TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

" በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር ነው " - ኢትዮጵያ

ትላንት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዶሎ በተባለ የጁባላንድ ከተማ " በፌዴራሉ የሶማሊያ ጦር ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ፤ በዚህ የሰው ሞት፣ ቁስለት ደርሷል " የሚል ክስ አሰምቷል።

ይህ መግለጫ እና በተፈጠረው ክስተት የኢትዮጵያ ኃይሎችን መክሰሱ ኢትዮጵያ አስቆጥቷል።

ክሱ ሀሰተኛ እንደሆነ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ " ሀሰተኛ ውንጀላው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታለመ ነው " ብሏል።

" ይህ የአፍሪካ ቀንድን ሰላም ለመበጥበጥ የሚፈልጉ እና በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር ነው " ሲል ገልጿል።

" በአንካራው ስምምነት ላይ እንደተገለጸው ሁለቱ ሀገራት ለሰላም የሚያደርጉት ቁርጠኝነት እንዳይደናቀፍ ክፍተት መፍጠር የለባቸውም " ሲል አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደሚቀጥልም አሳውዋል።

ኢትዮጵያ በአንካራ ስምምነት መሰረት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማደስ እና ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ከሰሞኑን በኢትዮጵያ የዘር ፍሬ ልገሳ ማከናወንን የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ " የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ " ይሰኛል። አስራ ሁለት ክፍሎች ያሉት ረቂቅ አዋጁ ፦ - ስለ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣ - ስለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ - ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች፤ - ስለ…
#ኢትዮጵያ

ሰሞኑን በፓርላማ የፀደቀው የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ?

➡️ የዘር ፍሬ በመለገስ ልጅ መውለድ እንዲቻል ለመፍቀድ ቀርቦ የነበረው የአዋጅ ድንጋጌ የለበትም።

➡️ በመሣሪያ ላይ የተመሠረተ አተነፋፈስ ማቋረጥ ተፈቅዷል።


" የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ " ለ3 ወር ያህል ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ ከቀናት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ9 ድመጸ ተአቅቦ ፣ 1 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።

የዘር ፍሬን በመለገስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ልጅ መውለድ እንዲቻል እንዲፈቅድ በረቂቅ ሕጉ ተካቶ የነበረው አንቀጽ እንዲወጣ ተደርጓል።

ለጤና፣ ማኅበራዊና ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ ውይይት ሲደረግበት በነበረው ረቂቅ አዋጅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት የሚፈቅደው ድንጋጌ እንዲወጣ ተጠይቆ ነበር።

ድንጋጌው እንዲወጣ ያደረገው " ልጅ እንዲኖረው የፈለገ ምን ይሁን ? " ለሚለው ጥያቄ፣ የጉዲፈቻ ልጅ በበቂ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ተነጋግሮበት በመወሰኑ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" ድንጋጌው ከረቂቁ እንዲወጣ የተደረገው ወላጆች ልጅ ለመውለድ ያላቸውን ፍላጎት ሳይሆን፣ ሕግ አውጪው የሚወለዱ ልጆች የማኅበረሰብ ቀውስ እዳያጋጥማቸው በማሰብ፣ ከእምነትና ከማኅበረሰብ መስተጋብር ጋር የተጣጣመ ሕግ መውጣት እንዳለበት ታስቦ ነው።

በተጨማሪም ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጭ ድንጋጌ ማውጣት ስለማይፈቀድ ነው።

ለተጋቢ ባለትዳሮች ፍላጎት ሲባል ይህ ሕግ ወጥቶ የሚወለደውን ሕፃን መብት መጋፋት አያስፈልግም።

ይሁን እንጂ የፀደቀው ሕግ በጋብቻ የተጣመሩ ባለትዳሮች ያለ ልገሳ የራሳቸውን የዘር ፍሬ ብቻ በመውሰድ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዷል " ብለዋል።

ለፓርላማ ቀርቦ የነበረው ረቂቅ ሕግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ በሕጋዊ ጋብቻ የተጣመሩ ወይም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ የማይችሉ መሆናቸው በዘርፉ ባለሙያ ሲረጋገጥ እንደሆነ ይል ነበር፡፡

የምክር ቤት አባላት የዘር ፍሬን በሕጉ ከተፈቀደው ውጪ አሳልፎ የሰጠ አካል ከተገኘ በወንጀል ሕግ ተጠያቂ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአዋጁ አንቀጽ 14 በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ድንጋጌ ተቀምጧል፡፡

በዚህ ድንጋጌ በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓትን ማቋረጥ የሚቻለው፣ የልብና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

አፈጻጸሙ አግባብነት ባላቸው ሶስት ባለሙያዎች ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል። ሚኒስቴሩ " የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን…
#ነዳጅ

ቤንዚን በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል።

ዛሬ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መወሰኑን አሳውቋል።

በዚሁ መሰረት ፦

አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር

አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር

አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር

የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር

አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።

#ነዳጅ #ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ሀገራዊ የጾም ፀሎት ጥሪ ከመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን !

መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 15 ድረስ የሚዘልቅ ሀገራዊ የጾም ፀሎት አውጃለች።

ቤተክርስቲያኗ በልመና / ምልጃ ጸሎት ወቅት ፦

➡️ " በሀገሪቱ በተለያዩ ሥፍራዎች ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች በኃላፊነት መንፈስ በጋራ ለሀገር እና ለህዝብ በአንድነት መስራት የሚችሉበትን ጥበብ፤ እውቀትና ማስተዋል እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው እንለምን። "

➡️ " በሀገራችን በሚገኙት የኦሮሚያ፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ያለው አፍተኛ የጸጥታ ችግር ጌታ እንዲያቆመው እንጸልይ። "

➡️ " በምድሪቱ ላይ ፍትህ እንዲሰፍን እንዲሁም በተለያዩ የሥልጣን ደረጃዎች ያሉ የመንግስት አካላት ሕዝቡን በከፍተኛ ኃላፊነት፤ አክብሮትና ቅንነት ማገልገል የሚችሉበትን ጥበብ፣ ማስተዋልና የልብ ስፋት እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው እንለምን። "

➡️ " የሀገራችን ኢኮኖሚ ስርዐት ድሃው ማህበረሰብ ሰርቶና በልቶ እንዲያድር ፍትሐዊ እንዲሆን እንጸልይ፡፡ "

... ብላለች።

(የቤተክርስቲያኒቱ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ ቤንዚን በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል። ዛሬ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መወሰኑን አሳውቋል። በዚሁ መሰረት ፦ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር…
#ነዳጅ

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።


አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር

አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር

አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር

የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር

አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር

#ነዳጅ #ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#AU #Ethiopia

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

በዚህም ዛሬ በተካሄደው ምርጫ #ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣለች።

@tikvahethiopia