TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የዜጎችድምጽ

" ወረዳው ከነእቃዬ ሜዳ ላይ ጥሎኝ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " - እንባ የሚተናነቃት ወጣት 


በአዲስ አበባ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቀበሌ 9/10 የምትገኝ ወጣት ከአሳዳጊ አክስቷ ጋር ትኖርበት ከነበረው የቀበሌ ቤት አሳዳጊዋ ስትሞት ከቤቱ እንድትወጣ ተደርጋ ጎዳና እንደወጣች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ አሰምታለች።

" ወረዳው ከነእቃዬን ሜዳ ጥሎ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " ብላለች።

ወርቅነሽ አለሙ የምትባለው ይህች ወጣት የአባቷ ታላቅ እህት ከ3 ዓመቷ ጀምሮ ከባህር ዳር ወደ አ/አ አምጥታት ነው ያሳደገቻት።

እዚሁ ቤት እስከ 2016 ዓ/ም ማለቂያ ድረስ ነበሩ።

በ2016 ዓ/ም አሳዳጊ አክስቷ ከሞትች ከ40 ቀናት በኃላ ወረዳው " ወራሽ ልጅ ስላልሆሽ ልቀቂ " ይላታል።

ጉዳዩን ይዛ ፍርድ ቤት ሄደች። ፍርድ ቤትም ሄዳ መፍትሄ አልተሰጣትም።

" ወረዳ እኔን ጠዋት በግብረ ኃይል ከነእቃዬ አውጥቶ ጥሎኝ ከሰዓት በኋላ ራሱ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ቤቴ ውስጥ አስገባው " ስትል ቅሬታ አሰምታለች።

ከዚህ አለፍ ሲል ቤቱ ሁለት ክፍል ሆኖ ሳለ ወደ አራት ክፍል አስፋፍቶ ሰርቶት ዞር ብሎ የጠየቀው አካል የለም ብላለች።

ወረዳው ምን ምላሽ ሰጠ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን ይዞ የወረዳ 6 ጽ/ቤት አስተዳደር ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሂጂቱን አነጋግሯል።

ቅሬታዋ አቅራቢዋ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብት እንዳላት አምነውበታል።

ኃላፊው ፤ " ባለመብት ናት የቀበሌ ቤት መውረስ የሚችለው ልጅ ነውና ልጅ ከሆነች መውረስ መብቷ ነው " ብለዋል።

" በሕጉ መሠረት የቀበሌ ቤት ፣ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብቷ የተጠበቀ ነው ፤ በዚያ ደረጃ ሆኖ ከነበረ እኔ ጋ ይምጡ እናስተካክላለን ይሄ የተነሳው ጉዳይ ትክክል ከሆነ " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ግልጽነት ስለሚፈልግ የሕግ ባለሙያ አነጋግሯል።

የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ምን አሉ ?

- ኑዛዜውን ማጽደቅ ትችላለች። ግን የቀበሌ ቤት ላይ ተወላጆች ካልሆኑ በስተቀር ከሕግ አንጻር በባዮሎጂካል ተወላጅ ያልሆነ ልጅ የጉጂፈቻ ማስረጃ ቀደም ሲል ሊኖር ይገባል።

- ለቀበሌ ቤት የጉዲፈቻ ማስረጃ ስሌላት ውርስ ተቀባዩዋን ከሞራልና ከአስተዳደራዊ አንጻር ካልሆነ በስተቀር ከሕግ አንጻር የወረዳው አስተደዳደር ሊያስተናግዳት አይችልም። 

- ከሞራል አንጻር አሳዳጊዋ ስላረፉ፣ ልጅቷ ደግሞ ተተኪ ልጅ ናት፤ በሥነ ልቦና እናትና ልጅ ሆነው አብረው ኖረዋል። የቀበሌ ቤት የሚባለው ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሚኖበት ነው። ስለዚህ ከሕግ አንጻር የኑዛዜ ተቀባይ መሆን ባትችልም አንዱ ወጥቶ ሌላው የሚገባበት፣ ለዜጎች የተሰራ ቤት በመሆኑ ልትኖርበት ይገባ ነበር ከሞራል አንጻር።

- ከሕግ አንጻር  በቀበሌ ቤት ላይ ኑዛዜ ማድረግ አይቻልም። 

- ለምሳሌ የፌደራል ኪራይ ቤቶችን አንድ ሰው ተከራይቶ ቢኖር ሲሞት ሊናዘዝበት አይችልም። ምክንያቱም የንብረቱ ባለቤት መንግስት ነው። በመሳሳይ ሁኔታ የቀበሌ ቤቶች ውስጥ የሚኖር ሰው ሲሞት ኑዛዜ ሊያደርግ አይችልም። ኑዛዜ ማድረጉ በሕግ ውጤት አያመጣም።

- በዜጎች ንብረትና ሕይወት ላይ ውሳኔ የሚሰጡ ሰዎች (ዳኞች) ከወረዳ ጋር በመመሳጠር ክርክር በተነሳበት የመንግስት ቤት ውስጥ መግባት የሕግ ጥሰት ነው። ሕግን ያልተከተለ አካሄድ ነው። በተወሰነ ደረጃ ሙስና ተብሎ ጉዳዩን ወደ ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ብታመለክትበት ዳኛው ከኃላፊነቱ የሚነሳበት ቀጥተኛ ማስረጃ ነው የሚሆነው።

- ክርክር በተነሳበት ጉዳይ ላይ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር እንዲህ ማድረግ ትልቅ የዲሲፒሊን ጥፋት ነው።

- ልጅቷ ቅጹ ላይ አለች፣ ደባል ናት፣ የቤተሰብ አባል ናት ቀጥተኛ ልጅ ባትሆንም፣ የቀበሌ ቤቶች ደግሞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎቸ ነው የተዘጋጁት፣ ሜዳ ላይ መጣል የለባትም ብሎ የወረዳው አስተዳደር ወስኖ ወይ በዚያው ቤት ሊያስቀጥላት ይገባል የቀበሌ ቤቱ የሚፈርስ ከሆነም ምትክ የመንግስት ቤት እንድታገኝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት። 

- በህሊና ፍርድ ወይ አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ የወረዳው አስተዳደር መፍትሄ ሊሰጣት ይገባል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-08

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM