውሸት የሚያራግቡ አካላትም ሆነ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባቸዋለን።

መረጃውን የትግራይ የመገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia